ፈልግ

2018.09.07 Francesco a Ground Zero, 25 settembre 2015 2018.09.07 Francesco a Ground Zero, 25 settembre 2015 

ሦስት ርዕሣነ ሊቃነ ጳጳሳት ፍቅር ከጥላቻ እንደሚበልጥ ማሳሰባቸው ተገለጸ።

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ እነዚህን የኣደጋ ሰለባዎች በማስታወስና እንደዚህ ካሉ ምሳሌኣዊ ቦታዎች የሁሉም ሃይማኖት ተከታዮች ለሰላምና የእግዚኣብሔርን ሥም ለጦርነት ወይም ላልተፈለገ ነገር እንዳያውሉ መልዕክት ኣስተላልፈዋል። በር.ሊ.ጳ. ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ 2ኛ ተጀምሮና በየዓመቱ በሁሉም የሃይማኖት ኣባቶች ስለ ሰላም ይደረግ የነበረው የኣሲዚው ጸሎት ይበልጥ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት በዚሁ ጊዜ ተወስቷል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ክቡር አባ ግርማቸው ተስፋዬ፤

ር.ሊ.ጳ. ቅዱስ ዮሃንስ ጳውሎስ 2ኛ ር.ሊ.ጳ. በኔዲክቶስ 16ኛና ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ከሽብርተኝነትና ከአረመኔያዊነት ይልቅ ሁሉንም ዓይነት የጥላቻ እና የጭካኔ ድርጊት የሚያሸንፍ የፍቅር ጎዳናን መከተል እንደሚገባ ጥሪ ማድረጋቸው ይታወሳል ሲል የቫቲካን ከተማ የሬዲዮ ኣገልግሎት ባልደረባ ኣሌክሳንድሮ ጊሶቲን ዋቢ በማድረግ ጠቅሷል።

ዕለቱ ረቡዕ መስከረም 12 ቀን 2001 ዓ.ም. እንደተለመደው በቅዱስ ጴጥሮስ ኣደባባይ ከተለያዩ ቦታ የተሰበሰቡ ምዕመናን እንደወትሮው ሁሉ ር.ሊ.ጳ ዮሃንስ ጳውሎስ 2ኛ በተገኙበት የዕለተ ረቡዕ ኣጠቃላይ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ቢሰበሰቡም እንደ ትናንት በኣሜሪካ ምድር በተከሰተው የኣሸባሪዎች እኩይ ተግባር ምክንያት እምብዛም ደስተኛ ኣይመስልም ነበር። ከኣንድ ቀን በፊት በኣሜሪካ የተከሰተው የመንትዮቹ ሕንፃዎች መመታት የአውሮፕላን በፔንታጎን ላይ መወድቅ ተስፋ የቆረጡ ሰዎች ከሚወድቁት ሕንፃዎች ለመሸሽ ወዲህና ወዲያ መሯሯጥ ከሕንፃ መፈራረስ የሚወታው አቧራ በየቦታው የነበረው የኣደጋው ሰለባዎች ደም በጎዳናዎች ላይ የሞቱ ሰዎች መመልከት በሕዝቡ ውስጥ የፍርሃት መንፈስ መዝራታቸው ግልጽ ነው።

ር.ሊ.ጳ ዮሓንስ ጳውሎስ 2ኛ ይህንን ኣስደንጋጭና ኣስጨናቂ ክስተት የተከታተሉት በጋንደልፎ ከሚገኘው የዕረፍት ቤታቸው ነበር። ይህንንም እንደተመለከቱ ር.ሊ.ጳ ዮሓንስ ጳውሎስ 2ኛ የኣሜሪካን ርእሰ ብሔር የሆኑትን ጆርጅ ቡሽን በማግኘት የተሰማቸዉን ጥልቅ ሓዘን ለእሳቸውና ለኣሜሪካን ሕዝብ ለመግለጽ ፈልገው በወቅቱ የቫቲካን ከተማ የሕትመት ክፍል ኃላፊ ወደሆኑት ወደ ጆኣኪን ናቫሮ ቫልስ ቢደዉሉም የኣሜሪካው ርእሰ ብሔር የሆኑትን ጆርጅ ቡሽ ግን ለደህነነታቸው ሲባል ያሉበት ቦታ በቀጠታ ሊገኙ ባለመቻላቸው ር.ሊ.ጳ ዮሓንስ ጳውሎስ 2ኛ ሰለተፈጠረው ኣስፈሪና ኢሰብኣዊ ሁኔታ ጠቅሰው በዚህ የኃዘነና የጭንቅ ሰዓት ኣብረዋቸው እንደሚቆሙና በጸሎትም ኣብረዋቸው እንዳሉ የሚገልጽ የቴሌግራም መልክት ልከው ነበር።

በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ጨለማው ቀን ቢሆንም ጥላቻ

በቅዱስ ጴጥሮስ የሚገኘው የድምፅ ማጉሊያ ይህ ኣስደንጋጭና ኣስገራሚ ክስተት ለሱባዔና ለጸሎት እንደጠራን በመጥቀስ በዕለቱ ኃዘኑን በማስመልከት ምንም ዓይነት ጭብጨባ እንዳይደረግ ምዕመናኑን ተማጽነዋል። የር.ሊ.ጳ. ካርሎ ዎይቲላ በኣደባባዩ ለተሰበሰበው ሕዝብ የዛሬው ዕለት ማለትም መስከረም 11 በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ የሰውን ክብር የሚነካና የሚፈታተን ጨለማ ቀን ነው ብለው ሲናገሩ በተከሰተው ክስተት እጅግ ማዘናቸው ከዉስጣቸው የሚወጣው ድምጻቸው ይመሰክር ነበር።

በመቀጠልም ኣንዳንድ ጊዜ የሰው ልጅ ልብ ከውስጡ ያልተጠበቁና ያልተገመቱ ሓሳቦች የሚፈልቁበት እጅግ በጣም ጥልቅ የሆነ ነው ካሉ በኃላ አንዴት እንዲህ ዓይነቱ ጨካኝና የዱር የሆነ አሳዛኝ ሁኔታ ሊከሰት ይችላል በማለት ኣስጨናቂውንና በሁሉም ልብ ውስጥ የሚመላለሰውን ጥያቄ ከጠየቁ በኃላ በምንም መልኩ ተስፋ መቁረጥ እንደማያስፈልግ ተናግረው ነበር። ምንም እንኳን ጨለማ ብርሃንን የዋጠ ቢመስልም እንኳን

እምነት ያለው ሰው ክፋትና ሞት የመጨረሻ ቃሎች እንዳልሆኑ እንደሚያስታውስ ጠቁመው ነበር። የጥላቻና የሕገወጥነት መንፈስ እንዳይነግስ ጸሎት ካደረሱ በኃላ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሁሉም ሰው የጥበብና የሰላም ሃሳብ እንዲኖረው ተማጥነዋል ።

ሃይማኖት በፍጹም ለግጭት ምክንያት ሊሆን ኣይችልም

ከጥቂት ቀናት በኋላ ር.ሊ.ጳ. ዮሐንስ ጳውሎስ 2 ኛ አብዛኞቹ ሙስሊሞች ወደሚኖሩበት ሀገር ወደ ካዛኪስታን የመጓዝ እቅድ ቢኖራቸውም ብዙ ሰዎች ይህንን ጉዞ በተለያዩ ምክንያቶች እንዲሰርዙ እያግባቧቸው ነበር ምክንያቱም ኣሜሪካ እ.ኣ.ኣ. በጥቅምት 7 ቀን የታሊባን ሽምቅ ተዋጊዎች ቢን ላዲንን ኣሳለፈን ኣንሰጥም በማለታቸው ኣሜሪካ ኣፍጋኒስታንን እንደምትደበድብ ኣስታውቃ ነበር ነገር ግን ካርሎ ዎይቲላ ወደ ካዛኪስታን በመጓዝ ከካዛኪስታን ዋና ከተማ ከኣስታና ለክርስቲያኖችና ለመላው ለተለያዩ እምነት ተከታዮች ሰላም የሰፈነባት ሕይወትን የምትወድና የምታከብር በሕገወጥነት ሳይሆን በ ፍትህና በወንድማማችነት የምታድግ ዓለምን ለመፍጠር እንዲተባበሩ ጠይቀው ነበር።

በመቀጠልም ክርስቲያኖችና እስላሞች በኣንድነት ወደፈጣሪኣቸው ወደ እግዚኣብሔር እንዲጸልዩ በዚሁም ምክንያት ለዓለም ሁሉ ኣስፈላጊና መሠረት የሆነው ሰላም በምድር ላይ ይነግሳል ብለዋል። ምንም እንኳን በእድሜና በህመም ብዙ ቢሰቃዩም በ 1986 ዓ.ም. እ.ኣ.ኣ. የተጀመረው ለዓለም ኣንድነትና ሰላም በተላያዩ የሃይማኖት መሪዎች በሚደረገዉ ጸሎት በቁርጠኝነትና በቀጣይነት ሊደረግ እንደሚገባዉም በ2002 በተደረገው ጸሎት ላይ ማሳሰባቸው ኣይዘነጋም።

ሰላምና ፍቅር ለሰፈነባት ዓለም እንሰራለን

ከሰባት ዓመት በኃላ ከዛ ኣስደንጋጭ የማክሰኞ ክስተት በኃላ በሚያዝያ 20 ቀን 2008 ዓ.ም. እ.ኣ.ኣ. ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛ ኒው ዮርክ ወደሚገኘው ግራዉንድ ዜሮ ወደሚባለው ለዚሁ ለመስከረም 11ዱ ክስተት ወደተዘጋጀው ሙዝየም ማምራታቸው ነገር ግን ምንም ዓይነት ንግግር ባያደርጉም ተሳፍረው በመጡበት ኣውሮፐላን በኒው ዮርክ እና በዋሺንግተን የኣደጋው ሰለባ ለሆኑት ሻማ ያበሩ ሲሆን የኣደጋው ሰለባ ቤተሰቦችንም ኣንዳንዶቹን ኣግኝተው ኣነጋግረዋል።

በዛም በኣንድ ወቅት አነዚያ ሁለቱ መንትያ ሕንፃዎች ቆመው በነበረበት ቦታ ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛ ተንበርክከው የፍቅር ኣምላክ ወደሆነው ወደ እግዚኣብሔር ፍቅር ርኅራሄና እርቅ በምድር ላይ እንዲሰፍን ተማፅነዋል። ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛ እግዚኣብሔር ወደዚህ ኣመፀኛ ወደሆነው ዓለምና ወደ ሁሉም የሰው ልጆች ልብ እንዲሁም በምድር ላይ ላሉ ሕዝቦች ሁሉ ሰላም እንዲሆን ተማጽነዋል። በመጨረሻም ከኒው ዮርክ ሊቀ ጳጳስ ኤድዋርድ ኤጋን ጋር በመሆን እግዚኣብሔር እንዲያጽናናን በተስፋ እንዲያጠነክረን ፍቅርና ሰላም በሰው ልጆች ልብና በዓለም ሁሉ እንዲሰራፋ እኛም ለዚሁ ያለመታከት እንድንሰራ ጥበብና ጉልበት እንዲሰጠን ተማጽነው የዕለቱ ፕሮግራም መቋጨቱ ይታወሳል።

በግራዉንድ ዜሮ በሚባለው ሙዚየም በመስከረም 11 ሰለባ ለሆኑት ነጭ ጽጌሬዳ እበባ ተቀመጠ

ሌላ ሁለተኛ ሰባት ዓመት ካለፈ በኃላ ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ከእሳቸው ቀደም ከነበረው ከቤኔዲክቶስ 16ኛ ሙሉ ለሙሉ የተለየ ሁኔታ አጋጥሟቸዋል። በፊት በኣደጋው ጊዜ የነበረው ፍርስራሽ ቦታ ልክ በመንትዮቹ ሕንፃ ልክ ሁለት ትልልቅ ገንዳዎች ተሰርተዋል። በጠርዙም ላይ የዘጠና ሃገራት ዜግነት ያላቸው የኣደጋው ሰለባዎች የሁለት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰባ ኣራት 2974 ሥም ዝርዝር ተፅፎ ይገኛል። በመስከረም 25 2015 ዓ.ም. እ.ኣ.ኣ. ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ለጻሎት ከመሰብሰባቸው በፊት ነጭ ጽጌሬዳ ኣበርክተዋል።

በዛን ጊዜ የነበረው ሰማይ ከኣሥራ ዐራት ዓመት በፊት የነበረዉን ሰማይ ቢያስታዉስም ሁለቱ መንትያ ሕንፃዎችና ከእነርሱም ግርዶሽ ያርፍ የነበረው ጥላ ግን በቦታው የለም ነገር ግን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ከመሄዳቸው ቅርብ ወራት በፊት የተመረቀው የነፃነት ሕንፃ እነሱን ተክቶ በቦታው ተገኝቷል። ከዚህ በፊት ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ የኣደጋው ሰለባ ቤተሰቦችን ከኣደጋው የተረፉትን ከከተማው ሊቀ ጳጳስ ጢሞቲ ዶላን ጋር በመሆን ኣግኝተው ስለነበረ ይህም እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ ከፉፏቴው የሚወጣው ድምጽ ካልሆነ በስተቀር ይህም የዝምታ ጉብኝት ነበር።

ኃይማኖቶች የሰላም, የፍትህ እና የማስታረቅ ኃይልዎች ናቸው

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ እነዚህን የኣደጋ ሰለባዎች በማስታወስና እንደዚህ ካሉ ምሳሌኣዊ ቦታዎች የሁሉም ሃይማኖት ተከታዮች ለሰላምና የእግዚኣብሔርን ሥም ለጦርነት ወይም ላልተፈለገ ነገር እንዳያውሉ መልዕክት ኣስተላልፈዋል። በር.ሊ.ጳ. ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ 2ኛ ተጀምሮና በየዓመቱ በሁሉም የሃይማኖት ኣባቶች ስለ ሰላም ይደረግ የነበረው የኣሲዚው ጸሎት ይበልጥ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት በዚሁ ጊዜ ተወስቷል።

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ከሙስሊሙ ኢማምና ከኣይሁዱ ራቢ ጋር ኣሸባሪነትንና ጦርነትን በተመለከተ ጸሎት ኣድርገዋል። እንዲሁም የሂንዱ፣ የቡዲስት የክርስቲያንና የሙስሊም ስለ ሰላም ኣጠር ያለ ጸሎት ኣድርገዋል እንዲሁም የዕብራዊው ሃይማኖት መሪ ስለ ሞቱት የጸለየ ሲሆን ። በስተመጨረሻም ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ሲናገሩ የእኛ ሁላችን እዚህ በኣንድነት መገኘት በዓለም በኣራቱም ኣቅጣጫ ለሚገኙ የሰው ልጆች ሰላምንና ፍትህን እንዲሁም እርቅን ለመገንባት ትልቅ ምልክትና ኃይል ነው ብለው ጥላቻን በቀልንና ክፋትን ለማስወገድ ጥረት እንዲደረግ በመጥቀስ በዚህ መልኩ ብቻ ወደ ፈጣሪ የሰላም መሳሪያዎች ኣድርገን ብለን መጸለይ እንችላለን ብለው ደምድመዋል።

11 September 2018, 18:25