ፈልግ

2018.09.16 Angelus Domini 2018.09.16 Angelus Domini 

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዓል ተከበረ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ አባ ግርማቸው ተስፋዬ - ቫቲካን፣

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ በተናንትናው ዕለት በሮማ ቅዱስ ጴጥሮስ ኣደባባይ ለተሰበሰበው ሕዝብ በዕለቱ በተነበበው ወንጌል ላይ ኣጠር ያለ ትንታኔ ከሰጡና መልኣከ እግዚኣብሔር ካደረሱ በኃላ ከትላንትና ወዲያ በሎሬቶ በሓዋርያዊ መንበር ሥር ባለች የቅድስት ቤት ቤተክርስቲያን ውስጥ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም የልደት በዓል በታላቅ ድምቅት መከበሩንና በዚሁም የበዓል ኣከባበር ላይ በዓለም ላይ ለሚገኙ ቤተሰቦች ሁሉ መንፈሳዊነት ጸሎት መደረጉን ኣውስተው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ቤት የቤተሰብ ቤት መሆኑን ተናግረዋል።

በመቀጠልም በዚሁ በዓል ለተሳተፉትና በተለያየ ሁኔታ ለበዓሉ መሳካት የተለያየ ኣገልግሎት ላበረከቱት ሁሉ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ጥበቃ እንዳይለያቸው ተማጥነዋል ።

በመቀጠልም በተናንትናው ዕለት በስትራስቡርግ የአልፎንሳ ማርያ ኢ ፒንገር የቅዱስ አዳኝ እህቶች ማኅበር መሥራች የብፅእና በዓል በታላቅ ድምቀት መከበሩን ገልፀው ስለዚች ታታሪና ጥበበኛ ሴት በተለይም በመንፈሳዊና ሥጋዊ ሕመም ለሚሰቃዩት ሥቃይን በዝምታና በጸሎት ውስጥ በማሰብ የእግዚአብሔርን ፍቅር በመመስከር ምሳሌ ስለሆነችና ስላደረገችው መልካም ሥራ ሁሉ ለእግዚአብሔርን ምስጋና እናቀርባለን ብለዋል። ለዝች ለኣዲሲቷ ብጽእት ለአልፎንሳ ማርያ ኢ ፒንገር የተሰበሰበው ሕዝብ ሁሉ በጭብጨባ ኣጋርንቱንና ደስታውን ገልጿል።

በመጨረሻም ልባዊ ሰላምታቸውን በሮማ እና ከኣካባቢው ለመጡ ምዕመናን እንዲሁም ከተለያዩ ቦታዎች ለተሰበሰቡ ነጋዲያንና ቤተሰቦች ሰበካ ቡድኖችና ማህበራት ከኮሞ ሃገረ ስብከት ለመጡ ሕዝበ እግዚኣብሔርና ወጣቶችና እንዲሁም ቤተክርስቲያ በምታዘጋጃቸው የተለያዩ ስብሰባዎች ላይ በንቃት ተሳታፊ የሆኑትን ሁሉ ኣመስግነው ለተሰበሰበው ሕዝብ ሁሉ መልካም ምሳ ተመኝተው ተሰናብተዋል።

09 September 2018, 18:42