ፈልግ

ከአንድ ዓመት በፊት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በኮሎምቢያ ያደረጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት ሲታወስ።

የዚህ ዘገባ አቅራቢ አባ ግርማቸው ተስፋዬ - የኢትዮጵያ ጳጳሳዊ ኮሌጅ፣ ቫቲካን

ከአንድ ዓመት በፊት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ በኮሎምቢያ ጉብኝት ማድረጋቸው በዛም ስለ ሰላምና ሥራ ኣስፈላጊነት መናገራቸው ይታወሳል። ፍራንሲስኮ በኮሎምቢያ ያደረጉት ጉዞ ከአንድ ዓመት በላይ ቢያስቆጥርም በቫቲካን ማህደረ መረጃ ስዕሎች, በቦጎታ, በቪላቪቼንሲዮ, ሜዴሊን እና ካርታጄና ውስጥ በጣም የተሻሉ እንቅስቃሴዎችን እንደታዘቡ የቫቲካን ከተማ የሬዲኦ ባልደረባ ጂኣዳ ኣኲሊኖን ዋቢ ኣድርጎ ዘግቧል።.

እ.ኣ.ኣ. ከመስከረም 6 እስከ 10 2017 ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ ወደ ቦጎታ, ቪላቪቼንሲዮ, ሜዴሊን እና ካርታጄና ያደርጉት በዚሁ 20ኛው ሓዋርያዊ ጉዞ ልቧን ለሕዝቧ መክፈትና እርቅ መፍጠር ኣለባት ብለው ባስታወሱት መሠረት የኮሎምቢያ ጳጳሳዊ ጉባዔ ይህንን ወር ሙሉ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስን ቃል መሠረት በማድረግ እንደሚሠራ ኣስታውቋል።

የግጭት ምልክቶች

በተለያዩ አንደ ፋርክ የፖለቲካና እንደ ኤሊን በሕብረት በተደራጁ ኃይሎች ከ 50 ዓመት በላይ ባስቆጠረው ጦርነት የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ ሠላምን ለማምጣት ያደርጉት ጉዞ የኮሎምቢያ መንግሥት እውቅና እንደሚሰጠው ኣስታውቋል። የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ በቪላቪቼንሲዮ ቦጃያ በሥርዐተ ኣምልኮ ውሰጥ የሃገራዊ እርቅ አንዲፈፀም ያደረጉት እንደው በኣጋጣሚ የተከሰተ ጉዳይ ሳይሆን እ.ኣ.ኣ. በ 2002 በተደረገው የጅምላ ጭፍጨፋ የኣካል ጉዳት ሰለባ የሆኑት ሰዎች ሁሉ የዚሁ የኣስከፊ ጦርነት ምልክቶችና ጠባሳዎች መሆናቸውን በመጥቀስ ሕዝቡ የጦርነትን ኣስከፊነት ከነዚህ መጥፎና ኣስከፊ ገፅታዎች እንዲረዳ የሚያመላክቱ ናቸው ብለዋል።

 

የዚሁ ጦርነት ሰለባዎችና ተጠቂዎች ከ 8,474 143 በላይ መሆናቸው ተገለፀ

የዚሁ ጦርነት ሰለባዎችና ተጠቂዎች ከ 8,474 143 ስምንት ሚሊዎን ኣራት መቶ ሰባ ኣራት ሺህ ኣንድ መቶ ኣርባ ሶስት በላይ መሆናቸው ተገልጿል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ የተለያዩ በጦርነቱ የተሳተፉትን በጦርነቱም ምክንያት የኣካልና የሥነ- ልቦና ቀውስ የደረሰባቸውን የምስክርነት ቃል ካዳመጡ በኃላ ሁሉም በትልቅ የይቅርታ መንፈስ እንዲተቃቀፉ ይቅር እንዲባባሉ እንዲሁም በሕብረት አንዲፀልዩ በዚሁም መንፈስ ለተሻለ የወደፊት ዕቅድ እምነትና ተስፋ እንዲያሳድሩ ጠይቀዋል።

ምክንያቱም ጥላቻ የመጨረሻው መደምደሚያ ሳይሆን ወደ ፍትህና ምህረት የሚመራንን ከእነሱም በፍጹም የማይነጣጠለውን እውነት እንድንይዝ ያስፈልጋል ብለዋል። ጥሪው ሓዘንን አንድንሽር ወንጀል የፈፀሙትን ሰዎች ከሰሩት ጥፋት ተምረው ተፀፅተው ወደ ሰላም ጉዞ እንዲመለሱና የሰላምን ጉዞ እንዲጀምሩ ለማድረግ

ነው። በዚሁም ኣኳኃን የእርቅ መንገድ በሆነው በጌታችን እየሱስ ክርስቶስ መስቀል ፊት የጦርነቱ ሰለባ የሆኑትን 8,474፣143 ስምንት ሚሊዎን ኣራት መቶ ሰባ ኣራት ሺህ ኣንድ መቶ ኣርባ ሶስት ሰዎች በጸሎታቸው ኣስበዋል። በኣሁኑ ሰኣትም ቢሆን የሰባዊ መብቶችን ጥሰት በመኖሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ የኣደጋው ሰለባዎች ቁጥር ቢቀንስም ሙሉ በሙሉ ግን ቆሟል ለማለት ኣይቻልም።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ በዚህ ጉዞኣቸው ቦጎታ እንደደረሱ በከተማዋ ያሉትን የመንግሥት ባለስልጣናት የቤተክርስቲያን ኃላፊዎች ብጹኣን ጳጳሳትንና ካህናትን እንዲሁም ወጣቶች ሠላምታ የሰጡ ሲሆን በመቀጠልም በቦሊቨር ፓርክ በተደረገው የመሥዋተ ቅዳሴ ሥርዓት ባሰሙት ቃለ-ምዕዳን የሰላም ፍለጋ ጉዳይ ሁሌም ቢሆን ክፍት መሆን አንዳለበት ሁልጊዜም ሠላምን ለማረጋገጥ መትጋት እንደሚያስፈልግ ሕዝቡም ለሠላም መረጋገጥ ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ እንዳለበት ኣስምረዉበታል። እግረ መንገዱንም የላቲን ኣሜሪካ የጳጳሳት ጉባዔ ይህንን ሠላም ለማረጋገጥ በሚደረገው ርብርብ ውስጥ በቅርብ ሆነው እንዲከታተሉና ለተግባራዊነቱም በተቻላቸው ኣቅም ሁሉ እንዲሰሩ ኣሳስበዋል ።

ፍቅርና ይቅር ባይነት

እንዲሁም እ.ኣ.ኣ. 1989 ለእምነት ጥላቻ ባለው ኤሊን በተሰኝው ቡድን በቪላቪቼንሲዮ የተገደሉት የኣራኡካ ጳጳስ የነበሩት ሞንሲኞር ጀሱስ ኤሚሊዎ ጃራሚሎ ሞንሳልቬ የብፅእና ሥርዐት ላይ በተደረገ ሥርዐተ-ቅዳሴ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ የሞንሲኞር ጀሱስ ኤሚሊዎን እንዲሁም እ.ኣ.ኣ. በ1948 በኣክራሪዎችና በነፃ ተቃዋሚዎች መካከል በተደረገ የእርስ በርስ ጦርነት ሕወታቸውን ያጡት ኣባ ማሪያ ራሚሬዝ ራሞዝን በማስታወስ እነዚህ ሰዎች ከበቀልና ከሕገ-ወጥነት የመውጣት ምሳሌዎች እንደሆኑ ተናግረዋል።

ከሜደሊን የእርቅና ሰላም ጥሪ ይግባኝ ወደ ሞት በሚል መልዕክት ኣስተላልፈዋል ይህም ጥሪ ቆየት ብሎ ሰላማዊ ትግል እርቅና ሰላም ተብሎ የተተረጎመ ሲሆን ሆጋር ሳን ጆሴ ከተባለ ኣካባቢ 300 የሚሆኑ የኣደጋው ሰለባ የሆኑ ሕፃናትን በኣንድ በሃገረ ስብከቱ በሚተዳደር የቤተሰብ ቤት ውስጥ የሚንከባከብ መሆኑ ታውቋል።

በማገባደጃቸውም ላይ ቅዱስ ኣባት ፍራንቼስኮስ ከካርታጄና ለመወደድ መዉደድ ይቅር ለመባል ይቅር ማለት እንደሚያስፈሊግ ጠቅሰው የግጭቶች ሁሉ መንስዔ የሆነውን ሕገ-ወጥነትን ወደ ጎን ካልተውነው ሁሉም ነገር ከንቱ ይሆናል ብለዋል። በስተመጨረሻም እያንዳንዱ ሰው እንክብካቤ ኣብሮ መሆንና የቅር ባይነት እንደሚያስፈለገው በኣንክሮት ኣውስተው ንግግራቸውን ደምድመዋል።

06 September 2018, 17:08