ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ እና ር.ሊ.ጳ በነዴክቶስ 16ኛ ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ እና ር.ሊ.ጳ በነዴክቶስ 16ኛ 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የቀድሞ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ር.ሊ.ጳ የነበሩትን በነዴክቶስ 16ኛ ጎበኙ

ባለፈው ታኅሳስ 12/2011 ዓ,ም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የገናን በዓለ አስመልክተው የቀድሞ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት እና ከርዕሰ ሊቃነ ጵጵሳናቸው በገዛ ፈቃዳቸው የዛሬ ስድስት አመት ገድማ የለቀቁትን በነዴክቶስ 16ኛን  በቫቲካን በሚገኘው እና እርሳቸው በሚኖሩበት ገዳም ተገኝተው መጎብኘታቸው ተገለጸ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በየአመቱ የገና በዓል መባቻ ላይ የቀድሞውን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዴክቶስ 16ኛ የመጎኘት ልምድ እንዳላቸው የሚታወቅ ሲሆን በቅርቡ በተመሳሳይ መልኩ በጥቅምት ወር ላይ ቅዱስ ጳውሎስ 6ኛ የቅድስና ማዕረግ በተቀበሉበት ወቅት ይህንን በዓል እንዲታደሙ ለመጋበዝ በማሰብ በቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዴክቶስ 16ኛ የሚኖሩበት ገዳም ድረስ በመሄድ መገናኘታቸው ይታወሳል። 

Photogallery

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ እና ር.ሊ.ጳ በነዴክቶስ 16ኛ
24 December 2018, 16:29