ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “እኛ ከዚህ ቀደም ከተካሄዱት አስቃቂ ጦርነቶች መማር አልቻልንም”

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስ ከመልኣከ እግዚኣብሔር ጸሎት በኋላ ያስተላለፉት መልእክት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በትላንትናው እለት ማለትም በሕዳር 02/2011 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን በእለቱ በተነበበው ቅዱስ ወንጌል ላይ ተመርኩዘው አስተንትኖ ካደርጉ በኋላ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ክብር በመስጠት ከሚደገሙ ጸሎቶች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀሰውን “የእግዚኣብሔር መልኣክ ማርያምን አበሰራት” የሚለውን የብስራተ ገብሬል ጸሎት ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከደገሙ በኋላ እንደ ተለመደው ለዓለም ባስተላለፉት መልእክት እንደ ገለጹት በዕለቱ የመጀመርያው የዓለም ጦርነት የተጠናቀቀበት 100ኛ አመት እየተዘከረ መሆኑን ገልጸው ይህ የመጀመርያው የዓለም ጦርነት እንደ ማንኛው አሁን በመካሄድ ላይ ያሉ ጦርነቶች ጠቃሚ የሆን ጦርነት እንዳልነበረ ገልጸዋል።

የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ታሪካዊ ገጽታ ሁሉም የሰው ልጆች የጦርነትን ባህል እንዲያስወግዱ  እና በአሁኑ ወቅት በብዙ የዓለማችን ክፍሎች እየተከሰቱ የሚገኙ ግጭቶችን ለማስቆም ህጋዊ የሆኑ መፍትሄዎችን እንዲፈጉ የሚያስጠነቅቅ እና የሚያስታውስ ክስተት ነው ያሉት ቅዱስነታቸው እኛ ግን ከእዚያ አስቃቂ ክስተት የተማርነው ነገር ያለ አይመስለኝም ብለዋል። በእዚያ አሰቃቂ እና አሳዛኝ የሆነ ጦርነት ሰለባ የሆኑትን ሰዎች በሙሉ በጸሎታችን በማስታወስ በመላው ዓለም ሰላም ይረጋገጥ ዘንድ ለጦርነት ሳይሆን ለሰላም በሙሉ ኃይላችን መሥራት ይኖርብናል ብለዋል።

በሚቀጥለው እሁድ ሁለተኛው ዓለማቀፍ የድኾች ቀን እንደ ሚከበር የገለጹት ቅዱስነታቸው ይህንን ክብረ በዓል በቅዱስ ወንጌል፣ በጸሎት እና በለጋስነት መንፈስ ታግዘን ልናከብር ይገባል ብለዋል። በወቅቱ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተገኙ ሰዎች ቅዱስነታቸው ሰላምታ ማቅረባቸው የታወቀ ሲሆን እንደ ተለመደው “እባካችሁን ለእኔ መጸለይ አንዳትረሱ”  ካሉ በኋላ ሐዋርያዊ ቡራኬያቸውን ሰጥተው መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
12 November 2018, 15:36