ፈልግ

2018.10.10 Udienza Generale 2018.10.10 Udienza Generale 

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ “በጥቅምት ወር በመቁጠሪያ ጸሎት እና በተልዕኮ ላይ ትኩረት ይደረግ”።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ አባ ግርማቸው ተስፋዬ - ቫቲካን

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ዛሬ ዕለተ ረቡዕ መስከረም 30 ቀን 2011 ዓ.ም. በቅዱስ ጴጥሮስ ኣደባባይ የሰጡት ኣጠቃላይ የትምህርተ ክርስቶስ ኣስተምህሮ ካበቃ በኋላ በኣደባባዩ ለተገኘው ለጣሊያንኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ነጋዲያን የፍራንቺስካውያን ገዳማዉያን ታናናሽ ወንድሞችን የፍራንቺስካውያን ያለ ኣዳም ኃጢአት የተፀነስሽ ድንግል ማርያም ደናግል እህቶችን የረዳኢተ ማርያም ደናግል እህቶችን ከተለያዩ ቦታዎች የተሰበሰቡትን ተማሪዎች ኣስተማሪዎች እንዲሁም ምዕመናንና ምዕመናት ከፓቲ እና ኦስትራ ቬቴሬ የመጡትን የኦሊቪኮልቶሪ ብሔራዊ ማኅበር ኣባላትን የቼርቪያ ማዘጋጃ ቤት ተወካዮችን ከቪቴርቦ የመጡትን የነጋዴዎች ማኅበር ተወካዮችን የኣቪስ ማኅበር ኣባላትን የቤሌግራን የጣሊያን ቀይ መስቀል ማኅበር ኣባላትን ሁሉ የከበረ ሰላምታቸውን ከሰጡ በኋላ ለወጣቶች ለአረጋውያን ለሕሙማንና ለኣዲስ ተጋቢዎች ሁሉ ኣንድ መልዕክት ኣስተላልፈዋል።

በዚህ በጥቅምት ወር ሙሉ በመቁጠሪያ እና በተልዕኮ ላይ ልዩ ትኩረትና ጸሎት እንዲደረግ ኣውጄኣለሁ። እኔም መቁጠሪያዬን ደግማለሁ ስለ ቤትክርስቲያን ቅድስናና ሰለ እናንተም ሓሳብ ጸልያለሁ ሓሳባችሁንም በእመቤታችን ቅድስት ማርያም ፊት ኣደርሳለሁ ይህም እያንዳንዱ ሰው ወደ ሌላው ክርስቶስን በመዉሰድ የዓለምን መንገድ በሚገባ ለመጓዝ እንዲችል ኃይልን ብርታትን እንድናገኝ ይረዳናል ብለው የዕለቱ ዝግጅት ተጠናቋል።

10 October 2018, 18:04