ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “እግዚኣብሔር በልባችን ውስጥ ካለ ሕይወታችን በደስታ ይሞላል!”

እግዚኣብሔር በመካከላችን ካለ እውነተኛ የሆነ ሰላም እና ደስታን እናገኛለን

የአውሮፓዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን በታላቅ መንፈሳዊነት ለማክበር ያስችለን ዘንድ የመዘጋጃ ወቅት የሚሆነን የስብከተ ገና ሳምንት በኅዳር 23/2011 ዓ.ም መጀመሩ ይታወሳል። በዚህም መሰረት በትላንትናው እለት ማለትም በታኅሳስ 07/2011 ዓ.ም ሦስተኛው የስብከተ ገና ሳምንት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮሰ አደባባይ ተከብሮ ማለፉን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በወቅቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በእለቱ ስርዓተ አምልኮ ወቅት በተነበቡት ምንባባት ላይ ተመርኩዘው ቅዱስነታቸው ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት “እግዚኣብሔር በልባችን ውስጥ ካለ ሕይወታችን በደስታ ይሞላል” ማለታቸውን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን እግዚኣብሔር በመካከላችን ካለ እውነተኛ የሆነ ሰላም እና ደስታን እናገኛለን ብለዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ክቡራ እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በታኅሳስ 07/2011 ዓ.ም በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን ያደርጉትን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉን እንጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

የእዚህ የሦስተኛው የስብከተ ገና ሳምንት ስርዓተ አምልኮ ደስተኞች እንድንሆን ይጋብዘናል። መልካም ስሜት እንዲሰማን፣ ደስተኞች እንድንሆን ይጋብዘናል። ነቢዩ ሰፎኒያስ እነዚህን የደስታ ቃላት ለእስራኤል ሕዝብ በትንሹ በማካፈል ሲናገር “የጽዮን ልጅ ሆይ፥ ዘምሪ፤ እስራኤል ሆይ፥ እልል በል፤ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ በፍጹም ልብሽ ሐሤት አድርጊ ደስም ይበልሽ” (ት.ሶፎኒያስ 3፡14) በማለት ይናገራል። የዛሬው እለተ ሰንበት በደስታ እንድንቧርቅ፣ ደስ እንዲለን ይጋብዘናል። እግዚአብሔር በቅድስቲቷ ከተማ ላይ የጣለውን ፍርድ ስለአስወገደ የቅዲስቲቷ ከተማ ነዋሪዎች ደስ እንዲላቸው ይጋብዛል። እግዚኣብሔር ቅጣት አልበየነባቸውም፣ እግዚኣብሔር ይቅር ብሉዋቸዋል። በዚህም ምክንያት ሕዝቡ የሚያዝኑበት ምንምዓይነት ምክንያት የላቸውም፣ ምቾት የሚናሳቸው ምንም ዓይነት ምክንያት የላቸውም፣ ሁልጊዜም ቢሆን የሚወዳቸውን ለማዳን ወደ ሚፈልገው ወደ እግዚኣብሔር በደስታ ይጮኻሉ። እግዚኣብሔር ለእርሱ ሕዝብ ያለው ፍቅር ከፍተኛ ነው፣ አንድ አባት ልጁ ካለው ፍቅር ጋር ማነጻጸር ይቻላል፣ አንድ ሙሽራ ለሙሽሪት ካለው ፍቅር ጋር ማነጻጸር ይቻላል፣ ነቢዮ ሰፎኒያስ በድጋሚ እንደ ሚለው “አምላክሽ እግዚአብሔር በመካከልሽ ታዳጊ ኃያል ነው፤ በአንቺ ደስ ይለዋል፥ በፍቅሩም ያርፋል፥ በእልልታም በአንቺ ደስ ይለዋል” (ሰፎንያስ 3፡17) ይላል። ይህ ሰንበት የደስታ ሰንበት የተባለውም በዚሁ ምክንያት ነው፣ ከገና በፊት ያለው ሦስተኛው የስብከተ ገና ሳምንት የደስታ ሰንበት ተብሎ የሚጠራውም በዚሁ ምክንያት ነው።

ይህ የነቢዩ ሰፎኒያስ ጥሪ በተለይም ደግም አሁን የገናን በዓል ለማክበር በምንዘጋጅበት በአሁኑ ወቅት በጣም ተገቢ የሆነ ጥሪ ነው፣ ምክንያቱ ይህ ጥሪ ለኢየሱስ፣ ለአማኑኤል፣ እግዚኣብሔር ከእኛ ጋር ነው የሚለውን ትርጉም ስለሚያሰማ የእርሱ በእኛ መካከል መገኘት ደግሞ የደስታችን ሁሉ ምንጭ ስለሆነ ነው። በእርግጥ ነብዩ ሰፎኒያስ “የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር በመካከልሽ አለ” ከዚያም ትንሽ ወረድ ብሎ ደግሞ “አምላክሽ እግዚአብሔር በመካከልሽ የሚኖር ታዳጊ ኃያል ነው” ያለውም በዚሁ ምክንያት ነው። ይህ መልዕክት ወንጌላዊው ሉቃስ እንደ ሚተርከው መልኣኩ ገብሬል ማርያምን ባበሰራት ወቅት ሙሉ የሆነ ትርጉም ያገኛል። መልኣኩ ገብርኤል ለማርያም የተናግራቸው ቃላት የነቢዩ ሰፎኒያስን ቃላት የምያስተጋቡ ናቸው። መልኣኩ ገብርኤል ማርያምን “ጸጋ የተማላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ፣ እግዚኣብሔር ከአንቺ ጋር ነው” (ሉቃ. 1፡28) በማለት ነበር የተናገረው። “ደስ የበልሽ” ነበር ያላት። በገሊላ በሚገኝ ገጠራማ መንደር ውስጥ፣ በአለም ሕዝቦች ብዙም በማትታወቀው ወጣት ሴት አማካይነት እግዚአብሔር በመላው ዓለም ውስጥ ደስታን ስያስፍን እናያለን። ዛሬም ተመሳሳይ የሆነ አዋጅ ለቤተክርስቲያኗ የቀረበ ሲሆን ወንጌልን በመቀበል ተጨባጭ የሆነ ህይወት በመኖር “አንቺ ትኝሽዬ የክርስቲያን ማኅበረሰብ የተሰበሰበብሽ፣ ምሲኪን እና ትሁት ነገር ግን በእኔ እይታ ውብ የሆንሽ እና ወደ መንግሥቴ በመጓዝ ላይ ያለሽ፣ ፍትህን የተጠማሽ እና የተራብሽ፣ በትዕግስት የተሞላሽ፣ ኃያላንን ሳይሆን ከድሆች ጋር በታማኝነት የምትቆይ አንቺን ደስ ይበልሽ” በማለት ለቤተ ክርስቲያን ጥሪ ያቀርባል። እኛ ሁል ጊዜ በዚህ አኳን የምንጓዝ ከሆንን ልባችን በጌታ ደስታ የተሙላ ይሆናል። ከሁሉም በላይ ደግሞ የደስታዎች ሁሉ የበላይ የሆነውን ሰላም እናገኛለን። ቅዱስ ጳውሎስ በበኩሉ በማንኛውም ሁኔታ ጥያቄዎቻችንን፣ ፍላጎቶቻችንን፣ ስጋቶቻችንን በጸሎትና በልመና ወደ እግዚአብሔር "አቅርቡ" በማለት ሰለምንም ነገር እንዳንጨነቅ ይጋብዘናል። በችግሮች ውስጥ ሁሌም ወደ ጌታ መመለስ እንደምንችል እና እርሱ መቼም ቢሆን ጥያቄዎቻችንን ቸል እንደ ማይል ማወቁ በራሱ የደስታ ምንጭ ነው። ምንም ዓይነት ጭንቀት፣ ምንም ዓይነት ፍርሃት ሰላማችንን ሊነጥቀን አይችልም፣ ከእግዚኣብሔር የሚመጣ ሰላም ሁሌም ከእኛ ጋር የሚሆን እና ሕይወታችን የተረጋጋ እንዲሆን የሚያደርገን ሰላም ነው። ችግሮችና መከራዎች ቢኖሩም እንኳ ይህ ተስፋ ብርታትና ድፍረት ያጎናጽፈናል። እኛ የጌታን የደስታ ግብዣ ለመቀበል ራሳችን ፈቃደኞች መሆን አለብን። ታዲያ ይህ ምን ማለት ይሆን? በዛሬው ቅዱስ ወንጌል ውስጥ እንደ ተጠቀሰው የመጥምቁ ዮሐንስን ስብከት ሰምተው “ታዲያ እኛስ ምን እናድርግ? ምን ዓይነት ተግባር መፈጸም አለብን? (ሉቃስ 3፡10) ብለው ሕዝቡ ወደ ንስሐ እንደ ቀረቡ ሁሉ እኛም ተመሳሳይ ጥያቄ ለጌታ ማንሳት ይኖርብናል። ይህም ጥያቄ በዚህ በያዝነው የስበከተ ገና ወቅት ልናነሳው የሚገባን ጥያቄ ነው፣ በዚህም መንገድ መንፈሳዊ ለውጥ ለማምጣት እንችላለን። እያንዳንዳችን “ምን ማድረግ አለብኝ?” በማለት ጥያቄን ማንሳት ይኖርብናል። እናታችን የሆነችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልባችንን ዘለዓለማዊ ለሆነው ለእግዚኣብሔር መክፈት እንችል ዘንድ እንድትረዳን፣ ዘላቂነት ያለው እውነተኛ ደስታን ማግኘት እንችል ዘንድ እንድትረዳን አማላጅነቷን መማጸን ያስፈልጋል።

17 December 2018, 16:20