ፈልግ

2018.10.03 Apertura lavori Sinodo 2018.10.03 Apertura lavori Sinodo 

ር. ሊ. ጳ. “የቤተ ክህነት በስልጣን መመካት በቤተክርስቲያን ውስጥ የበርካታ ድክመቶች መነሻ ሊሆን ይችላል”።

የብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ በሐዋርያዊ ዕቅዶቹ ወይም አገልግሎቶቹ ፍሬያማ እንዲሆኑ የሚያደርጉ፣ በራእይና በትንቢት የታገዙ፣ የወደፊት ተስፋ እንዲያብብ በሚያደርጉ፣ መተማመንን በሚጨምሩ፣ ቁስሎችን በሚጠግኑ፣ ግንኙነቶችን በሚያጎለብቱ፣ የተስፋ ብርሃንን በሚፈነጥቁ፣ አንዱ ከሌላው እንዲማር በሚያደርጉ፣ መልካም የሆነ የወደ ፊት ጊዜን በሚያመቻቹ እቅዶች የተደገፈ እንዲሆን ያስፈልጋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ መስከረም 23 ቀን 2011 ዓ. ም. በቫቲካን በተጀመረው  15ኛው የብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ጠቅላላ መደበኛ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ማድረጋቸው ይታወቃል። የቅዱስነታቸውን ንግግር ሁለተኛውንና የመጨረሻውን ክፍል ንግግር ትርጉም ሙሉ ይዘት እንደሚከተለው ይቀርባል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

“. . . . . በመሆኑ ማዳመጥን ከቤተክርስቲያን የአገልግሎት ስልጣን ጋር በማዛመድ የተመለከትን እንደሆነ፣ የቤተክርስቲያን አባቶች የምዕመናኖቻቸን ድምጽ በሚገባ የማዳመጥ ፍላጎት የማይታይ ከሆነ በሐዋርያዊ አገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ውስጥ ሊያጋጥም የሚችል እንቅፋት ማለፍ ከባድ ሊሆን ይቻላል። ከቤተ ክህነት በኩል የእግዚአብሔርን ሕዝብ በሚገባ የማዳመጥ ፍላጎት የማይታይ ከሆነ፣ ቤተ ክህነት ከቤተክርስቲያን የተቀበሉትን የአገልግሎት ጥሪ እንደ ስልጣን እንጂ እንደ አገልግሎት አልተቀበሉትም ማለት ነው። ይህም በቤተክህነትና በምዕመናን መካከል መለያየትን በመፍጠር አንዱ ወገን ከሌላው ወገን ሊሰማና ሊማር የሚችልበት አጋጣሚ እንዳይኖር ያደርጋል። የቤተ ክህነት በስልጣን መመካት በቤተክርስቲያን ውስጥ የብዙ ድክመቶች መነሻ ሊሆን ይችላል። ይህን በመገንዘብ እስካሁን ለተፈጸሙት ስህተቶች ከልብ በመጸጸት ይቅርታን መጠየቅ ይኖርብናል።

በሌላ ወገን በብዙ ወጣቶች በበኩል ራስን ችለናል የሚል ፈጣን መደምደሚያዎች እንደሚንጸባረቁ ይስተዋላል። በግብጾች አባባል “በቤትህ ውስጥ የዕድሜ ባለ ጸጋ ከሌለህ ሄደህ ይዘሄው ና፣ ምክንያቱም አንድ ቀን ያስፈልግህ ይሆናል። ለረጅም ዘመናት ያካበትናቸውን በልካም እሴቶቻችንን ሸሽጎ ማስቀመጥ ወይም በከንቱ መጣል፣ አሁን እየታየ ወደመጣው አደጋ ይዳርገናል እንጂ ምንም ፋይዳ አይኖረውም። መላውን ትውልድ ግራ ወደ መጋባት ደረጃ ያደርሳል። ትውልድ ለብዙ ዘመናት የኖረበትን መልካም ባሕልና ወግና ልማድ ጠብቆ ማቆየትና መጠቀም መተኪያ የሌለው ሃብት በመሆኑ ከአንድ ትውልድ ወደ ሌላ ትውልድ መሸጋገር ይኖርበታል። ይህን ስናደርግ፣ የሕይወታችንን ትክክለኛ ትርጉም እንድንገነዘብ የሚረዳንን የመለኮታዊ ግልጸትን በፍጹም መዘንጋት የለብንም።

ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፣ ይህ የብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ልባችንን ለፍቅር፣ ለመደማመጥና ለአገልግሎት እንዲነሳሳ የሚያደርግ ይሁን። ይህ ጊዜ ቤተክርስቲያን ከምን ጊዜም በላይ በተለያዩ ውጣ ውረዶች፣ ችግሮችና ከባድ ሸክሞችን ተሸክማ የምትገኝበት ጊዜ ነው። ቢሆንም ቸሩ እግዚአብሔር በፍቅሩ ብዛት ከችግር አውጥቶን የተሟላ ሕይወት ኣንደሚሰጠን እምነታችን ያስገነዝባል። መጭው ጊዜ በፍርሃት የሚያስጨንቀን ሳይሆን ከእግዚአብሔር ጋር፣ ከወንድሞቻችንና ከፍጥረታት በሙሉ አንድነትን በመፍጠር የሕይወት ልምዶችን የምንቀስበት አጋጣሚ ይሆናል። የተሰጠን ተስፋ ለምን እንደሆነ ተገንዝበን በተለይም ተስፋን ለተጠሙ ወጣቶቻችን ማስተላለፍ ይኖርብናል። “ደስታ እና ተስፋ” የሚለው ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ሰነድ በቁጥር 31 ላይ እንደሚለው፣ “የሰው ልጅ መጭው ዘመን፣  የሕይወትን ትርጉምና ተስፋን ለትውልዶች ለማካፈል በሚችሉት ሰዎች እጅ ላይ ነው”።

በትውልዶች መካከል የሚደረግ ግንኙነት ተስፋን በመስጠት ትልቅ እገዛን ሊያበረክት ይችላል። ነቢዩ ኢዩኤል በትንቢቱ መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈሳለሁ፣ ወንዶችን ኣሴቶች ልጆቻችሁ ትንቢት ይናገራሉ፣ ሽማግሌዎቻችሁ ሕልም ያልማሉ፣ ጎልማሶቻችሁም ራእይ ያያሉ፣ በምዕ. 2. 28.

ይህ ትውልድ በቀላሉ መረዳት በሚቸግርበት ስነ መለኮታዊ አገላለጽ ውስጥ ሳንገባ፣ የውሸት ተስፋን በመስጠትና ያለፉ ስሕተቶችን በመደጋገም ሳይሆን፣ የእግዚአብሔርን መንግስት በቀላሉ መረዳት የሚችሉበትን መንገድ በማሳየት መርዳት ያስፈልጋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዮሐንስ 23ኛ፣ ያለ በቂ ማስረጃ የሚናገሩትን ሰዎች በማስታወስ ባደረጉት ንግግራቸው እንደገለጹት “ ስህተትንና ድክመትን እንጂ  ሌላ ምንም መመልከት የማይችል ትውልድ፣ የሚኖሩበትን ዘመን ካለፈው ዘመን ጋር በማወዳደር እጅ የከፋ አድርጎ የሚያስቀምጥ ትውልድ እንጂ ካለፈው ታሪክ መልካም ነገርን መማር የማይፈልግ ትውልድ ላይ ደርሰናል” ማለታቸውን ማስታወስ ያስፈልጋል።

ስለዚህ ይህ የብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ በጥቂቶች እጅ ብቻ ገብቶ የሚነበብ ሰነድን የሚያወጣና በዚህም ብዙዎች  የሚተቹት መሆን የለበትም። የብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ በሐዋርያዊ ዕቅዶቹ ወይም አገልግሎቶቹ ፍሬያማ እንዲሆኑ የሚያደርጉ፣ በራእይና በትንቢት የታገዙ፣ የወደፊት ተስፋ እንዲያብብ በሚያደርጉ፣ መተማመንን በሚጨምሩ፣ ቁስሎችን በሚጠግኑ፣ ግንኙነቶችን በሚያጎለብቱ፣ የተስፋ ብርሃንን በሚፈነጥቁ፣ አንዱ ከሌላው እንዲማር በሚያደርጉ፣ መልካም የሆነ የወደ ፊት ጊዜን በሚያመቻቹ እቅዶች የተደገፈ እንዲሆን ያስፈልጋል። ልብን በሚማርክ፣ አእምሮን ብሩሕ በማድረግ፣ ለእጆቻችን ሃይልን በመስጠት፣ በውጣቶች መካከል ልዩነቶችን ሳይፈጥር ንቃትን በመስጠት የወደፊት ራዕያቸውን በወንጌል መልካም ዜናና በደስታ የሚሞላ መሆን ያስፈልጋል። አመሰግናለሁ”።

04 October 2018, 17:59