ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ፡ ዛሬ የተጠናቀቀው ሲኖዶስ እየተብላላ መሄዱን ቀጥሉዋል!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዘወትር እሁድ በቫቲካን በምገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ እርሳቸው በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተመርኩዘው የሚያሰሙትን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ለመከታተል በራካታ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ እንደ ሚገኙ ይታወቃል። ቅዱስነታቸው በዕለቱ ማለትም በጥቅምት 18/2011 ዓ.ም በዕለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተመርኩዘው ያደርጉት አስተንትኖ በዕለቱ የተጠናቀቀውን እና ከባለፈው መስከረም 23/2011 ዓ.ም እስከ እሁድ ጥቅምት 18/2011 ዓ.ም “ወጣቶች፣ እምነት እና በጥሪ ላይ በማስተዋል ጥበብ የተሞላ ውሳኔ ማድረግ” በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የነበረው 15ኛው የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን አጠቃላይ መደበኛ የብጹዕን ጳጳሳት ሲንዶስ ማጠቃለያን አስመልክቶ በእርሳቸው መሪነት በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ከተደርገው መስዋዕተ ቅዳሴ በመቀጠል እንደ ተለመደው እና ዘወትር እሁድ እኩለ ቀን ላይ በዕለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተመርኩዘው ባሰሙት አስተንትኖ እንደ ገለጹት ዛሬ (ጥቅምት 18/2011 ዓ.ም) የተጠናቀቀው ሲኖዶስ እየተብላላ መሄዱን ቀጥሉዋል ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ታዳሚዎች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በትላንትናው ዕለት ማለትም በጥቅምት 18/2011 ዓ.ም በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን በእለቱ የተጠናቀቀውን 15ኛውን የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የብጹዕን ጳጳሳት አጠቃላይ መደበኛ ሲኖዶስ በተመለከተ ያስተለለፉትን መልእክት ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አባራችሁን በመሆን እንድትከታተሉን ከወድሁ እናጋብዛለን።

የተወደዳቸሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደም አረፈዳችሁ!

ዛሬ ጠዋት በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ውስጥ ወጣቶች ላይ ትኩረት አድርጎ የነበረው የብጹዕን ጳጳሳት ሲንዶስ ማጠቃለያን በማስመልከት መስዋዕተ ቅዳሴን አሳርገናል። በወቅቱ በቀዳሚነት የተነበበው ከነብዮ ኤርምያስ (31፡7-9) ላይ ተወስዶ የተነበበው ምንባብ ሲሆን ይህም በዚህ አሁን ባለንበት ወቅት ትኩረት የሚስብ ቃል ሲሆን ምክንያቱም እግዚአብሔር ለሕዝቡ የሰጣቸውን ተስፋ በሚገባ የሚያስ በመሆኑ የተነሳ ነው። ይህም እግዚአብሄር የሕዝቡ አባት ነው ብሎ የሚነሳ ቃል በመሆኑ ሕዝቡን የሚወድ እና እንደ ልጁ አድርጎ የሚንከባከብ በመሆኑ፣ በፊለፊታቸው የሚገኘውን የወደፊት ጊዜ አድማስ የከፈተ በመሆኑ፣ በቀላሉ ሊደረስበት የሚችልና ሊራመዱበት የሚችሉበት መንገድ በመሆኑ የተነሳ በጨማሪም ከዚያ ባሻገር “ዕውሩንና አንካሳውን ያረገዘችና የወለደችውንም ሴት በአንድነት፤ ታላቅ ጉባኤ ሆነው ወደዚህ ይመለሳሉ” (ኤር. 31፡8) ይህም ማለት የተለያዩ ዓይነት ችግሮች ያሉባቸውን ሰዎች ሁሉ ማለት ነው፣ ብሎ በመናገሩ እና መንገድ በመክፈቱ የተነሳ ለሕዝቡ የመጽናኛ ቃል ነው። ምክንያቱም የእግዚኣብሔር ተስፋ ልክ እንደ አንድ ማራኪ እንደ ሆነ፣ ሁሉም መልካም እና ቆንጆ ሆኖ እንደ ሚታይበት አንድ ማራኪ ማስታወቅያ አይደለም፣ ነገር ግን ለእያንዳንዱ ጥንካሬ እና ድክመት ላላቸው ሰዎች ሁሉ፣ ብቃት እና ብስለት ላላቸው ሰዎች ሁሉ እንደ እኛ እንደ ሁላችን ማለት ነው፣ በአጠቃላይ የእግዚኣብሔር የተስፋ ቃል ኪዳን እንደ እኛ ላሉ እውነተኛ ለሆኑ ሰዎች ሁሉ ነው።

ይህ የእግዚአብሔር ቃል ባሳለፍናቸው ሲንዶሱ በተደረገባቸው ሳምንታት ውስጥ ያጋጠሙን ልምዳች መሆናቸውን በሚገባ ይገልጻል፣ ጊዜው የሚያጽናና እና የተስፋ ጊዜ ነበር። ከሁሉም በላይ ደግሞ የማዳመጥ ጊዜ ነበር፣ በእርግጥ ማዳመጥ ጊዜን፣ ትኩረት፣ አዕምሮ እና ልብን መክፍት ይጠይቃል። ነገር ግን ቁርጠኝነት በየቀኑ ወደ መፅናናት ተለወጠ፣ ምክንያቱም ከሁሉም በላይ ደግሞ ተነሳሽነት ያላቸው እና ሕይወት ሰጪ የሆኑ፣ ከገዛት ታሪካቸው እና አስተዋጾዎቻቸው ጋር በእኛ መካከል የነበሩ ወጣቶች በመኖራቸው የተነሳ ነው። ሲኖዶሱን በተካፈሉ አባቶች ምስክርነት የተነሳ የአዲሱ ትውልድ ከሁሉም አቅጣጫ የተውጣጣ፣ ይህም ማለት ከተለያዩ አህጉራት እና ከተለያዩ ብዙ ሰብዓዊ እና ማህበራዊ ሁኔታዎች የተውጣጡ የተለያዩ እውነታዎች ወደ ሲኖዶስ እንዲገባ አስችሉዋል።

በዚህ መሰረታዊ የማዳመጥ ዝንባሌ ታግዘን እኛ እውነታዎችን ለማንበብ እና የዘመኑን ምልክቶች ለመገንዘብ ሞክረናል። በማህበረሰባዊ ግንዛቤ በእግዚአብሔር ቃልና በመንፈስ ቅዱስ ብርሃን ታግዞ በማስተዋል ጥበብ ተሞልቶ የተደርገ ውስኔ ነው። ይህም ጌታ ለካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከሚሰጣቸው እጅግ በጣም ውድ ስጦታዎች መካከል አንዱ ነው፣ ይህም ከተለያየ ዓይነት የተለያዩ እውነታዎች፣ ድምፆችን እና የተለያዩ የፊት ገጽታዎችን ለመሰብሰብ እና በዚህም ምክንያት የወንጌልን ጥልቅ እና ውስብስብነት ግምት ውስጥ በማስገባት በወንጌሉ ብርሃን ውስጥ መተርጎም በመቻላችን ነው። ስለዚህ በእነዚህ ጊዜያት እንደ አሁን ያለንበት ዲጂታል ዓለም፣ የስደተኞች ፍልሰት፣ አካላዊ እና ወሲባዊ ስሜቶችን፣ የጦርነቶች እና የብጥብጦች ትዕይንቶችን ያሉ ብዙ ተፈታታኝ ሁኔታዎች እንዴት መልስ መስጠት እንዳለብን ተወያይተናል።

የወይን ጭማቂ ቀስ በቀስ እንደ ሚብላላ ሁሉ እንዲሁም የዚህ ሥራ ውጤቶች አሁን በመብላላት ላይ ይገኛሉ። ጥሩ የወይን ጠጅ ቀስ በቀስ እንደ ሚብላላ ሁሉ ይህ ለወጣቶች ትኩረት በመስጠት የተካሄደው ሲኖዶስ ጥሩ የሆነ ፍሬ እንደ ሚያመጣ ተስፋ ተጥሎበታል። ነገር ግን የዚህ ሲኖዶስ አጠቃላይ መደበኛ ስብሰባ የመጀመሪያው ፍሬ የተገኘው ሲኖዶሱን በትክክለኛው መንገድ ለማዘጋጀት ከሞከርነው ዘዴ ውስጥ ከተገኘው ትክክለኛ መንገድ የመነጨ መሆኑን ለመናገር እፈልጋለሁ። ይህ ሲኖዶስ (ምንም እንኳን ጠቃሚ እና በጣም አስፈላጊ የሆነ ነገር ቢሆንም) ነገር ግን በዚህ ሲኖዶስ ማጠቃለያ ላይ አንድ ሰነድ ይፋ ማድረግ ግን እንደ አንድ ግብ አድርጎ የያዘው ነገር አልነበረም። ከሰነዱ በላይ ግን ከወጣቶች እና ከአረጋውያን ጋር በጋራ በመሆን በማዳመጥ እና በዋስተዋል ጥበብ የሚደረጉ ውሳኔዎችን በማድረግ ለእውነታዎች ምላሽ ለመስጠት የሚረዳ አንድ ዘዴን መቀየስ እና ለሐዋርያዊ ምርጫዎች እና ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት በዚያም አግባብ መስራት አስፈላጊ ነው።

 

 

28 October 2018, 17:22