ፈልግ

2018.10.20 Steven Chu 2018.10.20 Steven Chu 

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ፣ ስቲቭ ቹን የጳጳሳዊ ሳይንስ አካደሚ አባል አድርገው ሰየሙ።

በጳጳሳዊ የሳይንስ አካደሚ ውስጥ አዲስ አባል የሆኑት ፕሮፌሰር ስቲቭ ቹ የተውለዱት፣ በሰሜን አሜርካ፣ ሚዙሪ ግዛት ውስጥ እ. አ. አ. የካቲት 28 ቀን 1948 ዓ. ም. ሲሆን፣ ከሮኬስተር ዩኒቨሲቲ፣ በሒሳብና በፊዚክስ ትምህርቶች የመጀመሪያ ድግሪያቸውን፣ ቀጥለውም እ. አ. አ. በ1976 ዓ. ም. ከካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲትይ በፊዝክስ የፒ ኤች ዲግሪያቸውን ማግኘታቸው ታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ፕሮፌሰር ስቲቭ ቹን፣ ከሌሎች የምርምር ባለሞያዎቹ ጋር በመሆን እንደ አውሮጳዊያኑ አቆጣጠአር 1997 ዓ. ም. በፊዝክስ የትምህርት ዘርፍ የኖቬል ሽልማት አሸናፊ እንደነበሩም ታውቋል። ፕሮፌሰር ስቲቭ ቹ ሽልማቱን ያገኙበት የጥናት ዘርፍ፣ የጨረር ብርሃንን በመጠቀም አቶሞችን ማቀዝቀዝ እንደነበር ታውቋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ በጳጳሳዊ የሳይንስ አካደሚ ውስጥ አባል እንዲሆኑ የሰየሟቸው ፕሮፌሰር ስቲቭ ቹ፣ በካሊፎርኒያ፣ ስታን ፎርድ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በፊዚክስ የትምህርት ዘርፍ፣ የሞለኪውል እና የሴሎች አፈጣጠር ትምህርት መምህር መሆናቸው ታውቋል። በቫቲካን፣ የጳጳሳዊ ሳይንስ አካደሚ የተመሠረተው እንደ አውሮጳዊያኑ አቆጣጠር በ1936 ዓ. ም. በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፒዮስ 11ኛ እንደ ተቋቋመ የሚታወስ ነው።

በቅድስት መንበር፣ የጳጳሳዊ ሳይንስ አካደሚ ስድስት ዋና ዋና ክፍሎች ያሉት ሲሆን እነዚህም ስለ መሠረታዊ ሳይንስ፣ ስለ ዓለማቀፍ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ፣ የሳይንስ ትምህርትና በማደግ ላይ ያሉ አገሮች ችግር፣ የሳይንስ ትምህርትና የፖሊሲዎች አወቃቀር፣ ባዮኤቲክስና የስነ እውቀት ምርምር የሚሉ እንደሚገኙበት ታውቋል። እነዚህ ሳይንሳዊ የምርምር ዘርፎች ከሚያልሙት በርካታ ግቦች መካከል፣ የምርምርና ቴክኖሎጂ ውጤቶች ለሰው ልጅ ጥቅማና አገልግሎት እንዲውሉ፣ የሳይንሳዊ ምርምር ለሰው ልጅ ከሚያቀርበው ቁሳዊ እድገት በተጨማሪ ሰብዓዊና ሞራላዊ እድገት ማምጣትን፣ ማሕበራዊ ፍትህን እንዲያስገኝ ማድረግን፣ እድገትን፣ በሕዝቦች መካከል አንድነትን፣ ሰላምን፣ ግጭቶች ለማስወገድ የሚያግዙ የመፍትሄ መንገዶችን ማግኘት፣ በሳይንስና እምነት መካከል ውይይቶችን ማድረግ፣ ባሕል፣ ከፍልስፍና እና ከእምነት የሚገኙ እሴቶችን መጠበቅ የሚሉ እንደሆነ ታውቋል።          

በጳጳሳዊ የሳይንስ አካደሚ ውስጥ አዲስ አባል የሆኑት ፕሮፌሰር ስቲቭ ቹ የተውለዱት፣ በሰሜን አሜርካ፣ ሚዙሪ ግዛት ውስጥ እ. አ. አ. የካቲት 28 ቀን 1948 ዓ. ም. ሲሆን፣ ከሮኬስተር ዩኒቨሲቲ፣ በሒሳብና በፊዚክስ ትምህርቶች የመጀመሪያ ድግሪያቸውን፣ ቀጥለውም እ. አ. አ. በ1976 ዓ. ም. ከካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲትይ በፊዝክስ የፒ ኤች ዲግያቸውን ማግኘታቸው ታውቋል። እ. አ. አ. ከ2013 ዓ. ም. ጀምሮ በሰሜን አሜርካ ስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ በፊዝክስ ዘርፍ የሞሌኩዩልና የሴል ፊዚክስ ትምህርት መምህር ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸው ታውቋል። በአቶሚክ ፊዚክስ ዘርፍ በርካታ ጥናታዊ ጽሑፎችን፣ በስማቸውም የተለያዩ የፈጠራ ባለቤትነት ማረጋገጫዎችን ማግኘታቸው ታውቋል። ከዚህም በተጨማሪ ፕሮፌሰር ስቲቭ ቹ እ. አ. አ. ከ2004-2008ን ዓ. ም. የሎሬንስ ብሔራዊ ቤተ መዘክር አስተዳዳሪና የፊዚክስ መምህር ሆነው እንዳገለገሉ፣ እ. አ. አ. ከ2009 – 2013 ዓ. ም. በሰሜን አሜርካ የኢነርጂ ዋና ጸሐፊ ሆነው ማገልገላቸው ታውቋል።

ፕሮፌሰር ስቲቭ ቹ ከሌሎች የምርምር አጋሮቹ ጋር በመሆን እ. አ. አ. በ1997 ዓ. ም. በፊዚክስ ትምህርት የኖቬል ሽልማት አሸናፊ መሆናቸው ታውቋል። ፕሮፌሰር ስቲቭ ቹ ሽልማቱን ያገኙበት የጥናት ዘርፍም፣ የጨረር ብርሃንን በመጠቀም አቶሞችን ማቀዝቀዝ እንደነበር ታውቋል። ከዚህም በተጨማሪ ፕሮፌሰር ስቲቭ ቹ በሰሜን አሜርካ የብሔራዊ ሳይንስ አካደሚ አባል፣ እንዲሁም በቻይናና በኮርያ የብሔራዊ ሳይንስና ቴክኖሎጂ አካደሚ አባል፣ ከተለያዩ የምርምር ተቋማት የክብር ድግሪን ማግኘታቸው ታውቋል።      

22 October 2018, 17:00