ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “እግዚ/ር ሁሌም በሕይወታችን ውስጥ አዲስ ክስተት እንዲፈጠር ያደርጋል”

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዛሬው እለት ማለትም በታኅሳስ 11/2011 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው የቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ለተገኙ ቀሳውስት፣ ደናግላን እና ምዕመናን ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያሰሙት ስብከት በእለቱ ከሉቃስ ወንጌል 1፡26-38 ላይ ተወስዶ በተነበበው “በስድስተኛውም ወር መልአኩ ገብርኤል ናዝሬት ወደምትባል ወደ ገሊላ ከተማ፥ ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ፥ የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ። መልአኩም ወደ እርስዋ ገብቶ። ደስ ይበልሽ፥ ጸጋ የሞላሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ አላት። እርስዋም ባየችው ጊዜ ከንግግሩ በጣም ደነገጠችና። ይህ እንዴት ያለ ሰላምታ ነው? ብላ አሰበች። መልአኩም እንዲህ አላት። ማርያም ሆይ፥ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግኝተሻልና አትፍሪ።እነሆም፥ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ” (ሉቃስ 1፡26-31) በሚለው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ መሰረቱን ያደርገ እንደ ነበረ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ይህ የመልኣኩ ገብርኤል ብሳራት የሰው ልጆችን ታሪክ በከፍተኛ ሁኔታ የቀየረ መሆኑን ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
በዛሬው እለት ከሉቃስ ወንጌል 1፡26-38 የተጠቀሰው መልአኩ ገብርኤል ማርያምን ያበሰረበት ሁኔታ ላይ ተመሥርቶ “ስብከት ማድረግ በጣም አስቸጋሪ” ነው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ሰዎችን በድንገተኛ ስጦታው የምያስደንቀው እግዚኣብሔር የሰዎችን የግል እቅዶች ሲቀይር እንመለከታለን ብለዋል። ቅዱስነታቸው ይህንን ሐሳባቸውን በሚገባ ለማብራራት በማሰብ የሚከተለውን ብለዋል. . .

ዛሬ ከሉቃስ ወንጌል (1፡26-38) ተወስዶ ሲነበብ የሰማነው የቅዱስ ወንጌል ክፍል በታሪክ ውስጥ እጅግ በጣም ወሳኝ የሆነ ጊዜን እና ታላቅ የሆነ ለውጦች መከሰታቸውን ይነግረናል። ይህ በጣም አስጊ የሆነ ሁኔታን ይፈጥራል፣ ሁሉም ነገር ይለዋወጣል፣ ታሪኩ ይቀየራል። በዚህ የቅዱስ ወንጌል ጥቅስ ላይ ተንተርሶ መስበክ በጣም አስቸጋሪ ነው። በተጨማሪም በገና በዓል ወቅት ወይም ደግሞ የማርያምን መበሰር በምናከብርበት ወቅት ይሕንን የሐያምኖት ምስጢር ተንበርክከን እንደግማለን። ምክንያቱም ይህ ሁሉንም ነገር ከሥር መሰረቱ የቀየረ ጉዳይ ነው። በሥርዓተ አምልኮዋችን ደንብ መሰረት ዛሬ ሁሉም ነገር ከሥር መሰረቱ የተቀየረበትን ቀን እናከብራለን። በዛሬው ሥርዓተ አምላኮ መግቢያ ላይ የተጠቀሰው የመግቢያ ሐሳብ “ከእሴይ ግንድ በትር ይወጣል፥ ከሥሩም ቁጥቋጥ ያፈራል” (ኢሳ. 11፡1) በማለት ስለሥር መሰረት ይናገራል። እግዚኣብሔር ራሱን ዝቅ ያደርጋል፣ እግዚኣብሔር በእኛ ታሪክ ውስጥ ይገባል፣ ይህንንም የምያደግረው ቀደም ሲል እንደ ሚፈጽመው አስገራሚ እና ድንገተኛ በሆነ መልኩ ነው። የምያስገርሙ ድንቅ ነገሮች የተሞላው እግዚኣቤር አሁንም እኛን ድነገተኛ በሆኑ ነገሮች ያስገርመናል።

ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን በቀጠሉበት ወቅት እርሳቸው በወቅቱ ከሉቃስ ወንጌል 1፡26-38 ላይ ተወስዶ በተነበበው እና መልአኩ ገብርኤል ማርያምን ያበሰረበትን ታሪክ የሚገልጸው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ ተንተርሶ አስተንትኖ መስጠት አሰችጋሪ እንደ ሆነ መገለጻቸው የሚታወስ ሲሆን በዚህም ምክንያት ምእመኑ ይህንን የቅዱስ ወንጌል ክፍል በሚገባ ለመረዳት ይችል ዘንድ በማሰብ እና ሐሳባቸውን ግልጽ ለማድረግ በማሰብ የሚከተለውን ብለዋል . . .

“ማርያም ሆይ በእግዚኣብሔር ፊት ሞገስ አግኝተሻልና አትፍሪ፣ እነሆ መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይወርዳል፣ የልዑል እግዚኣብሔር ኃይል በአንቺ ላይ ይሆናል። እነሆ ትጸንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ ከአንቺ የሚወለደው ልጅ የልዑል እግዚኣብሔር ልጅ ይባላል። መካን የተባለችው ዘመድሽ ኤልሳቤጥ ጸንሳላች። ከጸነሰች እንሆ ስድስተኛ ወሩዋ ነው፣ ለእግዚአቤር የሚሳነው ነገር የለም” በማለት መልአኩ ያበስራታል። ከዚያም በኃላ ማርያም “እነሆኝ የእግዚኣብሔ አገልጋይ እንዳልከኝ ይሁንልኝ” ከዚያም በኋላ መልኣኩ ከርሷ ተለይቶ ሄደ።

 

20 December 2018, 16:13