ፈልግ

Vatican Pope Angelus Vatican Pope Angelus 

በጥቅምት 11/2011 ዓ.ም ዓለማቀፍ የተልእኮ ቀን በቫቲካን መከበሩ ተገለጸ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በትላንትናው እለት ማለትም በጥቅምት 11/2011 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በእለቱ በተነበበው ቅዱስ ወንጌል ላይ ተመርኩዘው ካደረጉት የመጽሐፍ ቅዱስ አስተንትኖ በመቀጠል ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከደገሙት “የእግዚኣብሔር መልእክ ማርያምን አበሰራት” የሚለውን የመልእከ እግዚኣብሔር ጸሎት ከምዕመና ጋር በመቀባበል ከደገሙ በኋላ ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት በትላንትናው እለት ማለትም በጥቅምት 11/2011 ዓ.ም ዓለማቀፍ የተልዕኮ ቀን መከበሩን አስታውሰው ይህም ዓለማቀፍ የተልዕኮ ቀን “ከወጣቶች ጋር በጋራ በመሆን ቅዱስ ወንጌልን ለዓለም አናዳርስ” በሚል መሪ ቃል መከበሩን ቅዱስነታቸው ገለጸዋል።

የዚህ ዘገባ አቅራቢ መብራቱ ኃይለጊዮርጊስ ቫቲካን

በአሁኑ ወቅት ለወጣቶች ትኩረት በመስጠት 15ኛው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የብጹዕን ጳጳሳት አጠቅላይ መደበኛ ሲኖዶስ በመካሄድ ላይ እንደ ሚገኝ ያስታወሱት ቅዱስነታቸው በሁኑ ወቅት መልካም የሚባለውን መገድ በመጓዝ ትክክለኛውን የሕይወት ደስታ በማጣጣም ላይ የሚገኙ ብዙ ወጣቶች እንዳሉ ገልጸው ለእግዚኣብሔር ምስጋና ይግባውና ለሕይወታቸው ትክክለኛውን ትርጉም በማገኘት በእውነተኛ መንገድ ላይ በመጓዝ ላይ የሚገኙ ብዙ ክርስትያኖች እንደ ሚገኙም ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።

በአሁኑ ወቅት የጋዛ ሀገራቸውን ጥለው በመሄድ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች በብዙ ድካም እና ብርታት ሕይወታቸውን ለመንፈሳዊ ተልዕኮ ያዋሉ፣ የቅዱስ ወንጌል መስካሪ የሆኑ ብዙ ክርስትያኖች፣ ምዕመናን፣ ደናግላን፣ ካህናት እና አቡናትን በጸሎታችን ማሰብ እንደ ሚገባ የገለጹት ቅዱስነታቸው በዚህ አጋጣሚ ለእነርሱ ያለንን አድናቆት፣ ፍቅር እና ክብር በጸሎት በታገዘ መልኩ መገልጽ እንደ ሚገባ ከገለጹ በኋላ እንደ ተለመደው “እባካችሁን ለእኔ መጸለይ እንዳትዘነጉ” በማለት እንደ ወትሮ የመማጸኛ ጥሪያቸውን ካቀረቡ በኋላ ሐዋሪያዊ ቡራኬያቸውን ለግሰው ለእለቱ ያዘጋጁትን መልእክት አጠናቀዋል።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለማዳመጥ ከዚህ በታች የሚገኘውን ተጫወት የሚለውን ምልክት ይጫኑ
21 October 2018, 16:03