ፈልግ

ዓለማቀፍ የሰላም ቀን ዓለማቀፍ የሰላም ቀን  

መልካም ፖለቲካ ለሰላም

“መልካም ፖሌቲካ ለሰላም” በሚል አርእስት እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር 2019 ዓ.ም መጀመርያ ላይ ለሚከበረው ዓለማቀፍ የሰላም ቀን አስተንትኖ የሚረዳ መጽሐፍ ይፋ መሆኑ ተገለጸ።

እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በመጪው ጥር 1/2019 ዓ.ም (የፈረንጆቹ አዲስ አመት ሲከበር ማለት ነው) የሚከበረውን ዓለማቀፍ የሰላም ቀን ጽንሰ ሐሳብ በተመለከተ ስለዚህ ጉዳይ በስፊው የሚተነትን እና ማብራርያ የታከለበት መጽሐፍ በጥቅምት 27/2011 ዓ.ም ይፋ መሆኑ ተገለጸ።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

እያንዳንዱ ዜጋ ፖሌቲካዊ ኃላፊነት አለው

“የፖለቲካ ኃላፊነት ለሁሉም ዜጎች፣ በተለይም ደግሞ ለመጠበቅ እና ለመምራት ስልጣን ለተሰጣቸው ሰዎች ትክሻ ላይ እንደ ሆነ” የሚያመልክተው መጽሐፉ በመጪው የአውሮፓዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የዓለማችን ማኅበረሰቦች ዘንድ የሚከበረውን 2019 ዓ.ም አዲስ አመት መባቻ ላይ ለሚከበረው ዓለማቀፍ የሰላም ቀን ይሆን ዘንድ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የተመረጠው መሪ ቃል “መልካም ፖለቲካ ለሰላም” የሚለው እንደ ሆነ ለመረዳት ትችሉዋል።

ሰላም ያለመተማመን ሊረጋገጥ አይችልም

“የዚህ መጽሐፍ ተልዕኮ ሕገ-ወጥነትን በማስወገድ፣ የሰዎችን ሰብዓዊ መብቶች በማረጋገጥ እና በማኅበረሰቡ ውስጥ የተለያየ ሚና የሚጫወቱ አካለት መካከል ውይይት እንዲደረግ በማድረግ በአዲሱ ትውልድ እና በባሕል መካከል ያለውን ልዩነት በውይይት በመፍታት ሰላምን ማረጋገጥ” የሚል ተልዕኮ ያነገበ መጽሐፍ እንደ ሆነ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በአንድ ማኅበርሰብ ውስጥ እርስ በእርስ የመተማመን መንፈስ የሌለ እንደ ሆነ ሰላምን ማረጋገጥ እጅግ ከባድ እንደ ሆነ በሰፊው የሚያትት መጽሐፍ ነው። የከፍተኛ ፍቅር መግለጫ እና የልግስና ልምዶች አንዱ አካል የሆነው የፖለቲካዊ ቁርኝነት ለሕይወት እና ለዓለማችን እንዲሁም በጣም ወጣት እና ተጋላጭ ለሆኑ ዜጎች የወደፊቱ ፍላጎቶቻቸውን በሚገባ ለሟሟለት ከፍተኛ የሆነ ጥረት ማድረግን የሚጠይቅ እንደ ሆነ፣ በዚህም የተነሳ ማነኛውም ዜጋ ሰላምን ለማረጋገጥ ይቻል ዘንድ በፖሌቲካዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ በንቃት መካፈል ይኖርበታል የሚል እንድምታ ያዘለ መጽሐፍ እንደ ሆነ ለመረዳት ተችሉዋል።

07 November 2018, 15:38