ፈልግ

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ “እሁድ ከሕይወታችን ታሪክ ጋር ሰላም የምንፈጥርበት ቀን ነው”።

በዚህ ዘመን ያለው ህብረተሰብ የመዝናኛ እና የእረፍት ጊዜን ኣጥብቆ ይመኛል ትኩረትን የሚከፋፍሉ የጥፋት ኢንዱስትሪዎች በጣም እየበለጸጉ እና ዓለምን ሁሉም ወደደራሳቸው የሚስቡበት ትልቅ መጫወቻ ቦታ እንዲሆን ያደርገዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ አባ ግርማቸው ተስፋዬ - የኢትዮጵያ ጳጳሳዊ ኮሌጅ - ቫቲካን

“በክርስቶስ የተወደዳችሁ ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ

የዐሥርቱ ትዕዛዛት ጉዞ ዛሬ የዕረፍት ትዕዛዝ ወደሆነው ወደ ሦስተኛው ትዕዛዛት ይመራናል። እንዲሁ ስንመለከተው ቀለል ያለ ትዕዛዝ ይመስላል ነገር ግን ይህ የተሳሳተ ግንዛቤ ነው። እውነተኛ ዕረፍት በእውነቱ ቀላል ነገር ኣይደለም ምክንያቱም የተሳሳተ እና ትክክለኛ ዕረፍት ኣለ። እነዚህን እንዴት ለይተን ማወቅ እንችላለን?

በዚህ ዘመን ያለው ህብረተሰብ የመዝናኛ እና የእረፍት ጊዜን ኣጥብቆ ይመኛል ትኩረትን የሚከፋፍሉ የጥፋት ኢንዱስትሪዎች በጣም እየበለጸጉ እና ዓለምን ሁሉም ወደደራሳቸው የሚስቡበት ትልቅ መጫወቻ ቦታ እንዲሆን ያደርገዋል። ዛሬ ያለው ተፅእኖ ጽንሰ-ሐሳብ በእንቅስቃሴውና በተግባሩ ውስጥ የስበት ኃይል እንጂ ሽግግር አይደለም። የሚያገኝውን ገንዘብ የእራስን እርካታ ለመግኘት ብጫ ያውለዋል ነገር ግን እንደ ምሳሌ ሊወሰድ የሚገባው የሚያገኝውን ገንዘብ በተለያየና ትክክለኛ በሆነ የደስታ ቦታ ለማዋል ከሚችለው ስኬታማ ሰው ነው።

ይሁን እንጂ ይህ አስተሳሰብ ትክክለኛ ያልሆነ የኣእምሮ አለመረጋጋትና ሽሽት እያሳደረ ነው። ሰው ዛሬ እንደሚያርፈው አርፎ አያውቅም, ነገር ግን በተመሳሳይ መልኩ ሰው ልክ እንደ ዛሬ ብዙ ባዶነት ተሰምቶት አያውቅም! መዝናናት፣ መውጣት፣ መጓዝ፣ ጉዞ፣ ብዙ ነገሮች የልብ ሙላትን አያቀርቡም። በእውነቱ እነርሱ እረፍትንም የሚሰጡ ኣይደሉም።

የዐሥርቱ ትዕዛዛት መልዕክቶች ወይም ቃላቶች የችግሩን ልብ ፈልገው በማግኝት በላዩም ላይ የተለየ ብርሃን በማብራት እውነተኛ ዕረፍት ምን እንደሚመስል ያሰምሩበታል። በጌታ ስም የሚደረግ የዕረፍት በውስጡ ትክክለኛ እና የተለየ ምክንያት ኣለው ምክንያቱም "እግዚአብሔር ሰማይን, ምድርን ባሕርንና በውስጣቸው ያለውን ነገር በስድስት ቀን ስለፈጠረ በሰባተኛው ቀን አረፈ ስለዚህ እግዚአብሔር ሰንበትን ባርኮታል ቀድሶታልም" (ዘጸአት 20፣11)።

ይህ እግዚአብሔር የፍጥረትን ፍጻሜ ይናገራል "እግዚአብሔርም ያደረገውን አየ፣ እነሆም እጅግ መልካም ነበረ" (ዘፍ 1:31). ከዚያም የማረፊያ ቀን ይጀምራል ይህም እግዚአብሔር ለፈጠራቸው ፍጥረታት ሁሉ ትልቅ ደስታ ነው ይህ ቀን የማሰላሰል እና የበረከት ቀን ነው።

እንግዲህ ከዚህ ትዕዛዝ ኣኳያ ዕረፍት ምን ማለት ነው? ዕረፍት ማለት የማስተንተን ጊዜ ነው ዕረፍት ማለት የማመስገን ጊዜ እንጂ በከንቱ የሚያልፍ ጊዜ ኣይደለም ዕረፍት ማለት እውነታን የምንመለከትበትና ሕይወት መልካም መሆንዋን ተመልክተን የምናመሰግንበት ጊዜ ነው ዕረፍት ከእውነታ ሽሽት ከሆነ ግን ይህት የእግዚኣብሔር ትዕዛዛት ይህንን ይቃወማል።

ለእኛ ለክርስቲያኖች ለጌታችን እለት የጌታ እለት እሁድ ሲሆን በዚህም ቀን በቅዱስ ቁርባን ኣማካኝነት ምስጋናችንን ለእግዚኣብሔር እናቀርባለን። በዚህም ዕለት እግዚኣብሔርን ሰለሰጠን ህይወትህ

እናመሰግነዋለን ስለምሕረቱ እናመሰግነዋለን ስለሰጠን ስጦታዎች ሁሉ እ ግዚኣብሔርን አናመሰግነዋለን። እሁድ ሌሎች ቀኖችን የምናስታውስበትና የምንባርክበት ቀን በሕይወታችን ከሁሉ ነገር ጋር ሰላም የምንፈጥርበት ቀን እንጂ እነርሱን የምንደመስስበት አይደለም። በጣም ብዙ ሰዎች በሰላምና በፍቅርና በደስታ ለመኖር እድል ያላቸው ሲሆን በሰላምና በፍቅርና በደስታ ሲኖሩ ግን ኣይታዩም። ሰንበት ግን በኣንፃሩ ህይወት ውድ መሆንዋን ቀላል አለመሆንዋን አንዳንድ ጊዜ ዉታ ውረድ የበዛባት ብትሆንም ሁለ ጊዜ ግን ውድ መሆንዋን ይነግረናል።

ወደ ትክክለኛ ዕረፍት ውስጥ መግባታችን ይህ የእግዚአብሄር ሥራ ነው ነገር ግን ከእርግማን እና ከእርሱ ጋር ተያይዘው ከሚመጡ ነገሮች እንድንርቅ ያስፈልገናል (Apostolic Exhortation Evangelii Gaudium, 83ን ይመልከቱ) ልብን በደስታ ውስጥ እንዳይመላለስ ማድረግ በቀላሉ የልብን ደስታ ማጨለም ነው። በረከት እና ደስታ ልብን ወደ መልካምነት የሚመሩ ትክክለኛና በሳል ኣካሄዶች ናቸው።

መልካም የሆነ ነገር ሁሉ መልካም ነውና የሚወደድ ነገር ነውና በሰው ላይ ሊጫን ሳይሆን ሰው ሁሉ በራሱ የሚመርጠው ነገር ነው።

እምዲሁ ሰላምም ልክ እንደ መልካም ነገር የሚመረጥ እንጂ በሰው ላይ የሚጫን ወይም በድንገት የሚገኝ ነገር ኣይደለም። ሰው በልቡ ውስጥ ካለው ከሚቆረቁረው ነገር ለመሸሽ የግድ ያከሚቆረቁረው ነገር ጋር መስማማት ይጠበቅበታል። ከራስ ታሪክ እና ከራስ ነባራዊ ሁኔታ ጋር መታረቅ የግድ ነው።

እኔ ራሴን እጠይቃለሁ, እያንዳንዱስ ከገዛ ራሱ ታሪክ ጋር ታርቋልን? እንዲህ ብለንም ራሳችንን እንጠይቅ: እኔ ከኔ ከራሴ ታሪክ ጋር እርቅ አለኝን? እውነተኛ ሰላም ማለት የራስን ታሪክ መለወጥ ሳይሆን ነገር ግን የራስን ታሪክ እንዳለ ተቀብሎ ዋጋ ሰቶ መመርመርና ትክክለኛ መስመር እንዲይዝ ማድረግ ነው።

በኑሮ ሒደት ውስጥ ስንት ጊዜ የታመሙ ክርስቲያኖች ከሌላ ነገር ከሚገኝ ደስታ ይልቅ በእውነተኛ ነገር በተመሰረተ ትክክለኛ ደስታ ሲፅናኑ እንዲሁም በጣም ጥቂት ነገር ኖሯቸው በዛች ጥቂት በሆነች ነገር እጅግ በጣም ደስተኛ የሆኑ ክርስቲያኖች ብዙ ኣሉ።

ጌታ በኦሪት ዘዳግም ውስጥ እንዲህ ይላል"በፊታችሁ ሕይወትንና ሞትን በረከትንና መርገምን እንዳስቀመጥኩ ኣኔ ሰማይና ምድርን በኣንተ ላይ ኣስመሰክራለሁ እንግዲያው አንተና ዘርህ በሕይወት ትኖሩ ዘንድ ሕይወትን ምረጡ" (30:19). ይህ ምርጫ የድንግል ማርያም "ምርጫ" ነው። ይህ ምርጫ ለመንፈስ ቅዱስ ራስን የማቅረብና ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ እጅግ በጣም ከባድ በሆነ ፈተና ጊዜ ለአብ ራሱን አሳልፎ የሰጠበትና እንዲሁም ወደ ትንሳኤ የተራመደበት ምርጫ ነው።

ህይወት መቼ ነው ቆንጆ ነው ምንለው? ህይወት ቆንጆ ነው የምንለው ምንም እንኳን ሕይወት መንም መልክ ቢኖረው ሰለ ራሱ መልካም ማሰብ ሲጀምር። እውነተኛ ዕረፍት እንዳይኖረን ውስጣጭን የሚፈጠሩ የጥርጣሬ ግድግዳዎችን ማፈራረስ ስንችል ብቻ ነው። ልባችንን ወደ እግዚኣብሔር ጥበቃና እርዳታ በመመለስ በመዝሙር 62፣2 ላይ እንደሚገኘው "ነፍሴ በእግዚኣብሔር ብቻ እረፍት ታደርጋለች የሚለዉን ቃል" በእምነት መድገም ስንችል ብቻ ሕይወት የተዋበች ትሆናለች”።

05 September 2018, 17:47