ፈልግ

የቫቲካን ከተማ ግዛት ዋና አስተዳደር የቫቲካን ከተማ ግዛት ዋና አስተዳደር  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ለቫቲካን ከተማ ግዛት ዋና አስተዳደር ያወጡት አዲስ ሕግ ያፋ መሆኑ ተገለጸ።

አዲሱ እና የተሻሻለው የቫቲካን ከተማ ግዛት አዲሱ ሕግ ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ የአሠራር ስልቶችን፣ ግልጽነት፣ የቁጥጥር ስርዓት እና የአደረጃጀት ቅንጅትን የተመለክቱ ሕጎችን በዋነኛነት አቅፎ የያዘ ነው

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በመሆናቸው ያላቸው ሐዋርያዊ ስልጣን ወይም ሐዋርያዊ ኃላፊነት በሚፈቅድላቸው መሰረት በላቲን ቋንቋ (Motu Proprio) በአማርኛው በግርድፉ ሲተረጎን (በራሳቸው ተነሳሽነት ለቤተ ክርስቲያኗ አጠቃላይ መንፈሳዊ እና አስተዳደራዊ ጉዞ ይጠቅማል ብለው ያመኑበትን መልእክት ወይም ሕግጋትን ያመልክታል) በዚህም መሰረት በኅዳር 26/2011 ዓ.ም ይፋ ባደርጉት መልእክት የቫቲካን ከተማ ዋና አስተዳደር ቢሮ የሚተዳደርበትን አዲስ ሕግ ይፋ ማድረጋቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ይህ በቅዱስነታቸው ይፋ የሆነው አዲሱ ሕግ ከሚቀጥለው ሰኔ ወር አንስቶ በተግባር ላይ የሚውል ሕግ እንደ ሆነ ተያይዞ የተገለጸ ሲሆን ይህ አዲሱ ሕግ በሥራ ላይ የሚውለው የቫቲካን ከተማ ግዛት አስተዳደርን በማነኛውም አስፈላጊ እና ሕጋዊ በሆነ መንገድ ለማስተዳደር ታልሞ የተረቀቀ አዲስ ሕግ ሲሆን ይህም ቤተ ክርስቲያኗ በዓለም ዙርያ እያከናወነች የምትገኘውን ሐዋርያዊ አገልግሎት ይበልጥ ተስማሚ እና ውጤታም በሆነ መልኩ እንድታከናውን የምያስችላት እና የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስት በዓለም ዙርያ የሚያደርጉትን ተልዕኮ ውጤታማ በሆነ መልኩ ለማስፈጸም እንደ ሚረዳ ታምኖ የተረቀቀ ሕግ ነው።

ይህ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በኅዳር 26/2011 ዓ.ም ይፋ የሆነው የቫቲካን ከተማ ግዛት ዋና አስተዳደር አዲሱ ሕግ እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከመጪው ሰኔ 07/2019 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ ላይ የሚውል ሕግ እንደ ሆነ በመግለጫው ወቅት የተገለጸ ሲሆን ይህ አዲሱ ሕግ እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በኅዳር 11/2000 ዓ.ም በወቅቱ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነበሩት በዮሐንስ ጳውሎስ ሁለተኛ ጸድቆ ላለፉት 18 ዓመታት የቫቲካን ከተማ ግዛት ዋና አስተዳደር መተዳደሪያ ሆኖ የቆየውን ሕግ የሚተካ እንደ ሆነ ለመረዳት ተችሉዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በኅዳር 26/2011 ዓ.ም ይህንን አዲሱን የቫቲካን ከተማ ግዛት ዋና አስትዳደር  የማሻሻያ ሕግ ይፋ ባደርጉበት ወቅት እንደ ገለጹት የዚህ ሕግ ማሻሻያ ተመጣጣኝ እና ምክንያታዊ በሆነ መልኩ ኢኮኖሚያዊ እና  ተያያዥነት ያላቸውን ጉዳዮች ቀለል ባለ መልኩ ለማስተዳደር የሚረዱ አራት ዋና ዋና መርሆዎችን እና መመዘኛዎችን አቅፎ የያዘ ሕግ መሆኑን ገልጸው በዚህም መሰረት ይህ አዲሱ እና የተሻሻለው የቫቲካን ከተማ ግዛት አዲሱ ሕግ ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ የአሠራር ስልቶችን፣ ግልጽነት፣ የቁጥጥር ስርዓት እና የአደረጃጀት ቅንጅትን የተመለክቱ ሕጎችን በዋነኛነት አቅፎ መያዙን መግለጻቸው ይታወቃል።

ለቫቲካን ከተማ ግዛት ዋና አስተዳድር የወጣው አዲሱ ሕግ ከዚህ በፊት በዋና አስተዳደሩ ሥር ይተዳደሩ የነበሩ ዘጠኝ የሥራ አስፈጻሚ ተቋማት አንዳንዶቹን በማጠቃለል ቁጥራቸው ወደ ሰባት እንዲቀንስ መደረጉን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በዚህም መሰረት ቀደም ሲል የነበሩት የሥራ አስፈጻሚ ተቋማትን በማጠቃለል የመሰረተ ልማት እና የአገልግሎት መስጫ ተቋም፣ የቴለኮሚንኬሽን እና የኢንፎርማሽን ቴክኖሎጂ ተቋም፣ የኢኮኖሚ ተቋም፣ የደህንነት አገልግሎቶች እና የሲቪል ጥበቃ ተቋም፣ የጤና እና የንጽህና መስጫ ተቋም፣ የቫቲካን ሙዚዬም እና የታሪካዊ ቅርስ መጠበቂያ ተቋም እንዲሆን ተደርጉዋል። በተጨማሪም የቫቲካን ከተማ ግዛት ዋና አስተዳደር ሥር ሲተዳደሩ የነበሩ አምስት ማዕከላዊ ቢሮዎች ወደ ሁለት በመጠቃለል የሰራተኞች ጉዳይ ማስፈጸምያ ጽ / ቤት እና የፍትህ ቢሮ በመሆን እንዲቀጥሉ ተወስኑዋል።

 

06 December 2018, 16:24