ፈልግ

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ “ማመን ማለት በሕይወት መካከል እውነተኛ ፍቅርን ማስቀደም ነው”።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በትናንትናው ዕለት እሑድ መስከረም 6 ቀን 2011 ዓ. ም. በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ላይ ለተሰበሰቡት ምዕመናንና የሃገር ጎብኝዎች በዕለቱ ከማርቆስ ወንጌል ምዕ. 8፤ 27-35 ተውስዶ በተነበበው ቅዱስ ወንጌል ላይ ተመርኩዘው አስተንትኖ “ማመን ማለት በሕይወት መካከል እውነተኛ ፍቅርን ማስቀደም ነው” ማለታቸው ታውቋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ያደረጉትን አስተንትኖ ሙሉ ይዘት እንደሚከተለው ቀርቧል።   

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ አባ ግርማቸው ተስፋዬ - ቫቲካን

“በክርስቶስ የተወደዳችሁ ወንድሞቼና እህቶቼ

በዛሬው ዕለት ያዳመጠነው የማርቆስ ወንጌል 8, 27-35 ያለዉን ሲሆን በኣጠቃላይ ወንጌሉ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ማን አንደሆነ ወይ ስለ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ማንነት ላይ የሚያጠነጥን ወንጌል ነው። ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ይህንን ሰዎች ማን ይሉኛል የሚለውን ተመሳሳይ ጥያቄ በስተመጨረሻ ላይ ለራሱ ሓዋርያቶችም ላይ ኣቅርቦላቸው ነበር ምክንያቱም ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ማነው የሚለዉን ነገር በደንብ እንዲያውቁና እንዲረዱ ስለፈለገ ነው።

ይህ ሰዎች ማን ይሉኛል የሚለው የጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ጥያቄ ወደ ሓዋርያቶቹ ከመምጣቱ በፊት ሌሎች ሰዎች ስለ እርሱ ምን እንደሚሉ ከሓዋርያቶቹ ለመስማት ፈልጎ ሰዎች ስለ እኔ ምን ይላሉ ብሎ በቁጥር 27 ላይ እንደተገለፀው ጠየቃቸው። በእርግጥ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ሓዋርያቶቹን ሰዎች ስለ እርሱ ምን እንድሚያስቡ ይጠይቅ እንጂ ሓዋርያቶችም ሆኑ ሕዝቡ እንደ ኣንድ ትልቅ ነቢይ እንሚያዩት እንደሚቆጥሩት ያውቃል።

ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ሕዝቡ ስለእርሱ የሚሰጠው መልስም ሆነ ሓዋርያቶች በተለያዩ የቅዱስ መጽሓፍ መጻሕፍት ላይ የተጠቀሱትን ታላላቅ ሰዎችን ሥም በመጥቀስ ሰዎች እንዲህ ያስቡሃል እንዲህ ይሉሃል የሚሉት ሁሉ ለእርሱ ምንም ማለት ኣልነበሩም። በጌታችን እየሱስ ክርስቶስ እይታ በኣንድ ቀመር ውስጥ ብቻ የታጠረ እምነት የቅርቡን ብቻ እንጂ ከዛ ወጣ ያለ የወደፊቱን ወይ የሩቁን የመመልከት ኣቅሙ የደከመ ስለሚሆን ነገሮችን ሰፋ ኣድርጎ ነገሮችን ዘርዘር ኣድርጎ የመመልከቱ ኣቅሙ እጅግ ውሱን ነው።

ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ የዛሬዉም ሆነ የነገው ሁሉም የእርሱ ተከታዮች ከእርሱ ጋር የጠበቀና ግላዊ የሆነ ግንኙነት እንዲኖራቸው ይፈልጋል። ይህንን ካደረጉ ብቻ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ በእነርሱ ሕይወት ውስጥ ዋናውና ትልቁ ቁምነገር ይሆናል በሕይወታቸውም ውስጥ ይነግሳል። ለዚህም ነው ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ በእውነተኛ ሁኔታ እርሱ በእነርሱ ሕይወት ውስጥ ምን ቦታ እንዳለው እራሳቸውን እንዲገመግሙና ኣንዲረዱ በማሰብ እናንተስ ስለእኔ ማንነት ምን ትላላችሁ ብሎ የጠየቃቸው።

ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ዛሬም ተመሳሳይ ጥያቄ ለእያንዳዳችን ኣንተ ኣንቺ ስለ እኔ ማንነት ምን ትላላችሁ እያለ ይጠይቀናል። እኔ ለኣንተ ለኣንቺ ማን ነኝ? እያለ ይጠይቀናል። እያንዳዳችን እግዚኣብሔር የእርሱን ልጅ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስን እንድናዉቅ በሰጠን ጸጋና ብርሃን በመመራት ከልባችን ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ለእኔ ማን እንደሆነ መመለስ ይገባኛል። ምናልባት በመንፈስ ተሞልተን ልክ እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ ኣንተ ክርስቶስ ነህ ብለን እንድንመልስ በውስጣችን ያለ የእግዚኣብሄር መንፈስ ሊመራን ይችላል። ጌታችን እየሱስ

ክርስቶስ ለሓዋርያቶቹ የተናገራቸውን ቃል ለእኛ በሚናገረን ጊዜ ማለትም የእርሱ የጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ተልዕኮ የሚፈፀመው በሰፊዉና ብዙ ስኬት ባለበት የዓለም መንገድ ሳይሆን ልክ ቅዱስ ጴጥሮስ እንደደረሰበትና የተሰቃየው የተናቀው በሰዎች ዘንድ ተቀባይነት ያጣውና በመጨረሻም የተሰቀለው ደጉ ኣገልጋይ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ በተጓዘበትና ኣስቸጋሪ በሆነው ኣቅጣጫ እንድንጓዝ ልንጠየቅ እንችል ይሆናል። ወይም ደግሞ ሁሌም የዓለምን እንጂ የመንፈሳዊነትን መንገድ በማያሳስበው ኣቅጣጫ እንድንጓዝ ልንጠየቅ እንችል ይሆናል። በዛን ጊዜ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ጴጥሮስን እንደገሰፀው እኛም በጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ኣንተ ሰይጣን ወደኃላ ሂድ ኣንተ የሰውን እንጂ የእግዚኣብሔርን ነገር ኣታስብም በማለት ልንገሰጽ እንችል ይሆናል።

በክርስቶስ የተወደዳችሁ ወድሞቼና እህቶቼ በጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለን እምነት በቃላትና በኣፍ ላይ የተመሠረተ ብቻ ሳይሆን በእውነተኛነት እና በእርግጠኛነት ላይ የተመሠረተ ሊሆን ይገባል። በእግዚኣብሔር እውነተኛ ፍቅር የታተመ ሊሆን ይገባል። በኣንድ ትልቅና ለወንድም እህቱ ትልቅ ፍቅር ያለው እምነት ላይ ሊመሠረት ይገባል። ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ እንደሚለን እርሱን ለመከተል የእርሱ ደቀመዛሙርት ለመሆን ራስን መካድ ማለትም ራስወዳድነትንና ኩራትን ያለእኔ ማን ኣለ ባይነትን ኣውልቀን በመጣል መስቀልን መሸከም ያስፈልጋል።

ከዚህ በመቀጠል ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ኣንድ ትዕዛዝ ወይንም ኣንድ ሕግ ይሰጠናል ይኸውም የራሱን ሕይወት ለማዳን የሚፈልግ ሁሉ ያጠፋታል ይለናል። ኣብዛኛዉን ጊዜ በተለያዩ ምክያቶች ከመንገዳችን እንሳሳታለን በነገሮች ሁሉ ላይ የተሳሳተም ቢሆን ቀለል ያሉትን መንገዶች እንመርጣለን ወይንም ደግሞ ሰዎችን እንደሚገባቸው ዓይነት ክብር ኣንሰጣቸውም በእነዚህ ሁሉ ላይ ግን እውነተኛ ፍቅር ኣናገኝም እውነተኛ ደስታንም ኣናገኝም። እውነተኛ ፍቅር ወይንም እውነተኛ ደስታ የሚገኘው በጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ያለውን እውነተኛ ፍቅር ወይንም እውነተኛ ደስታ ስናገኝና ወደ ውስጣችን ገብቶ ሲቀይረን ሲለውጠን ብቻ ነው። ፍቅር ሁሉንም የመለወጥ ሁሉንም የመቀየር ኃይል ኣለው ፍቅር እኛን እያንዳዳችንን የመቀየር ኃይል ኣለው ስለዝህ ራሳችንን ለፍቅር ተገዢ እናድርግ። ይህንንም ሁኔታ ቅዱሳኖች በተሞክሮኣቸው ያረጋግጡልናል ባሳለፉት ሕይወት ይመሰክሩልናል።

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ኣንድ ልጇን ጌታችን እየሱስ ክርስቶስን በመከተል እምነቷን በታማኝነት እንደጠበቀች እኛም በእርሷ መንገድ እንድንጓዝና ይህም ሕይወታችን ለእኛ ብቻ ሳይሆን በጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ለወንድም እህቶቻችን ሁሉ መሆኑን እንድንረዳ የእርሷንም ኣብነት ተከትለን ወደፊት ለመጓዝ እንድንችል ታድርገን”።

16 September 2018, 17:26