ፈልግ

Pope Francis' General Audience Pope Francis' General Audience 

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ “ሲመቸን ብቻ ማፍቀር ተገቢ አይደለም”!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ዘወትር ረቡዕ ረፋዱ ላይ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎቢዎች በተለያዩ አርእስቶች ላይ ተንተርሰው የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። በዚህ መረሃ ግብር መሰረት በዛሬው እለት ማለትም በጥቅምት 14/2011 ዓ.ም በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች ቅዱስነታቸው ያደረጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ከዚህ ቀደም በዐስርቱ ትዕዛዛት ዙሪያ በተከታታይ ያደርጉት የነበረው የትምህርት ክርስቶስ አስተምህሮ ቀጣይ ክፍል እንደ ነበረ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን “አታመንዝር” በሚለው 6ኛው ትዕዛዝ ዙሪያ ላይ እንደ ነበረ ከስፍራው ለቫቲካን ዜና ከደርሰው ዜና ለመረዳት የተቻለ ሲሆን “ሲመቸን ብቻ ማፍቀር ተገቢ የሆነ ባሕርይ አይደልም”  ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዛሬው እለት ማለትም በጥቅምት 14/2011 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በስድስተኛው እና “አታመዝር” በሚለው ትዕዛዝ ላያ ተመርኩዘው ያደርጉትን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉ ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደ ምን አረፈዳችሁ!

ከዚህ ቀደም በዐስርቱ ትዕዛዛት ዙሪያ የጀመርነውን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በመቀጠል ዛሬ ደግሞ ስሜትን እና ጾታዊ ጉዳዮችን በሚመለከተው እና “አታመዝር” በሚለው በስድስተኛ ትዕዛዝ ላይ እናተኩራለን።

ይህ ትዕዛዝ የሚያቀርብልን ፈጣን የሆነ ጥሪ “ታማኝነት” የሚለውን ቃል የሚያሰማ ሲሆን በእርግጥ የትኛውም ዓይነት ሰብዓዊ ግንኙነት ተአማኒነት የጎደለው ከሆነ እውነተኛ የሆነ ነገር ሊሆን አይችልም።

አንድ ሰው "ሲመቸው" ብቻ መውደድ የለበትም፣ ፍቅር ሁሉንም ነገር ያለገደብ በሚሰጥበት ጊዜ የራሱን ጥቅም ከማጣት አልፎ ይገለጻል። የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ እንደ ምያረጋግጠው “ፍቅር ተጨባጭ መሆንን ይፈልጋል” (ቁ. 1646) ይለናል። ታማኝነት ማለት ነጻ፣ የበሰለ እና ኃላፊነት የሚሰማው የሰው ልጅ ግንኙነት ባህሪ ማለት ነው። አንድ ጓደኛ እንኳን እራሱ እውነተኛ መሆኑን ማረጋገጥ ይኖርበታል፣ እውነተኛነቱን ካላረጋገጠ ግን በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ጥሩ ጓደኛ ሆነ መቀጠል አይችልም። ክርስቶስ አብ ለወልድ ያለውን ጥልቅ እና እውነተኛ ፍቅር ገልጾልናል፣ በዚህ ኃይል የተነሳ እርሱ እኛ ምንም እንኳን ስህተቶችን የምንሠራ ቢሆንም እርሱ የእኛ ታማኝ ጓደኛ በመሆን መልካምነታችንን በመመኘት ምንም እንኳን የተገባን ባንሆንም እርሱ ደስ የሚያሰኝ ወዳጃችን ሆኖ ይቀጥላል።

ሰብዓዊ ፍጡራን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ሊወደዱ የገባል፣ ይህንን በተግባር የማይገልጽ እና ሌሎችን የማይቀበል ሰው ምልዐት ይጎለዋል፣ ብዙ ጊዜ ይህንን የምናደርገው ባለማወቅ ነው። የሰዎች ልብ ይህንን የጎደለውን ፍቅር በሌሎች ትርኢቶች ማለትም በግጭቶች እና ሚዛናዊነት በጎደለው መልኩ ለመሙላት በመፈለግ ፍቅር ግልጽ ያልሆነ ጣዕም እንዲኖረው ያደርጋሉ። አደጋው “ፍቅርን” ያልተለመዱ ዓይነት ግንኙነቶችን እና በሳል ያልሆኑ ግንኙነቶችን በመመስረት የሕይወት ብርሃንን ማግኘት አለመቻላቸው ነው።

ስለዚህም ለምሳሌ ያህል አካላዊ ለሆነ መስዕብ  በጣም ከፍተኛ የሆነ ቦታ እንሰጣለን፣ ይህ በራሱ ከእግዚአብሔር የተሰጠ ስጦታ ቢሆንም፣ ነገር ግን ከእውነተኛው ሰው ጋር እውነተኛ እና ታማኝ የግንኙነት መንገድ ማዘጋጀት ግን አስፈላጊ ነው። ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ሁለተኛ ሰብዓዊ ፍጡር "የተጠራው ሙሉ እና የጎለበተ ግንኙነት እንዲመሰርት ነው" ይህም "አንድ ልብ ቀስ በቀስ በማስተዋል ጥበብ ላይ የተመሰረተ ከልብ የመነጨ የውሳኔ ፍሬ ውጤት ነው” ይሉ ነበር። እያንዳንዱ ሰብዓዊ ፍጡር "በንፅህና እና በስነ-ጽንአት የአካል ትርጉም ምን መሆኑን ሲማር እና ሲያውቅ ቢቻ የሚከሰት ተግባር ነው።

ወደ ጋብቻ ሕይወት የሚደረገው የግንኙነት ጥሪ ግንኙነቱ ጥራት ያለው እንዲሆን እና ለማግባት የተደረገው ጥሪ ግንኙነቱ ጥራት እና የተሳትፎ ጊዜ ለማረጋገጥ በጥንቃቄ መሻትን ይጠይቃል። እጮኛሞች ምስጢረ ተክሊል ከመፈጸማቸው በፊት በእነሩስ ግንኙነት ውስጥ የእግዚኣብሔር እጅ መኖሩን በብስለት ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፣ ይህም በሕይወት ጉዞዋቸው ከእነርሱ ጋር በመሆን “በክርስቶስ ጸጋ ታግዤ ለዘለዓለም ታማኝ ሆኜ ለመኖር ቃል እገባለው” ብለው በድፍረት እንዲናገሩ ይረዳቸዋል። "በሐዘንና በደስታ፣ በጤና እና በህመም" ታማኝነታቸውን ቃል በቃል ሊጠብቁ አይችሉም፣ እንዲሁም በመልካም ፍልጎት እና በተስፋ ላይ ብቻ ተመስረተው በሕይወታቸው ዘመን ውስጥ በእየቀኑ እርስ በእርሳቸው ለመዋደድ እና ለመከባበር ቢፈልጉም፣ ነገር ግን ተግባራዊ ለማድረግ አይችሉም። ሕይወታቸውን በእግዚኣብሔር ታማኝ ፍቅር ጽኑ መሰረት ላይ መገንባት ይኖርባቸዋል። በዚህም ምክንያት ምስጢረ ተክልሊ ከመፈጸማቸው በፊት ጥልቅ የሆነ ቅድመ ዝግጅት ያስፈልጋል፣ ጥልቅ የሆነ የትምህረት ክርስቶስ አስተምህሮ ያስፈልጋል፣ ምክንያቱ በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ በፍቅር ላይ መጫወት የለባቸውም፣ በፍቅር መጫወት በፍጹም አይገባም። ምስጢረ ተክሊልን ለመፈጸም በቁምስና ውስጥ ሦስት ወይም አራት ቀናት ብቻ ትምህርቶችን ማዘጋጀት ባራሱ በቂ መስሎ አይሰማኝም፣ በፍጹም! ይህ በቂ የሆነ የዝግጅት ጊዜ ነው ብዬ አላምንም። በዚህ ሰበብ ለሚፈጹሙ በደሎች ኃላፊነት የሚወድቀው ይህ ጉዳይ በቀጥታ በሚመለከተው ሰው ላይ ነው፣ ይህም ማለት ኃላፊነቱን የሚወስደው ቆመሱ እና ይህ ነገር እንዲከሰት ፈቃድ በሚሰጠው ጳጳሱ ላይ ነው። ለምስጢረ ተክሊል የሚደረግ ዝግጅት በብስለት የሚደረግ እና በቂ ጊዜ ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ ነው። ለምስጢረ ተክሊል የሚደረግ ዝግጅት እንዲሁ ለይስሙላ የሚደረግ ዝግጅት ሊሆን በፍጹም አይገባውም፣ የቤተ ክርስቲያን አንዱ ምስጢር እንደ ሆነ በሚገባ ማወቅ ያስፈልጋል። በዚህም የተነሳ በእውነተኛ መንፈስ ሊሰጥ የሚገባው ትምህረተ ክርስቶስ ሊሆን ይገባዋል።

ታማኝነት ማለት ተጨባጭ የሕይወት መንገድ ማለት ነው። በታማኝነት መሥራት፣ ከልብ በመነጨ መልኩ መናገር፣ ለእራሱ በእራሱ አስተሳሰቦች እና ድርጊቶች ታማኝ ሆኖ መኖር ማለት ነው። የታማኝነት ሕይወት በተገቢው መልኩ በሁሉም መልኩ ሊገለፅ ይችላል፣ ይህም በሁሉም ሁኔታዎች ውስጥ ታማኝ እና እምነት ያላቸው ወንዶችና ሴቶች እንዲፈጠሩ ያስችላል ማለት ነው።

ነገር ግን እንደዚህ ዓይነት ውብ የሆነ ኑሮ ላይ ለመድረስ የሰው ተፈጥሮአዊ ባሕሪ በራሱ ብቻ በቂ አይደለም፣ የእግዚአብሄር ፍፁም የሆነ ታማኝነት በእኛ ሕልውና ውስጥ መግባት ይኖርበታል፣ እኛን ሊያረካን ይገባል። ይህ ስድስተኛው ትዕዛዝ እኛ ክርስቶስን እንድንመለከት ይረዳናል፣ እሱም በታማኝነት የእኛን አመንዝራ የሆነ ልብ ሊወስድና ታማኝ የሆነ ልብ ሊሰጠን ይችላል። ፍጹም የሆነ ፍቅር የሚገኘው በእርሱ እና በእሱ ውስጥ ብቻ ነው፣ ሙሉ የሆነ ስጦታ እና ጥልቅ የሆነ አቀባበል እስከ መጨረሻ የሚያደርግልን እርሱ ብቻ ነው።

ከእርሱ ሞት እና ትንሳሄ ውስጥ ለእኛ ያለው ታማኝነት ይመነጫል፣ ያለ ቅድመ ሁኔታ ከሚሰጥን ፍቅር ውስጥ ደግሞ ከእርሱ ጋር ያለን ቀጣይ የሆነ ጥብቅ ግንኙነት ይመነጫል። ከእርሱ፣ ከአብ እና ከመንፈስ ቅድሱ ጋር ካልን ኅብረት ደግሞ በመካከላችን ኅብረት ይፈጠራል፣ ግንኙነታችንን በታማኝነት እንዴት መኖር እንደ ሚገባን እንድናውቅ ይረዳናል። 

ይህንን አስተምህሮ በድምጽ ለማዳመጥ ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት ይጫኑ!!
24 October 2018, 14:34