ፈልግ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ወደ ባልቲክ አገሮች ያደረጉትን ሐዋርያዊ ጉብኝት አስታውሱ።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በዛሬው ዕለት ማለትም ረቡዕ መስከረም 16 ቀን 2011 ዓ. ም. በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ላይ ለተሰበሰቡት በብዙ ሺዎች ለሚቆጠሩ ምእመናን፣ ነጋዲያንና ሀገር ጎብኝዎች የተለመደውን ሳምንታዊ የረቡዕ ዕለት የጠቅላላ ትምሕርተ ክርስቶስ አስተምህሮአቸው ለአራት ቀናት በሊቱዋኒያ ሌቶኒያ እና ኢስቶኒያ ያደረጉትን ሐዋርያዊ ጉብኝት በማከል የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮአቸውን ኣስተላልፈዋል። የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮአቸው ትርጉም ሙሉ ይዘት የሚከተለው ነው።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ አባ ግርማቸው ተስፋዬ - ቫቲካን

“በክርስቶስ የተወደዳችሁ ወድሞቼና እህቶቼ እንደምን ኣረፈዳችሁ!

ባለፉት ቀናት ወደ ባልቲክ ሃገሮች ማለትም ሊቱዋኒያ ሌቶኒያ እና ኢስቶኒያ ነፃነታቸውን የተቀዳጁበትን መቶኛ ዓመት የሚያከብሩበትን ጊዜ ምክንያት በማድረግ ሓዋርያዊ ጉብኝት ኣድረጌኣለሁ። እነዚህ የባልቲክ ሃገሮች ለመቶ ዓመታት በከባድ ቀንበር ሥር ነበሩ። በተለይም በመጀመሪያ በናዚ መንግሥት በማስከተልም በሶቪየት ጫና የተለያየ ችግርና መከራ ኣሳልፈዋል።

ከዚያም በመቀጠል በተለያዩ ማኅበራዊና ሰው ሰራሽ ችግሮች ውስጥ ተሳታፊም ነበሩ ለዚህ ነው ታዲያ ፈጣሪ የተመለከታቸው መከራቸውን የቆጠረላቸው። እዛ ለነበረኝ ቆይታና በተለይም ለ 3ቱ ሃገራት መሪዎች እና ከፍተኛ ባለሥልጣኖች የከበረ ምስጋናዬን ለማቅረብ እወዳለሁ። እንዲሁም ጳጳሳትንና ይህን ሓዋርያዊ ጉዞ እውን ለማድረግ በየትኛዉም መልኩ ደፋ ቀና ያሉትን ሁሉ ከልቤ ላመሰግናቸው እወዳለሁ።

እኔ ያደረኩት ጉዞ ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ሁለተኛ በእነዚሁ ሃገራት ካደረጉት ሓዋርያዊ ጉዞ ጋር ሲነፃፀር በብዙ መልኩ ይለያያል የእኔ ተልዕኮ ለእነዚህ ሕዝቦች በኣዲስ መልኩ የወንጌልን ደስታ የምሕረትን ኣብዮትና የርኅራኄን መንፈስ ለማወጅ ነበር። ምክንያቱም ነጻነት ፍፁም ትርጉም ባለው ፍቅር የታጀበ ካልሆነ በስተቀር እንደው በደረቁ ነጻነት ነጻነት ብንል ይህ ምንም ወደ ኣንጀት ጠብ የማይል ነገር ነው።

ወንጌል በችግራችን ጊዜ ሁሉ ብርታትን ያላብሰናል ነፍሳችንንም ለነጻነት ትግል ያነሳሳል እንዲሁም ደግሞ በነጻነት ጊዜ ማኅበረሰብ ቤተሰብና እያንዳንዱ ሰው የየዕለቱን ጉዞ በብርሃን ውስጥ ኣንዲጓዝ የሚያደርግ ነው።

ይህ ወንጌል በሚገባ ለኖረው ሰው ሕይወቱ የተስተካከለና ጥሩ ጣዕም እንዲኖረው የሚያደርግ ወይንም ለሕይወቱ ማጣፈጫ የሆነውን ጨው እንደመጨመር ነው። ይህ ወንጌል ከመጥፎ ብጥብጥ እና ከመደብ ልዩነት ኣንዲሁም ከራስ ወዳድነት መንፈስ ይጠብቀናል።

በሊቱአኒኣ የካቶሊኩ ማኅበረሰብ ቁጥሩ እጅግ ከፍ ያለ ነው ሌቶኒአ እና ኤስቶኒኣ የኦርቶዶክስና የሉተራን እምነት ተከታዮች ይበዛሉ እንደዚሁም ከእምነት ርቀው የሚኖሩትም የኅብረተሰብ ክፍል ብዛት ቁጥራቸው ቀላል ነው የሚባልም ኣይደለም። የሆነ ሆኖ ትልቁ ቁም ነገር በክርስቲያኑ ኅብረተሰብ መከከል ያለዉን ማህበራዊ ግንኙነት ላቅ ወዳለ ደረጃ ማድረስ ነው።

በእርግጥ እነዚህ ሕዝቦች ከዚህ በፊት በነበራቸው ተሞክሮ ይህንን በመካከላቸው ያለዉን ትስስርና መረዳዳት እንዲሁም መከባባር በመልካም ሁኔታ ኣዳብረዉታል። እንደ እውነቱም ከሆነ ውጤታማ በሆነ መልኩ ይህ የሃይማኖቶች ሕብረት በጉልህ የተስተዋለበት ነበር ለዚህም እማኝ የሚሆነው በሪጋ በሚገኘው የሉተራን ቤተክርስቲያን ካቴድራል በጸሎት መስተጋብር የመሳተፍና እንዲሁም በታሊኒ ከተለያዩ እምነት ተከታይ ወጣቶች ጋር የመነጋገርና የመወያየት ዕድል ኣግኝቻለሁ።

ከእነዚህ ከሦስቱ ሀገራት ባለስልጣኖች ጋር በተነጋገሩበት ጊዜ ለማህበረሰቡ በተለይም ደግሞ ለአውሮፓ ማህበረሰብ የሚሰጡትን ከፍተኛ አስተዋጽኦ በኣጽንዎት ኣሳስቤአለሁ። በተለይም የሰው ልጅ ክብርን በተመለከተ እንዲሁም ካለፈው ታሪክ ልምድ በመነሳት የማኅበራዊ እሴቶችን ለማሳደግ በሚደርገው ጥረት ከፍተኛ ኣስተዋጽ ማበርከት እንድሚችሉ ጠቅሻለሁ። አዛውንትና ወጣቱ ትውልድ በጋራ መወያየታቸው በተለይም ወጣቱ ትውልድ ከሥር መሠረቱ ብዙ ነገር ከኣባቶቹ መማር ወይም መቅሰም ይችላልና ይህ የሁለቱ ግንኙነት መቀጠል እንዳለበት ኣስገንዝቤኣለሁ ምክንያቱም እንዲህ በእድሜ የገፉትና ወጣቱ ትውልድ እየተመካከሩ ሲሠሩ ኣሁንንና መጪውን ጊዜ በእርግጠኝነት ውጤታማ ለማድረግ ይችላሉ።

ለእነዚህ ሃገራት ነጻነት ከመተሳስብና ከመረዳዳት እንዲሁም ከመልካም ኣቀባበል ጋር ኣብሮ የሚሄድና የእነርሱ ባሕል ጭምርመሆኑን ኣስታውሻቸዋለሁ። ሁለት ልዩ ስብሰባዎች ከወጣቶች እና ከአዛውንቶች ጋር ኣድርጌኣለሁ ከወጣቶቹ ጋር በቪልኒኡስ ያደርኩት ሲሆን ከኣዛውንቶቹ ጋር ደግሞ በሪጋ የደረኩት ነው። በቪልኒኡስ ኣደባባይ እጅግ በርካታ ወንዶችና ሴቶች ወጣቶች ነበሩ። በሊቱአኒአ በሚደረገው ጉብኝት ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ የእኛ ተስፋ የሚለው ጽሑፍ በኣደባባዩ ብትልቁ ተሰቅሎ ነበረ። በቦታው ይካሔዱ የነበሩት ምሥክርነቶች የጸሎቱንና የመዝሙሩን ውበት የሚገልጹና መንፈስን የሚያነቃቁ ለእግዚኣብሔር ልብን የሚከፍቱ ነበሩ። ሌላዉን ለማገልገል የነበረው ስሜት ከእኔንት የመዉጣት ስሜት በጣም ጥልቅ ነበር።

በሌቶኒአ ከኣዛውንቶቹ ጋር የትዕግሥትና የተስፋን ኣንድነት በተመለከተ ተወያይቻለሁ። በዚህም ላይ ከዚህ በፊት የነበሩትን ኣሰቃቂ ሁኔታዎች በእዚህም ውስጥ ያለፉቱ ሁሉ ኣዲሱ ትውልድ በእነርሱ ላይ ተተርሶ የወደፊት ጉዞው ብሩህ እንዲሆን እንዲያብብና ብሎም ፍሬ እንዲያፈራ ያደርጉታል። ውስጣችንን ሁል ጊዜ ክፍት በማድረግ ሁሉንም በልባችን በማቀፍና ተባብሮ በመጓዝ ሁሉን ማሸነፍ ይቻላል ነገር ግን ለእዚህ የመንፈስ ቅዱስ እርዳታና አብሮነት ያስፈልገናልና በጸሎት እንትጋ የእግዚኣብሔርንም ቃል ያለመታከት እናዳምጥ።

በሌቶኒአ ካካህናት ሕይወታቸውን ለእግዚኣብሔር አገልግሎት ካበረከቱና ከሴሚናሪስቶች ጋር የተወያየን ሲሆን እነሱም ሕይወታቸን በእግዚኣብሔር ላይ ማተኮርና ለፍቅሩም ተገዢ መሆን እንደሚገባቸው ከዚህ በፊት ይችን የእግዚኣብሔርን ቤተክርስቲያን ለማቋቋም ብለው የተሰደቡትን የተዋረዱትን የታሰሩትን የተሰደዱትን እስከ መጨረሻ ድረስ የተገለሉትን በመስታወስ እነርሱም ማለትም ካህናትና ደናግላን እንዲሁም ሁሉም ሕይወታቸውን ለእግዚኣብሔር አገልግሎት የሰጡት ሁሉ የሰማዕታትን ታሪክ በመጠበቅ የእነርሱን ኣብነት እንዲከተሉ ግድላቸውንም እንዲፈጽሙ ጠይቄኣለሁ።

ይህ ሁሉ ሰቆቃ በቆመበት በ75ኛው ዓመት በቪሊኒኡስ ሊቱዋኒያ ለሞቱት በብዙ ሺህ ለሚቆጠሩት ኣይሁዳዉያን ጸሎት ኣድርጌኣለሁ። በተመሳሳይ መልኩ በትግልና እና በነጻነት ሙዚየም ውስጥ በጊዜው የነበረው መንግሥት ለገደላቸው ላሰራቸው ለገረፉቸውና በከባድ ሁኔታ ላሰቃያቸው ሁሉ ጸሎት ኣድርጌኣለሁ።

ዓመታት ያልፋሉ መንግሥታትም ያልፋሉ ነገር ግን በቪሊኒኡስ የንጋት በር ላይ የምሕረት እናት የሆነችው ማርያም ኣስተማማኝ በሆነ ተስፋና መጽናናት ሕዝቧን መጠበቋን ቀጥላለች። 2ኛ የቫቲካን ጉባዔ ሰነድ ሉመን ጀንሲኡም ቁጥር 68.

የወንጌል ጠንካራ ምልክት ሁሌም እርግጠኛ የሆነ የፍቅር ሥራ ነው። እምነት ያለ ተግባር ከንቱ ነው። እንዲሁም ዓለማዊ ኣስተሳሰብና ኣመለካከት በሰፊው በተንሰራፋበት ቦታና ኣካባቢም ቢሆን እግዚኣብሔር ሰብአዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሁሉ ይህ እርዳታ እንዲደረግ በፍቅር ቋንቋ ይናገራል በምንችለው ሁሉ ነፃ ኣገልግሎት ለመስጠት ሁላችንም ዝግጁዎች መሆን ይጠበቅብናል። ልቦች ሲከፈቱ ተአምራት ይከሰታሉ እልም ባለ በረሃም ኣዲስ ሕይወት ይጀምራል”።

በመጨረሻም ሊቱአኒኣ ካኡናስ በሌቶኒአ ኣግሎና በኤስቶኒአ ታሊኒ በተደረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴዎች ላይ በጉዞ ላይ ያለው የእግዚኣብሔር ሕዝበ ክርስቶስ እውነተኛ ተስፋችን ነው በሚለው ቃል ላይ ዘወትር የእግዚኣብሔር ልጆች ሁሉ በተለይም በችግርና በሥቃይ ውስጥ ላሉ ሁሉ እናት ከሆነች ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጋር እምነቱን ኣድሶ የእግዚኣብሔር የተመረጠ የተቀባና የተቀደሰ ሕዝብ እግዚኣብሔር በውስጡ የጥምቀትን ጸጋ የሚያነሳሳለት መሆኑ ትገልጾ ሕዋርያዊ ጉብኝቱ ተደምድሟል

26 September 2018, 17:44