ፈልግ

የአዲሱ “ውዳሴ ላንተ ይሁን” መጽሐፍ የሽፋን ገጽ፣ የአዲሱ “ውዳሴ ላንተ ይሁን” መጽሐፍ የሽፋን ገጽ፣ 

የር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ “ውዳሴ ላንተ ይሁን” ሐዋርያዊ መልዕክት በብዛት ታትሞ መውጣቱ ተነገረ።

በዘጋቢ ፍቶግራፍ አንሺነትና በጥናታዊ ፊልም ደራሲነት ለ72 ዓመታት ያህል የሠራው ጋዜጠኛ አቶ ያን አርቱስ በርትራንድ፣ “ምድር ከሰማይ ላይ ስትታይ” በሚል ርዕስ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ ዩኔስኮ፣ እንደዚሁም ከሌሎች ታዋቂ ከሆኑት የፊልም ደራሲዎች ጋር በመተባበር ምድራችን በዘመናችን የምትገኝበትን ሁኔታ በፎቶግራፍ የሚያሳይ የሥራ ዉጤት በ2001 ዓ. ም. ማሳተማቸው ይታወሳል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “ውዳሴ ላንተ ይሁን” በሚል ርዕስ ይፋ ያደረጉት ሐዋርያዊ መልዕክት ቁጥሩን በርከት በማድረግ፣ በውስጡም ፎቶግራፎችን በማካተት እንዲታትም መወሰኑ ታውቋል። በብዛት እንዲታተም የተደረገው የርዕሠ ሊቃነ ፍራንችስኮስ ሐዋርያዊ መልዕክት በውስጡ የተለያዩ ፍቶግራፎችን ይዞ እንዲወጣ የበኩላቸውን አስተዋጽዖ ያበረከቱት፣ የአካባቢ ጥናት ጥበብት የሆኑት ፈረንሳዊ ጋዜጠኛ አቶ ያን አርቱስ በርትራንድ መሆናቸው ታውቋል። ጋዜጠኛው ያሳተሙትና “ውዳሴ ላንተ ይሁን” የሚል ርዕሥ የተሰጠውን የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሐዋርያዊ መልክት እያንዳንዱ ሰው ተገንዝቦት፣ ለምንኖርባት ምድር እንክብካቤን እንዲሰጥ፣ ለፍጥረታት በሙሉ የሚገባውን አክብሮትና እንክብካቤን ካለመስጠት የተነሳ ወደ ጥፋት እንዳይሄድ ማድረግ እንደሚያስፈልግ አብራርተዋል።   

ለምድራችን የሚገባውን እንክብካቤ አልሰጠናትም፣

በዘጋቢ ፍቶግራፍ አንሺነትና በጥናታዊ ፊልም ደራሲነት ለ72 ዓመታት ያህል የሠራው ጋዜጠኛ አቶ ያን አርቱስ በርትራንድ፣ “ምድር ከሰማይ ላይ ስትታይ” በሚል ርዕስ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ ዩኔስኮ፣ እንደዚሁም ከሌሎች ታዋቂ ከሆኑት የፊልም ደራሲዎች ጋር በመተባበር ምድራችን በዘመናችን የምትገኝበትን ሁኔታ በፎቶግራፍ የሚያሳይ የሥራ ዉጤት በ2001 ዓ. ም. ማሳተማቸው ይታወሳል።

ድፍረት የታከለበት የሥራ ዉጤት፣

ሐይማኖት እንደሌላቸው የሚታወቁ ጋዜጠኛ አቶ ያን አርቱስ በርትራንድ፣ በአስታሳሰባቸውና በአቋማቸው የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳትን ሃሳብ የሚጋሩ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን “ውዳሴ ላንተ ይሁን” የተሰኘውን የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ መልዕክት በድጋሚ ያሳተሙት ድፍረት በተሞላ ልብ እንደሆነ ሲር ከተባለ የቤተክርስቲያን የዜና ማሰራጫ ማዕከል ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ገልጸዋል።

የእድገት ማነቆ፣

ጋዜጠኛ አቶ ያን አርቱስ በርትራንድ ከዜና ማሰራጭ ማዕከል ጋር ባደረጉት ቆይታ ወቅት እንደገለጹት አሳትመው ያወጡት፣ ውዳሴ ላንተ ይሁን መልዕክትን የካተተ መጽሐፍ ትልቅ ለውጥን ያመጣ እንደሆነ ገልጸው፣ በርካታ መንግሥታትና መንፈሳዊ ተቋማትም ቢሆኑ ምድራችን ያለችበትን ሁኔታ እውነትን ተከትለው አለመናገራቸውን ገልጸው፣ በሌላ ወገን ለምድራችን ሊሰጥ የሚገባውን እንክብካቤ ጥቂት መንግሥታት ብቻ እንደሚያከብሩ ገልጸዋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለምድራችንና በምድራችን ውስጥ ለሚገኘው ተፈጥሮ በሙሉ እንክብካቤን እንድንሰጥ በሚወተውቱበት ባሁኑ ጊዜ፣ ይህን የእርሳቸውን በጎ እቅድና ዓላማ የማይደግፉ አዳዲስ የሐይማኖት ወገኖች እየተወለዱ መሆኑን ጋዜጠኛው ገልጸዋል።                

06 December 2018, 16:23