ፈልግ

Canonization of Pope Paul VI Canonization of Pope Paul VI  

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ በቅድስና አዋጅ ክብረ በዓል ለተገኙት በሙሉ ሰላምታቸውን አቅርበዋል።

እሑድ ጥቅምት 4 ቀን 2011 ዓ. ም. መላዋ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን፣ ሰባት አዳዲስ ቅዱሳኖችን ለመላው ምዕመናኖቿ ይፋ አድርጋለች። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ላይ ለተሰበሰቡት ምዕመናን፣ ነጋዲያንና የሃገር ጎብኝዎች እንዲሁም በመላው ዓለም የዕለቱን ልዩ የመስዋዕተ ቅዳሴውን ስነ ስርዓት ለተከታተሉት በሙሉ፣ ስባት የቤተክርስቲያን ልጆች ወደ ቅድስና መብቃታቸው ይፋ አድርገዋል። ቅድስናቸው የታወጀላቸውም የቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ብጹዕ ጳውሎስ ስድስተኛ፣ አቡነ ኦስካር አርኑልፎ ሮመሮ ጋልዳሜዝ፣ ፍራንቸስኮ ስፒነልሊ፣ ቪንቼንሶ ሮማኖ፣ ማርያ ካታሪና ካስፐር፣ የቅድስት ተሬዛ ናዛሪያ ኢኛሲያና ኑንሲዮ ሱልፕሪዚዮ መሆናቸው ታውቋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ በሮም 15ኛ የብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ አጠቃላይ መደበኛ ጉባኤን በመካፈል ላይ ከሚገኙት ብጹአን ካርዲናሎች፣ ብጹዓን ጳጳሳትና ክቡርን ካሕናት ጋር ሆነው ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት የስብከተ ወንጌል አስተንትኖ እንደገለጹት ቅዱሳን በኢየሱስ ክርስቶስ በሙላት እንድንኖር ያስተምሩናል ብለዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በተናንትናው ዕለት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ላይ ለተሰበሰቡት ቤተክህነት፣ ምዕመናንና እንግዶች በሙሉ ሰላምታቸውንም ካቀረቡ በኋላ አጭር ንግግር አድርገዋል። መስዋዕተ ቅዳሴን ከመፈጸማቸው በፊት ባደረጉት ንግግር አማካይነት ብጹዓን ካርዲናሎችን፣ ብጹዓን ጳጳሳትን፣ ካህናትንና፣ ለቅድስና አዋጅ ክብረ በዓል ብለው ከመላው የዓለም አካባቢዎች ለመጡት ምዕመናን በሙሉ ሰለምታቸውንና ምስጋናቸውን አቅርበውላቸዋል።

ንግግራቸውን በመቀጠል፣ ትናንት ይፋ ባደረጉት የቅድስና አዋጅ ላይ ለመገኘት ብለው ከበርካታ አገሮች ለመጡት ልኡካን በሙሉ ምስጋናቸውን አቅርበው በተለየ መልኩ ለንግስት ሶፊያ፣ ለኢጣሊያ ሪፓብሊክ መንግሥት ፕሬዚደንት፣ ለቺሊ ፕሬዚደንት፣ ለኤልሳልቫዶርና ለፓናማ ፕሬዚደንቶች ሰላምታቸውን አቀርባለውላቸዋል።

ለክብርት ግራሲያ ሮውን ዊሊያምና በካንተርበሪ ሊቀ ጳጳስ ለተመራው ልኡካን በሙሉ ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበውላቸዋል።

ለመንፈሳዊ ነጋዲያን፣ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ሆነው በብዙሃን መገኛዎች በኩል የመስዋዕተ ቅዳሴውን ስነ ስርዓት ለተከታተሉት በሙሉ ሰላምታቸውን አቅርበውላቸዋል። ቀጥለውምል በቅዱስ ጳውሎስ ስድስተኛ ዘንድ በስፋት የሚታወቀው የኢጣሊያ ካቶሊካዊ ሰራተኞች ማሕበር አባላት ሰላምታቸውን አቅርበውላቸዋል። 

የእነዚህን ቅዱሳን ፈልግ ለመከተል እገዛ እንድትሆነን በማለት ባቀረቡት ሃሳብ ወደ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዘንድ የጋራ ጸሎት ካደረሱ በኋላ የዕለቱን ስነ ስርዓት አጠቃልለዋል።

15 October 2018, 18:09