ፈልግ

2018.09.20 SALA CLEMENTINA: Associazione nazionale Lavoratori mutilati e invalidi del lavoro (Anmil) 2018.09.20 SALA CLEMENTINA: Associazione nazionale Lavoratori mutilati e invalidi del lavoro (Anmil) 

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የሰዎች መተጋገዝ የጋራ ጥቅምን ያሳድጋል ማለታቸው ተገለጸ።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የኢጣሊያ የአካል ጉዳተኞች ሕብረት ሥራ ማሕበር አባላትን ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት፣ ማሕበሩ በሥራ ላይ በሚያጋጥማቸው አደጋም ይሁን ሕመም ምክንያት የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው አባላት እና ለቤተሰቦቻቸው ለሚያደርጉት ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበውላቸውል።

የዚህ ዜና  አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ትናንት መስከረም 10 ቀን 2011 ዓ. ም. የኢጣሊያ የአካል ጉዳተኞች ሕብረት ሥራ ማሕበር አባላትን ተቀብለው ባነጋገሩበት ጊዜ እንዳስታወቁት የሕብረት ሥራ ማህበርን አንዱ በሌላው ጫንቃ ላይ የሚሆንበት አድርጎ መውሰድ እንደሌለበት አሳስበዋል።

በተባበሩት መንግሥታት ዓለም አቀፍ የሥራ ድርጅት ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት ከሥራ ጋር በተያያዘ በዓለማችን በየሁለት ደቂቃዎች ልዩነት ሁለት ሰዎች እንደሚሞቱ ታውቋል። በዚህም መሠረት ከሥራ ጋር በተያያዘ አደጋና ሕመም የተነሳ በዓመት ከ2 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ወንድና ሴት ሥራተኞች እንደሚሞቱ ታውቋል። በተጨማሪም በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩትን ሰዎች በግማሽ ወይም ሙሉ በሙሉ አካለ ጎደሎ እንደሚያደርጋቸው በተባበሩት መንግሥታት ዓለም አቀፍ የሥራ ድርጅት አሳውቋል።

ሐሙስ ጠዋት መስከረም 10 ቀን 2011 ዓ. ም. ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የኢጣሊያ የአካል ጉዳተኞች ሕብረት ሥራ ማሕበር አባላትን ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት፣ ማሕበሩ በሥራ ላይ በሚያጋጥማቸው አደጋም ይሁን ሕመም ምክንያት የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው አባላት እና ለቤተሰቦቻቸው ለሚያደርጉት ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበውላቸውል። ቅዱስነታቸው በተጨማሪም የአካል ጉዳተኞቹ በደረሰባቸው የአካል መጓደል ምክንያት ሥራን መስራት ካልቻሉ የሚሰማቸውን ሐዘን አስታውሰው ይህም በቤተሰቦቻቸው ወይም በወላጆቻቸው ላይ ሊያስከትል የሚችለው የኑሮ ቀውስ እንዳለ አስረድተው ለእነዚህ የአካል ጉዳተኞችና ለቤተሰቦቻቸው ያላቸውን ቀረቤታን ገልጸውላቸዋል።

የጋራ ትብብርና ድጎማ ሊኖር ይገባል፣

ከመንግሥት በኩል የአካል ጉዳተኞችን ለመደጎም ተብሎ የሚወሰድ ውሳኔ በማዕከላዊ ባለስልጣን ወይም መንግሥት በኩል እንደሚደረግ መልካም ተግባር እንጂ አካል ጉዳተኞችን የሕብረተሰብ ሸክም ለማድረግ የሚወሰድ ውሳኔ ተደርጎ መወሰድ የለበትም ብለዋል። በመሆኑም የጋራ ትብብር በማሕበራዊ ድጋፍ በመታገዝ ለጋራ ጥቅም ሲባል አቅመ ደካማ ለሆኑት በሙሉ ሊደረግ የሚገባ እገዛ ነው ብለዋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ማሕበራዊ አስተምህሮን በማስታወስ በጋራ ትብብርና በመስግሥት ድጎማ መካከል ሚዛናዊ እኩልነት ሊኖር ይገባል ብለው ለአካል ጉዳተኞች የሚደረግ ትብብርና ድጎማ ተረጂዎችን ማከናወን በሚችሉት የሥራ ዘርፍ ተሰማርተው ለዓለማችን እድገት የበኩላቸውን አስተዋጽዖ የሚያበረክቱ ማድረግ አለበት እንጂ የሚያሰንፍ መሆን የለበትም ብለዋል።

ሕዝብና የምርት ውጤቶች፣

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሥራና በሥራ ውጤቶች መካከል ያለውን ግንኙነት በማሰብ እንዳስገነዘቡት የሰዎችን ማንነት ከሚያመርቱት የምርት ውጤትና ሃብት ጋር ማዛመዱ ከምንም ጋር የማይወዳደረውን ሰብዓዊ ማንነታቸውን ሊያሳንስ እንደሚችል ያላቸውን ስጋት ገልጸዋል። የዚህ ዓይነት ሥርዓት ወይም አካሄድ የሰውን ልጅ ለጭቆናና ለምዝበራ ወደሚዳርግ ጽንሰ ሃሳብ ሊያመራ እንደሚችል አስረድተዋል።

በመሆኑም ዓይናችንን ከፍተን እነዚያ ማሕበራዊ እድገት ለማምጣት በሥራ ላይ የተሰማሩት ሰብዓዊ ፍጡር መሆናቸውን፣ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን መሆናቸውን መገንዘብ እንጂ እንደ ምርት ውጤቶች ወይም እንደ ዕቃ መመልከት የለብንም ብለዋል። 

21 September 2018, 16:41