ፈልግ

2018.10.06 Incontro Giovani e Padri Sinodali 2018.10.06 Incontro Giovani e Padri Sinodali 

ር. ሊ. ጳ. ፍራንቼስኮስ የጊዜውን ጥበብ መካፈል እንደሚያስፈልግ አሳሰቡ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ አባ ግርማቸው ተስፋዬ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ ጥቅምት 23 2018 ዓ.ም. እ.አ.አ. የወጣቶችን ሲኖድ በተመለከተ የጊዜውን ጥበብ መካፈል በሚል ርዕስ ከወጣቶች እና ከአዛውንቶች ጋር በአጉስቲኒያኑም ውይይት እንደሚኖራቸው ታወቀ።

ይህ በጥቅምት 23 ቀን 2018 ዓ.ም. እ.አ.አ. በሮማ ከተማ በአጉስቲኒያኑም የብጹኣን ጳጳሳትን ሲኖዶስ ምክንያት በመድረግ የሚደረገው ውይይት የሲኖዶሱ ተሳታፊዎች ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ ጋር በተለያዩ የወደፊት እቅዶች ላይ እንደሚመክሩና እንደሚወያዩ የተለያዩ ፅሑፎች እንደሚቀርቡ በተጨማሪም በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ ስለ ታሪክና ሕይወት በሚል ርእስ የሚቀርብ መጽሓፍም የፋ እንደሚሆን ታውቋል።

ወደፊት ለመራመድ ያለፈውን ጊዜ ማጤን አስፈላጊ ነው ጥልቅና ነባር ስርዓቶችም ያስፈልጋሉ ያለፉ መታሰቢያዎችንም ከግምት ውስጥ ማስገባት አስፈላጊ ነው ድፍረትና ወኔ ምናባዊ ነገርም ሊታከልበት ይገባል። በመቀጠልም ይላሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ ዓለም በወጣቶችና በአረጋውያን መካከል የሚደረግ ቅርርብና ውህደት እንዲሁም ኣብሮ መጓዝ ያስፈልጋታል።

ይህ የጊዜውን ጥበብ መካፈል ማለት በሕዝቦች መካከል ያለዉን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ዓለም ኣቀፍ ውጥን ነው። ይህ የጊዜውን ጥበብ መካፈል ማለት በዉስጡ ጥልቅ የሆነ ታሪክ ያዘለ ነው። ይህ የጊዜውን ጥበብ መካፈል ማለት የብጹኣን ጳጳሳትን ሲኖዶስ ምክንያት በመድረግ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ ከወጣቶችና እና አዛውንቶች ጋር በሮማ ኣጉስቲኒያኑም ጥቅምት 23 ቀን 2018 ዓ.ም. እ.አ.አ. ተገናኝተው የሚወያዩበት መልካም ኣጋጣሚ ነው።

በዚሁ ኣጋጣሚ በ2019 ዓ.ም. እ.አ.አ. የዓለም ኣቀፍ ወጣቶች ቀን አደረጃጀት ኮሚቴ ፕሬዚዳንት የሆኑት የፓናማው ሊቀ ጳጳስ ብጹኣ ኣቡነ ጆሴ ዶሚንጎ እንዲሁም የካቶሊክ ስልጣኔ ዳይሬክተር የሆኑት አንቶንዮ ስፓዳሮ ከመላው ዓለም ከተሰበሰቡ ወጣቶችና እና አዛውንቶች እንዲሁም ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ ጋርም ተገናኝተው እንደሚነጋገሩ ታውቋል።

የዚህም ክንውን መነሻ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ ከረጅም ጊዜ ጀምሮ በውስጣቸው ከነበረ በሰው ልጆችና በእነርሱም ትውልዶች መካከል ያለው ግንኙነት እንዲጠናከርና ኣብረው ኣስከ መጨረሻ መዝለቅ የሚችሉበት መንገድን ለማመቻቸት የሚለው ሲሆን ይህም ከ 30 በላይ በሆኑ ሀገራት ከ 250 በላይ ቃለ

ምልልሶችን በማሰባሰብ የተቀናበረ መሆኑንና ይህም በአንድ ለትርፍ ያልተቋቋመ አሜሪካን በቀል የሆነ የሕትመት ድርጅት ከሌሎች የሕትመት ድርጅቶች ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው።

ይህ በተመሳሳይ ጊዜ በአሜሪካን በእንግሊዘኛ እና በጣሊያንኛ ቋንቋ ታትሞ የሚወጣው መጽሐፍ በሌሎች አያሌ ቋንቋዎች ሊታተም እየተዘጋጀ ሲሆን ይህም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ በውስጣቸው የነበራቸው የረጅም ጊዜ ዕቅድና ተነሳሽነትን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችልና ይህም በትውልዶች መካከል ያለው ግንኙነት እንዲጠናከርና አብረው ኣስከ መጨረሻ መዝለቅ የሚችሉበት መንገድን ለማመቻቸት የሚያስችል እንደ የማዕዘን ድንጋይ ሊወሰድ የሚችል ሲሆን በዚሁም መጽሓፍ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ የካቶሊክ ስልጣኔ ዳይሬክተር ከሆኑት ከአንቶንዮ ስፓዳሮ ጋር ያደረጉትን ንግግር ያካተተ ሲሆን ይህም ንግግራቸው ከዚህ በፊት በኣንድ ማርሲሊኦ በሚል የጣሊያን የህትመት ድርጅት መታተሙ ይታወሳል።

09 October 2018, 17:26