ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ 

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ መልካም ፖለቲካ ለሰላም

የከፍተኛ ፍቅር መግለጫ እና የልግስና ልምዶች አንዱ አካል የሆነው የፖለቲካዊ ቁርኝነት ለሕይወት እና ለዓለማችን እንዲሁም በጣም ወጣት እና ተጋላጭ ለሆኑ ዜጎች የወደፊቱ ፍላጎቶቻቸውን በሚገባ ለሟሟለት ከፍተኛ የሆነ ጥረት ማድረግን የሚጠይቅ እንደ ሆነ፣ በዚህም የተነሳ ማነኛውም ዜጋ ሰላምን ለማረጋገጥ ይቻል ዘንድ በፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ በንቃት መካፈል ይኖርበታል የሚል እንድምታ ያዘለ መልእክት ነው።

መልካም ፖለቲካ ለሰላም

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እ.አ.አ. በመጭው ጥር 1/2011 ዓ.ም ለሚከበረው 52ኛው ዓለማቀፍ የሰላም ቀን ይሆን ዘንድ የመረጡት መሪ ቃል “መልካም ፖለቲካ ለሰላም” የሚለው እንደ ሆነ የተገለጸ ሲሆን እውነተኛ ፖለቲካ ሰብአዊ መብቶችን የሚያከብር እና የሚያስከብር፣ የዘጎችን ስብዕና የሚገነባ፣ ወጣቶችን የሚያበረታታ ከሆነ ፖለቲካ የበጎ አድራጎት እና ለሰላም ግንባታ አገልግሎት የሚውል ድንቅ መሳርያ ይሆናል ማለት ነው ማለታቸው ተገልጹዋል።
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

“የፖለቲካ ኃላፊነት ለሁሉም ዜጎች፣ በተለይ ደግሞ ሕዝቡን ለመጠበቅ እና ለመምራት ስልጣን በተሰጣቸው ሰዎች ትክሻ ላይ እንደ ሆነ” የሚገልጸው መልእክቱ የአውሮፓዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የዓለማችን ማኅበረሰቦች ዘንድ በሚከበረው የ2019 ዓ.ም አዲስ አመት መባቻ ላይ ለሚከበረው ዓለማቀፍ የሰላም ቀን ይሆን ዘንድ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የተመረጠው መሪ ቃል “መልካም ፖለቲካ ለሰላም” የሚለው እንደ ሆነ ቀደም ሲል መግለጻችን ይታወሳል።
ሰላም ሊረጋገጥ የሚችለው በመተማመን መንፈስ ብቻ ነው
“የዚህ ‘መልካም ፖለቲካ ለሰላም’ በሚል አርእስት የቀረበው የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ መልእክት ዋነኛው ተልዕኮ ሕገ-ወጥነትን በማስወገድ፣ የሰዎችን ሰብዓዊ መብቶች በማረጋገጥ እና በማኅበረሰቡ ውስጥ የተለያዩ ሚናዎችን የሚጫወቱ አካለት መካከል ውይይት እንዲፈጠር በማድረግ በአዲሱ ትውልድ እና በባሕል መካከል ያለውን ልዩነት በውይይት በመፍታት ሰላምን ማረጋገጥ” የሚል ተልዕኮ ያነገበ መልእክት እንደ ሆነ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በአንድ ማኅበርሰብ ውስጥ እርስ በእርስ የመተማመን መንፈስ የሌለ እንደ ሆነ ሰላምን ማረጋገጥ እጅግ ከባድ እንደ ሚሆን በሰፊው የምያትት መልእክት ነው። የከፍተኛ ፍቅር መግለጫ እና የልግስና ልምዶች አንዱ አካል የሆነው የፖለቲካዊ ቁርኝነት ለሕይወት እና ለዓለማችን እንዲሁም በጣም ወጣት እና ተጋላጭ ለሆኑ ዜጎች የወደፊቱ ፍላጎቶቻቸውን በሚገባ ለሟሟለት ከፍተኛ የሆነ ጥረት ማድረግን የሚጠይቅ እንደ ሆነ፣ በዚህም የተነሳ ማነኛውም ዜጋ ሰላምን ለማረጋገጥ ይቻል ዘንድ በፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ በንቃት መካፈል ይኖርበታል የሚል እንድምታ ያዘለ መልእክት ነው።
ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ታዳሚዎች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በመጭው ጥር 1/2011 ዓ.ም ለሚከበረው 52ኛው ዓለማቀፍ የሰላም ቀን ይሆን ዘንድ “መልካም ፖለቲካ ለሰላም” በሚል አርእስት በኅዳር 30/2011 ዓ.ም ይፋ ያደረጉትን መልእክት የመጀምርያ ክፍል እንደ ሚከተለው አቅርበነዋል ተከታተሉን።

መልካም ፖለቲካ ለሰላም

ክፍል አንድ

1. “ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን!”
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያቱን ለመንፈሳዊ ተልዕኮ በላከበት ወቅት “ወደምትገቡበት ቤት ሁሉ አስቀድማችሁ ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን በሉ። በዚያም የሰላም ልጅ ቢኖር፥ ሰላማችሁ ያድርበታል፤ አለዚያ ግን ሰላማችሁ ይመለስላችኋል” (ሉቃ 10፡5-6) በማለት ልኮዋቸው ነበር። ሰላም ማረጋገጥ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ከተሰጣቸው ተልዕኮዎች መካከል ቀዳሚው ነው። በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ በምያሳዝን እና አሰቃቂ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ ሰላምን ለማግኘት ለሚፈልጉት ወንዶች እና ሴቶች ሁሉ ይህ ሰላም ይሰጣቸዋል። ኢየሱስ "ቤት" በማለት የተናገረው በሁሉም ስብዕና እና ታሪክ ውስጥ ያለ እያንዳንዱ ቤተሰብ፣ ማኅበረሰብ፣ አገር እና አህጉር ነው። ከሁሉም በላይ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው ማንንም ሳያገል እና ምንም ዓይነት ልዩነት ሳይፈጠር ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው እያንዳንዱ ግለሰብ ነው። በመቀጠል እግዚኣብሔር እንድንከባከበው እና እንድንጠብቀው የሰጠንን "የጋራ መኖርያ ቤታችን” የሆነውን ዓለማችንን ይመለከታል። በመሆኑም በአዲሱ ዓመት መጀመሪያ ላይ “ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን” በማለት ሰላምታዬን ላቀርብላችሁ እወዳለሁ።
2. መልካም ፖለቲካ የሚገጥሙት ተግዳሮቶች
ገጣሚው ቻርለስ ፒዬጊ (እ.አ.አ 1914 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት የተለየ ፈረንሳዊ ገጣሚ ነው) እንደገለጸው ሰላም የተስፋ በዓል ነው። ልክ በአንድ ድንጋያማ በሆነ ስፍራ ላይ ለመብቀል ወይም ለማበብ እንደ ሚፈልግ አበባ ዓይነት ነው። ፖለቲካ በሰብአዊ ህብረተሰብ እና ተቋማትን መገንባት የምያስችል ወሳኝ ዘዴ ነው፣ ነገር ግን የፖለቲካ ህይወት ለህብረተሰብ አጠቃላይ አገልግሎት የማይውል ከሆነ ግን በተቃራኒው የጭቆና፣ የማግለያ እና በተጨማሪም የጥፋት መንገድ ሊሆን ይችላል።
ኢየሱስ እንዲህ ይላል “የሁሉም የበላይ ሊሆን የሚፈልግ ሰው የሁሉም አገልጋይ ይሁን” (ማር. 9፡35) ይለናል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ 6ኛ “በአገር ውስጥ፣ በክልል፣ በብሔራዊ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በፖለቲካዊ አቋም መገንባት - ማለት እያንዳንዱ ግለሰብ እውነታውን እንዲረዳ እና ነጻነት ክብር የሚሰጠው እሴት መሆኑን በመረዳት ለእያንዳንዱ ግለሰብ፣ ለከተማው፣ ለሀገር እና በአጠቃላይ ለሰብዓዊ ፍጡር መልካም ተግባሮችን በአንድነት እንዲሠራ መንገዱን መክፈት ማለት ነው” ማለታቸው ይታወሳል።
ስለዚህ የፖለቲካ አገልግሎት እና የፖለቲካ ሃላፊነት ይህንን አገልግሎት ለሀገራቸው እየሰጡ ለሚገኙ ሰዎች ከፍተኛ የሆነ ጥረት በማደረግ በሀገራቸው የሚኖሩ ስዎችን ለመጠበቅ እና ለአሁኑ እና ለሚመጣው የወደፊት ጊዜ መልካም ሁኔታዎችን ለመፍጠር የተቻላቸውን ሁሉ ጥረት እንዲያደርጉ የሚገፋፋ ነው። ፖለቲካ ለሰዎች መሠረታዊ ክብር መረጋገጥ የሚውል ከሆነ፣ ለነጻነት እና ሰብዓዊ የሆኑ መብቶችን ለማስከበር የሚተጋ ፖለቲካ ከሆነ የፓለቲካ ሕይወት የላቀ የፍቅር መገለጫ ሊሆን ይችላል።

 

18 December 2018, 15:51