ፈልግ

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ፡ “ነጻነት በአግባቡ እንድንጠቀም እግዚኣብሔር የስጠን ስጦታ ነው”!

ከሕዳር 13-16/2011 ዓ.ም ድረስ ስምንተኛው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ማኅበራዊ አስተምህሮ ፌስቲቫል የሰሜን ጣሊያን ግዛት በሆነችው በቬሮና በመካሄድ ላይ ይገኛል። በዚህ በስምንተኛው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ማኅበራዊ አስተምህሮ ፌስቲቫል ላይ ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ በርካታ ተሳተፊዎች መገኘታቸውን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ለዚህ ፌስቲቫል ተሳታፊዎች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ባስተላለፉት የቪዲዮ መልእክት ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት “ነጻነት ለሁሉም ሰው የተሰጠ እና ሁሉም በአግባቡ ሊጠቀምበት የሚገባው የእግዚኣብሔር ስጦታ ነው” ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ በቪዲዮ ያስተላለፉትን መልእክት ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል ተከታተሉን።

የተወደዳችሁ ጓደኞቼ

በዚህ በስምንተኛው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ማኅበራዊ አስተምህሮ ፌስቲቫል ላይ ተሳታፊ ለሆናችሁ ሁሉ  ሞቅ ያለ ሰላምታዬን አቀርባለሁ። የዚህ ፌስቲቫል አዘጋጆች "የሰዎችን አካሄድ ምንጊዜም ለመደገፍ በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ ጠለቅ ያለ አስተሳሰብ እንዲኖር ለመጋበዝ ነጻነትን አደጋ ላይ የሚጥሉ ጉዳዮች” የሚለውን መሪ ቃል መርጠዋል። ነገር ግን ብዙን ጊዜ የእግዚኣብሔር ታላቅ ስጦታ የሆነው የነፃነት ምኞት - የሰው ልጅ መጥፎ ጠላት የሆኑትን ጦርነቶች፣ የፍትሕ መዛባትና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እያስከሰተ ይገኛል።

በቅዱስ ወንጌል የምናምን ክርስቲያኖች እና ለወንድሞቻችን ያለንን ሃላፊነት የምንገነዘብ ሰዎች እንደ መሆናችን መጠን እኛም "ነጻነትን አደጋ ላይ የሚጥሉ ስጋቶች" ምን እንደ ሆኑ ለማወቅ ዋናውን እና እጅግ በጣም አስፈላጊ የሆነውን ትርጉም እንዳይስት ነቅተን በጥንቃቄ መጠበቅ እንደ ሚገባን ጥሪ ያቀርብልናል። “ነጻነትን አደጋ ላይ መጣል” ማለት በነጻነት መጫወት ማለት ነው። እኛ የተጠራነው አንድ ላይ በመሆን የሰዎችን ነጻነት አደጋ ላይ የሚጥሉ ነገሮችን ለማስወገድ አንድ ላይ እንድንሰራ ነው። በተመሳሳይ መልኩ እግዚአብሔር የሰጠንን "የጋራ መኖሪያችንን" እንዴት መጠበቅ እንዳለብን ጣዕሙን የሚሰጠን ነጻነት እንዴት በወጉ መጠቀም እንደ ሚገባን መመልከት ይገባናል።

ዛሬም ቢሆን ብዙ ወንዶችና ሴቶች ነፃነታቸውን በመልካም ሁኔታ መጠቀም የማይችሉባቸው በርካታ ሁኔታዎች አሉ፣ ነጻነታቸው አደጋ ላይ እንዲወድቅ የሚያደርጉ ብዙ ሁኔታዎች አሉ። ከእነዚህ መካከል ሦስቱን ለመጥቀስ እፈልጋለሁ፡ ድህነት፣ የቴክኖሎጂ የበላይነት እና የሰው ልጅ የፍጆታ እቃዎችን የመሸመት/በከፍተኛ ደረጃ የመጠቀም ባርነት ውስጥ መክተት የሚሉትን መጥቀስ ይቻላል።

በመጀመሪያ ደረጃ በየከተሞቻችን ውስጥም እንኳን ሳይቀር በመላው ዓለም በሚፈጸሙ ዋና ዋና ኢፍትሐዊ የሆኑ ድርጊቶች ያስከተሉት ትርፍ ድህነት ብቻ ነው። ይህ የምያመልክተው "በአሁን ጊዜ በሰፊው የሚታየውን ብዝበዛ እና ጭቆና ሳይሆን ከዚህ የተለየ አዲስ ነገር ነው፡ ስር መሰረታችንን በመዘንጋት የማኅበረሰቡ አንድ አካል መሆናችንን በመዘንጋት ብዙዎችሁ ከዚህ እንዲገለሉ እየተደረገ ይገኛል፣ ምንም ዓይነት ጉልበት ስለሌላቸው ከሁሉም ነገር ውጪ ይሆናሉ። የተገለሉ ሰዎች ተበዝብዘዋል ማለት ግን አይደለም፣ ነገር ግን እንደ ማያስፈልጉ እንደ ትርፍ ነገር ተደርገው ነው የተቆጠሩት። ነገሮችን የመጣል ባሕል! አንድ ወንድ ወይም ሴት እንደ "ትርፍ" መቆጠር ከጀመሩ የነጻነትን መጥፎ የሆነ ፍሬ መቋደስ ከመጀመራቸው ባሻገር በራሳቸው ምክንያት ነፃነታቸውን "አደጋ ላይ ሊጥሉ" በሚችል መልኩ የተጭበረበሩ ናቸው፣ የራሳቸውን፣ የቤተሰባቸውን በተጨማሪም በፍትህ እና በክብር የተሞላ ሕይወታቸውን ለአደጋ ያጋልጣሉ።

የነፃነት ተሞክሮ ላይ አሉታዊ ተፅእኖን የሚያጠላ አንድ ሌላ ነገር አለ፣ ይህም በኃላፊነት የመጠቀም አቅም ሳይገነባ፣ እሴቶችን ባልጠበቀ መልኩ እና ሕሊና ባልተጠናከረበት ሁኔታ በአሁን ወቅት በከፍተኛ እደገት ላይ የሚገኘው የቴክኖሎጂ እድገት ነው፣ ይህ በራሱ በሰው ነጻነት ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እያስከተለ ይገኛል። ስለዚህ እኛ ውስን መሆናችንን እና ገደብ ያለን ሰዎች መሆናችንን በመዘንጋት ከፊት ለፊታችን ያሉትን ተግዳሮቶች እንዳንምለከት ያደርገናል። ለቴክኖሎጂ ከፍተኛ የሆነ ቦታ ከተሰጠው ደግሞ በሰው ልጅ ላይ ተፅዕኖ ሊያስከትል ይችላል።  በተባበሩት መንግሥታ የዓለም የእርሻ እና የምግብ ድርጅት በእንግሊዘኛው ምጻረ ቃል FAO 25ኛውን ጉባሄ ላይ ቅዱስ ጳውሎስ 6ኛ በወቅቱ ባደርጉት ንግግር እንደ ግለጹት  በጣም አስደናቂ የሆነ ሳይንሳዊ እድገቶች፣ በጣም አስገራሚ የቴክኒሎጅ ፈጠራዎች፣ እጅግ በጣም አስደናቂ የሆነ የኢኮኖሚ ዕድገት በትክክለኛ የማህበራዊና የሞራል እድገት ውስጥ ካልተካተቱ የሰው ልጅ ሕልውናን መጻረራቸው አይቀሬ ነው” (እ.አ.አ ሕዳር 16/1970) በማለት ተናግረው እንደ ነበረ ይታወሳል።

የሰውን ልጅ የፍጆታ እቃዎች የመሸመት ባርነት ውስጥ እንዲገባ በማድረግ ሰብዓዊ ሕልውናውን ወደ የፍጆታ እቃ ተጠቃሚነት መቀነስ የሚለው ደግሞ ሶስተኛው አሉታዊውን ተፅእኖ የሚያመልክተው ነው።  እዚህ ጋር ያለው የነጻነት "አደጋ" ደግሞ ቅዤታዊ ነው። በእርግጥ "ይህ ንድፍ ሐሳብ ሁሉም ሰው በነጻነት የፈለገውን የፍጆታ ዕቃ የመጠቀም ነፃነት እንዳላቸው እንዲያምኑ የሚያደርጋቸው ሲሆን ነገር ግን እውነታው ከዚህ በጣም የተለየ ነው፣ በዚህ ረገድ የሸማቹን ነጻነት በበላይነት የያዙት ደግሞ ኢኮኖሚያዊ እና የገንዘብ አቅም ያላቸው በጣም ጥቂት የሚባሉ ሰዎች እንደ ሆኑ የሚያጎላ ነው”። ይህ ደግሞ ነጻነት ሳይሆን ባርነት ነው፣ የዕለት ተዕለት ሥራዎቻቸው ከስራ መባረር፣ አለመተማመን መፍጠር፣ ፍርሃት መፍጠር እና ኪሳራ ሲያጋጥማቸው ድርጅቶቻቸውን መዝጋት የመሳሰሉ ነገሮችን ያስከትላል።

እነዚህ ልዩነቶች ቢኖሩም እንኳን እያንዳንዳችን የግል ነጻነታችንን "አደጋ ላይ የሚጥሉ" ነገሮችን ፈጽሞ እንዲከሰቱ አንፈቅድም። በባርነት እና በብዝበዛ ታሪክ ውስጥ ያለፉ ሰዎች እንኳን ቢሆኑ ይህንን ሁኔታ አይቀበሉም። በዚህ ፌስቲቫል ወቅት ነጻነታቸውን መልሰው የተጎናጸፉ ሰዎች ምስክርነት መስማት ትችላላችሁ፣ ለምሳሌ ዝሙት አዳሪነት፣ ከእገታ ነጻ የወጡ እነዚህን ከመሳሰሉ ሁኔታዎች ነጻ የሆኑ ሰዎችን ምስክርነት ታዳምጡ ይሆናል። እነዚህ ጥንካሬ እና ተስፋን የሚሰጡ በቀጣይነት ነፃነትን የሚያረጋግጡ ምስክርነቶች ናቸው። የእነዚህ ሰዎች ምስክርነት "አዎን" "አደጋ ላይ የነበረውን ነፃነት” መታደግ እንደ ሚቻል የሚያሳዩ ታሪኮች ናቸው።

ምንም እንኳን አንዳንዶች የሚነፍሰውን ማዕበል ተሻግረው ለመሄድ ፍርሃት ያለባቸው ቢሆንም ነገር ግን  ብዙዎች በዕለታዊ ሕይወታቸው፣ የኑሮ ዘይቤዎች፣ ድጋፍ በመስጠት ሰዎችን በመቀበል የአኗኗር ዘይቤያቸው አንዱ አካል አድርገው እየኖሩ ይገኛሉ። እንደ ነፃ ሰው ሆነው ስለሚንቀሳቀሱ በተለያየ ባርነት ውስጥ ላሉ ሰዎች እርዳታ ለመስጠት ትክክለኛ መልስ ናቸው። ተለዋዋጭ ምኞቶችን ያቀዘቅዛሉ፣ አጽናፎችን ይከፍታሉ፣ ጥሩ ጥሩ ነገሮችን ይመኛሉ። ነፃነት በፍጹም ሕልምን አይገድልም፣ ነገር ግን ብዙ ሰዎች ለመከተል የፈለጉትን ነገር ግን ያላገኙትን ፍላጎቶችን በህይወት ውስጥ ይገነባል ። በእርግጥ ነጻነት ፈታኝ የሆነ ነገር ነው፣ ዘላቂ የሆነ ተግዳሮት ቢሆንም ነገር ግን ይማረካል፣ ያሸንፋል፣ ድፍረት ይሰጣል፣ ምኞትን ይፈጥራል፣ ተስፋን ያነሳሳል፣ ወደ በጎ ነገሮች ይመራል፣ መጪውን ጊዜ እንድናምን ያደርገናል። ስለዚህ ከየትኛውም ባርነት የበለጠ ጠንካራ የሆነ ኃይል ይዟል። ዓለማችን ነጻ የሆኑ ሰዎች ያስፈልጓታል!

“የሰው ልጅ ባደገ፣ በጎረመሰ እና ራሱን ወደ ቅድመ-ግንኙነት ለማስገባት ራሱን በምያነጻበት ወቅት፣ ከራሱ በመውጣት ከእግዚኣብሔር፣ ከፍጥረታት እና ከሌሎች ሰዎች ጋር ሕብረት በመፍጠር ለመኖር በሚሞክርበት ወቅት ነጻነት ይሰማዋል። ይህም ከፍጥረት ጀምሮ በቅድስት ሥላሴ ውስጥ ያለውን ሕብረት ያሳየናል። ሁሉም የተሳሰሩ ናቸው። ይህ እኛም ብንሆን ኅበረትን በመፍጠር መኖር እንዳለብን የምያስተምረንን መንፍሳዊነት ማጎልበት እንደ ሚኖርብን ያስተምረናል፣ ከቅድስት ስላሴ የመነጨ ዓለማቀፍ የሆነ ኅብረት እንድንመሰርት ያስተምረናል። ለዚህም ነው ሰብዓዊ ነጻነት በጥልቀት ሊገኝ የሚችለው በጥልቀት በመመርመር እና በልጁ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የተገለጠውን እና የሚደገፈው፣ የፍቅር ነጻነት ሁሉ ምንጭ በሆነ በእግዚኣብሔር አብ ፍቅር እና ምሕረት ታግዘን ነው። በእሱ ርህሩህ እይታ እያንዳንዱ ሰው "ነፃነት ከሚፈጥረው አደጋ" ነጻ ሆኖ መንገዱን ሁሌም መቀጠል ይችላል።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ ነጻ ሕዝብ እንድትሆኑ እና ራሳችሁን ለሌልች አሳልፋችሁ መስጠትን ሳትፈሩ፣ መልካም ነገር ለምሥራት እጆቻችንሁን እንድታቆሽሹ እና የተቸገሩትን ለመርዳት እጆቻችሁን መዘርጋት እንዳትዘነጉ።

ለእናንተ ያለኝን አጋርነት እና ከእናንተ ጋር በጸሎት መሆኔን ላረጋግጥላችሁ ወዳለሁ። ከልብ የመነጨ ሐዋርያዊ ቡራኬ ይድረሳችሁ! እባካችሁን ለእነ መጸለይ እንዳትዘነጉ። አመስግናለሁ።

 

 

23 November 2018, 14:53