ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከበሽተኞች ጋር ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከበሽተኞች ጋር  

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ፡ ጤና እንደ ሸቀጥ የምንሸምተው ነገር ሳይሆን ዓለማቀፍዊ ይዘት ያለው መብት ነ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቅርቡ በካዛኪስታን በመካሄድ ላይ በነበረው ዓለማቀፍ የጤና አጠባበቅ ኮንፈረንስ ተሳታፊዎች በጹሑፍ ባስተላለፉት መልእክት እንደ ገለጹት የጤና አጠባበቅ ተቋማት ለሁሉም የሰው ልጆች ተደረሻ ይሆኑ ዘንድ የሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት በሙሉ ኃይላቸው እንዲረባረቡ ጥሪ ማቀረባቸውን ለቫትካን ዜና ከደርሰው ዘገባ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን “ጤና እንደ ሸቀጥ በየመደብሩ የሚሸመት ነገር ሳይሆን እያንዳንዱ ሰው ልያገኘው የሚገባው ዓለማቀፍ ይዘት ያለው መብት ነው ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ቅዱስነታቸው ይህንን በተመለከተ በትላንትናው እለት ከ41 ሚልዮን በላይ ተከታዮች ባሉት atPontifex በተሰኘው የትዊተር ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት የጹሑፍ መልእክት እንደ ገለጹት ጤና እንደ ቁሳቁስ የሚሸመት ነገር ሳይሆን ነገር ግን ጤና ዓለማቀፍ ይዘት ያለው መብት ነው፣ ሁላችንም ኃይላችንን አስተባብረን የጤና መስጫ ተቋምት ለሁሉ ተደራሽ ይሆኑ ዘንድ መስርታ ይኖርብናል” ማለታቸውን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ቅዱስነታቸው ይህንን መልእክት ያስተላለፉት ከጥቅምት 15-16/2011 ዓ.ም “የመጀመርያ ደረጃ የጤና ክብካቤ መስጫ ተቋም” በሚል መሪ ቃል በካዛኪስታን ዋና ከተማ በስታና በመካሄድ ባለው የዓለማቀፍ የሕጻናት መርጃ ድርጅት በምጻረ ቃሉ UNICEF ባዘጋጀው የሁለት ቀን ኮንፈረንስ ላይ ለነበሩ ተካፋዮች እንደ ነበረ ለመረዳት ተችሉዋል።

በጤና እንክብካቤ መስክ ያለው የንግድ ፉክክር ሰዎችን ሊጎዳ ይችላል

“በአሁኑ ወቅት በቀዳሚነት የምርት ብክነት ከሚታይባቸው የንግድ ዘርፎች መካከል በቀዳሚነት የሚቀመጠው የጤና ክብካቤ ዘርፍ ነው” ይህም በጣም አሳሳቢ እና አሳዛኝ ደረጃ ላይ የደረሰ ጉዳይ ነው በማለት መልእክታቸውን የጀመሩት ቅዱስነታቸው ይህንን ተመሳሳይ ቃል እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በየካቲት 10/2017 ዓ.ም ከጣሊያን የካቶሊክ ብጹዕን ጳጳሳት ጉባሄ ላይ ቅዱስነታቸው ተመሳሳይ የሆነ ምልእክት ማስተላለፋቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

“አንድ የታመመ ሰው ከእነ ሙሉ ክብሩ እንክብካቤ ካልተሰጠው እና የትኩረት ማዕከል ካልሆነ የሌሎች ሰዎችን መጥፎነት ለመገምገም ሊነሳሳ ይችላል። ይህ ደግሞ በጣም ከባድ የሆነ ነገር ነው! ለዚህ ጉዳይ ከፍተኛ የሆነ ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል፣ በተለይም ደግሞ የታመመው ሰው የእድሜ ባለጸጋ ከሆነ እና በጣም በከፋ ሁኔታ የታመመ ከሆነ፣ በማይድን በሽታ የተጠቃ ከሆነ፣ እነርሱን ማከም በጣም ከባድ ሊሆን ይችላል” ብለዋል። ነገር ግን የሰው ልጆች በመሆናቸው የተነሳ ለሰው ልጅ የሚሰጠው ሰብዐዊ ክብር በፍጹም ሊነፈጋቸው እንደ ማይገባ ቅዱስነታቸው ቀደም ሲል ባስተላለፉት መልእክት መግለጻቸው የሚታወስ ሲሆን በቀዳሚነት ሊቀመጥ የሚገባው ጉዳይ የጤና ክብካቤን እንደ ማንኛው የንግድ ዘርፍ አድርጎ መቁጠር ሳይሆን የሰው ልጆች በቀላሉ ሊያገኙት የሚገባው ዓለማቀፍ ይዘት ያለው ሰብዐዊ መብት ነው ብለዋል።

የሕይወት መብት መከበር ማለት ለጤና መብት ጥበቃ ማድረግ ማለት ነው

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከዚህ ቀደም እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በጥር 8/20118 ዓ.ም ከዓለማቀፍ የዲምሎማትክ አካላት ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት “የሕይወት መብት ማስከበር እና አካልን መንከባከብ ማለት የሰው ልጆችን ሁሉ ለጤና ክብካቤ መስጫ ተቋምት ተደራሽ ማድረግ ማለት ነው፣ ይህም ዓለማቀፍ ይዘት ያለው የሰዎች ዓለማቀፍ የሰብዐዊ መብት ድንጋጌ አንዱ አካል ነው” ማለታቸው የሚታወስ ሲሆን ይህም እያንዳንዱ ሰው በጤና ተቋማት አማካይነት ተገቢውን እንክብካቤ የመግኘት መብት እንዳለው ያሳያል ማለታቸው ይታወሳል።

ይህ ዓለማቀፍ የሰው ልጆች የሰብዐዊ መብት ድንጋጌ የዛሬ 40 አመት ገደማ መደንገጉን ያወሱት ቅዱስነታቸው ከ40 አመታት በኋላ እንኳን ይህንን ድንጋጌ በተግባር በማዋል የጤና ክብካቤ መስጫ ተቋማትን ለሁሉም የዓለማችን ሕዝቦች ተደራሽ ማድረግ እንዳልተቻለ ገልጸው ዛሬ (ጥቅምት 16/2011 ዓ.ም) በካዛኪስታን ዋና ከተማ በመካሄድ ላይ የነበረው ዓለማቀፍ ኮንፈረንስ ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት ኃይላቸውን አሟጠው በመጠቀም በዓለማቀፍ ደረጃ የጤና ክብካቤ መስጫ ተቋሟት ለሁሉም የሰው ልጆች ተደራሽ ይሆኑ ዘንድ መሥራት እንደ ሚጠበቅባቸው የሚያሳብ ጉዳይ እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።

26 October 2018, 16:13