ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ  ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ጣዖት እግዚብ/ር በልባችን ውስጠ የተከለውን ምልኣት ያለው ፍቅር ይነቅላል”

አዲሱ ህግ በክርስቶስ ውስጥ እና በመንፈስ ቅዱስ ፍላጎት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዘወትር ረቡዕ ዕለት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ወይም እንዳስፈላጊነቱ እና እንደ አየሩ ጸባይ በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን፣ መንፈሳዊ ነጋዲያን እና የሀገር ጎቢኚዎች ሳምንታዊ የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ሚያደርጉ የሚታወቅ ሲሆን በዚህ መረሀ ግብር መሰረት ከሳምንታት በፊት በዐስርቱ ትእዛዛት ዙርያ ጀምረውት የነበረው ተከታታይ የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ማብቂያ እንደ ነበረ ለመረዳት ተችሉዋል። በዛሬው ዕለት ማለትም በሕዳር 19/2011 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ ያደረጉት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ክርስቶስ የሰጠን አዲሱ ሕግ እና የመንፈስ ቅዱስ ፍላጎት በሚል አርእስት የቀረበ የጠቅላላ አስተምህሮ እንደ ነበረ ለቫቲካን ዜን ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን “ጣዖት እግዚብ/ር በልባችን ውስጠ የተከለውን ምልኣት ያለው ፍቅር ይነቅላል” ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

በእለቱ የተነበበው የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ

ነገር ግን እላለሁ፥ በመንፈስ ተመላለሱ፥ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ። ሥጋ በመንፈስ ላይ መንፈስም በሥጋ ላይ ይመኛልና፥ እነዚህም እርስ በርሳቸው ይቀዋወማሉ፤ ስለዚህም የምትወዱትን ልታደርጉ አትችሉም። በመንፈስ ብትመሩ ግን ከሕግ በታች አይደላችሁም። የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።  እንደዚህ ያሉትን የሚከለክል ሕግ የለም (ገላቲያ 5፡16-18,22-23)። 

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዛሬው እለት ማለትም በሕዳር 19/2011 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ ለተሰበሰቡ ምዕመናን ያደርጉትን የጠቅላላ አስተምህሮ ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው እናቀርብላችኋለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደ ምን አረፈዳችሁ

በዛሬው (ሕዳር 19/2011 ዓ,ም) የጠቅላላው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በዐስሩ ትእዛዛት ዙሪያ ከዚህ ቀደም ጀምረነው የነበረውን አስተምህሮ በማጠቀጠል የሕይወትን ጉዞ በመፈተሽ እና ዐስርቱን ትእዛዛት በማንበባችን የተነሳ የተወሰዱትን እርምጃዎች በአጠቃላይ በክርስቶስ የመገለጥ ብርሃን ውስጥ በማስገባት ለመመለስ የሚያስችለን ቁልፍ የሆኑ ፍላጎቶቻች ጭብጥ ዙሪያ የሚያጠነጥን ነው።

ለእርሱ በምንሰጠው ምስጋና ላይ ሥር መሰረታችንን በማድረግ ግንኙነታችንን በእርሱ በመታመን እና ለእርሱ ታዛዢ መሆናችንን በመግለጽ ጀምረን እንዳየነው እግዚኣብሔር ለእኛ ብዙ ብዙ ነገሮችን በቅድሚያ ሳይሰጠን ከእኛ ብዙ ነገሮችን አይጠይቅም። በእኛ ላይ ከፍተኛ ኃይል ካላቸው የጣዖት አምልኮዎች ሸሽተን ራሳችንን እንድናድን ይጋብዘናል። እንዲያውም በዚህ ዓለም ጣዖታት ውስጥ የራሳችንን እርካታ መፈለግ ባዶ እንድንሆን እና በባርነት ቀንበር ውስጥ ገብተን እንድንኖር ያደርገናል፣ ነገር ግን እኛን ከፍ የሚያደርገን በቀጣይነት እንድንኖር የሚረዳን ከእርሱ ከአባትነት መንፍስ በሚመነጨው ግንኙነት እኛን ልጆቹ በሚያደርገን ክርስቶስ ከእርሱ ጋር የሚኖረን ግንኙነት ነው። ይህም የሚያመለክተው የመባረክ እና የነፃነት ሂደትን ነው የሚያመለክተው፣ ይህም እውነተኛ እረፍት ነው። “ያለ እርሱ የሚያድነኝ የለም፣ መከላከያዬም እርሱ ስለሆነ ክቶ አልናወጥም” (መዝ 62፡2)።

ይህ ነጻ የሆነ ሕይወታችን ግላዊ የሆነ ታሪካችንን እንድንቀበል እና ከሕጻንነት እስከ ዛሬ ቀን ድረስ አዋቂዎች የሚያደርገን እና ለህይወታችን እውነታዎች ጣዕም የሆነውን እና በሕይወታችን ውስጥ ላጋጠሙን ብዙ ሰዎች ትክክለኛውን ክብደት የመስጠት ችሎታ ያለው ነው። በዚህ መንገድ ላይ በመጓዝ እግዚአብሔር ለልጁ ክርስቶስ ኢየሱስ ያሳየውን ፍቅር እንደ መነሻ በመጠቀም ከጎረቤቶቻችን ጋር ያለንን ግንኙነት እንገነባለን፣ ይህም  የታማኝነት፣ የለጋስነትና እውነተኛ እና የተደረገል ውብ የሆነ ትክክለኛ ጥሪ ነው።

ነገር ግን እንደዚህ ለመኖር በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ አዲስ ልብ ያስፈልገናል። ይህንን "ልባችንን በአዲስ ልብ መቀየር ይምንችለው እንዴት ነው? በእግዚአብሔር የደህንነት ምስጢር ውስጥ በተዘረዘሩ አዳዲስ ምኞቶች (ሮሜ 8 6)፣ በተለይም ደግሞ ዐስርቱን ትእዛዛት ከግምት ባስገባ መልኩ ኢየሱስ በተራራ ላይ በሰበከው ስብከት በሰጠው የማጠቃለያ ሐስብ ላይ ተመርኩዘን ነው።

በእርግጥ በዐስርቱ ትእዛዛት ውስጥ የተገለጸውን ሕይወት አመስጋኝ፣ ነጻ፣ እውነተኛ፣ በበረከት የተሞላ፣ የጎለመሰ ሕይወት፣ ተንከባካቢ እና ህይወት ያለው፣ ታማኝ፣ ለጋስና ልባዊ፣ የሆነ ድንቅ ሕይወት እኛ ይህንን ሳንገነዘብ ራሳችንን በክርስቶስ ፊት እናገኛለን። ዐስርቱ ትእዛዛት ልክ እንደ “ኤክስሬ” ማሽን ናቸው የእርሱን ፊት ቁልጭ አድርገን እንድናይ የሚረዱን መሳሪያዎች ናቸው። በዚሁ መልክ መንፈስ ቅዱስ የልቦና ስጦታዎች በመስጠት የመንፈስ ፍላጎት መሻቶች ውስጥ እንድንገባ በማድረግ ልባችንን ያዳብረዋል።

ክርስቶስን ስንመለከት ውበት፣ መልካምነት እና እውነት እናያለን። እናም መንፈስ ቅዱስ እነዚህን ምኞቶች በመከተል ተስፋን፣ እምነትንና ፍቅርን በውስጣችን ያስጀምራል። ስለዚህ በዚህ መልኩ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “እኔ የመጣሁት ሕግን ለመሻር ሳይሆን ሕግን ለመፈጸም ነው” ብሎ የተናገረበትን ምክንያት በሚገባ ለመረዳት እንችላለን፣ ሕግን ሥጋዊ በሆነ አግባባ የምንመለከተው ከሆነ በጣም ብዙ የሆኑ ዝርዝሮች የተካተቱበት እና የተለያዩ ነገሮች እንዲፈጸሙ ወይም እንዳይፈጸሙ የሚከለክል ሲሆን ነገር ግን ይህንን በመንፈስ ቅዱስ እይታ ስንምለከተው ደግሞ ይህ ሕግ የሕይወት ምንጭ ሲሆን እናያለን፣ ምክንያቱም በዚህ ረገድ ሕግ እንዲያው ዝም ብሎ እንደ አንድ ሥጋዊ የሆነ ደንብ የሚቆጠር ነገር ሳይሆን ነገር ግን ያ ሥጋ የሚወደን፣ የሚፈልገን፣ ይቅር የሚለን፣ የሚያጽናናን፣ በኃጢያት ምክንያት ጠፍቶ የነበረውን የሰው ልጅ በእርሱ አካል አማካይነት ከአባቱ ጋር ኅብረት እንድንፈጥር የሚያደርገን የእርሱ የክርስቶስ ሥጋ ይሆናል ማለት ነው።

ዐስርቱ ትእዛዛት ለሰው ልጆች ፍርድ ሳይሆን ነገር ግን ለሰው ልጆች እውነተኛ የሆነ ሕይወት መስጠት የሚችሉት እና በፍቅር፣ በሰላም፣ በደስታ፣ ማራኪ የሆነ ሕይወት ለመኖር፣ በቸርነት፣ በጎነት፣ በእምነት፣ በየዋሕነት፣ ራስን በመግዛት ለመኖር ያለንን ምኞት እውን የሚሆነው በክርስቶስ እና በእርሱ አማካይነት ብቻ እንደ ሆነ ይገልጻሉ።

ክርስቶስን በዐስርቱ ትእዛዛት ውስት መፈለግ ጠቀሜታው ምንድነው፣ ልባችን በፍቅር የተሞላ እንዲሆን እና ልባችን ለእግዚኣብሔር ተግባራት እንዲከፈት፣ ልባችንን እንድናሰፋ ይረዳናል። አንድ ሰው ከክርስቶስ ጋር ለመኖር ፍላጎት ሲያሳይ በራሱ ኃይል ልያገኘው የማይችለውን፣ ነገር ግን መሐሪ እና ለጋስ የሆነው እግዚኣብሔር ወደ ደህንነት የሚወስደውን መንገድ ይከፈትለታል። ሰውን ወደ ክፋት የሚመራው ክፉ ምኞት ከሆነ (ማቴ 15 18-20)፣ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ በልባችን ውስጥ የእርሱን የቅድመ-መለኮታዊ ፍላጎቶች በልባችን ውስጥ ያስቀምጣል። በእርግጥ አዲስ ሕይወት ከአንድ ደንብ ርዕሰ-ጉዳዩ ጋር ተጣጥሞ ለመሄድ የሚደረግ ጥረት ማለት አይደለም፣ ነገር ግን የእግዚኣብሔር መንፈስ ራሱ ፍሬያማ ወደ ሆነ መንገድ እኛን በመምራት በመወደዳችን በመደሰት እና እኛም እርሱን ለመውደድ በምናደርገው ጥረት ምክንያት ደስተኛ የሆነ ሕይወት ለመኖር እንችል ዘንድ ይረዳናል።

ለእኛ ለክርስቲያኖች ዐስርቱ ትእዛዛት ማለት የእርሱን ልብ እንዲሰጠን ክርስቶስን ማሰላሰል፣ እርሱን መመኘት፣ የእርሱን መንፈስ ቅዱስ ለመቀበል በመሻት ማሰላሰል ማለት ነው።

28 November 2018, 16:02