ፈልግ

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ የደቡብ ኢጣሊያ ግዛት በሆነችው በሲሲሊያ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸውን አካሂደዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ አባ ግርማቸው ተስፋዬ - ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳስት ፍራንችስኮስ የደቡብ ኢጣሊያ ግዛት በሆነችው በሲሲሊያ ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማድረግ ወደዚያው መጓዛቸው ታውቋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳስት ፍራንችስኮስ በኢጣሊያ ውስጥ የሚያደርጉትን ሐዋርያዊ ጉብኝት ቀጥለው ቅዳሜ መስከረም 5 ቀን 2011 ዓ. ም. ጠዋት በማለዳ ከቫቲካን ከተማ ተነስተው በደቡብ ኢጣሊያ ወደምትገኝ ወደ ሲሲሊያ ደሴት ተጉዘዋል። የቅዱስነታቸው ሐዋርያዊ ጉብኝት ዓላማ  ከ25 ዓመት በፊት በፓለርሞ ከተማ ውስጥ በማፊያ እጅ ለተገደሉት ለብጹዕ አባ ጁሰፔ ፑሊሲ መታሰቢያ በሚደረገው መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ለመገኘት እንደሆነ ታውቋል። ቅዱስነታቸው በሲጎነላ አውሮፕላን ጣቢያ ሲደርሱ የሃገረ ስብከቱ ብጹዓን ጳጳሳትና ከፍተኛ የመንግሥት ተውካዮች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ቅዱስነታቸው በአውሮፕላን ጣቢያ ከተደረገላቸው የአቀባበል ስነ ስርዓት በኋላ ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ላይ በቅድሚያ ወደ አርመሪና አደባባይ በመሄድ በሥፍራው ይጠብቋቸው ለነበሩት ከአርባ ሺ በላይ ምዕመናን ሰላምታ ካቀረቡ በኋላ መልዕክት ኣስተላልፈዋል። የመልዕክታቸውን ይዘት ተርጉመን እንደሚከተለው ኣቅርበነዋል።

“በክርስቶስ የተወደዳችሁ ወንድሞቼና እህቶቼ

በቅድሚያ በመካከላችሁ ስለተገኝሁ እግዚኣብሔርን እያመሰገንኩ ስለተደረገልኝ ደማቅ ኣቀባበል ሞንሲኞር ሮሳሪኦ ጂሳናን የኣካባቢውን ከንቲባና ሌሎች የኣካባቢው ባለሥልጣናት እንዲሁም በዚህ ጉብኝት ዙሪያ ለተሳተፋችሁ ሁሉ የከበረ ሰላምታዬ አቀርባለሁ።

በፒያሳ አርሜሪና የምትገኘው ቤተክርስቲያን በትልቅ ተስፋና ደስታ በኣካባቢው ላይ ስላሉ የተለያዩ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ለመግታት እያሳየች ያለዉን ከፍተኛ ተነሳሽነትና እገዛ ላመሰግን እወዳለሁ። በእርግጥ እየተፈታተኗችሁ ያሉት ችግሮች ጥቂት ኣይባሉም ኣንዳንዶቹንም ለመዘርዘር ያህል: ማህበራዊና ባህላዊ እሴቶች ኣለመዳበር የሠራተኛ ጉልበት ብዝበዛ ለወጣቶች ክብር ያለው ሥራ አለመኖር የቤተሰቡ ፍልሰት የኣራጣ ኣበዳሪዎች መስፋፋት የአልኮል ሱሰኝነት እና ሌሎች ሱሶች ቁማር በቤተሰብ መካከል ያለ ትስስር እና መጠቃቀም እና የመሳሰሉት ይገኙበታል።

በእነዚህና በመሳሰሉት ብዙ ሥቃዮች ኣማካኝነት የቤተ ክርስቲያኒቱ ማህበረሰብ ወይም ምዕመናኑ አንዳንድ ጊዜ የጠፉ እና የደከመው ሊመስለው ይችል ይሆናል ነገር ለእግዚኣብሔር ምስጋና ይግባውና በጥሩ መንፈስ ወደፊት ሁሉም እንደሚሻሻል በማመን ሕዝቡ እየተንቀሳቀሰ ሕይወቱንም እየመራ ይገኛል። በተለይም ደግሞ በእምነታቸው ላይ መጥፎ ጠባሳና ኣለመተማመን ለሚታይባቸው ወድሞችና እህቶች የሚያደርገው ወንድማዊ ኣዘኔታና እገዛ እጅግ ሊመሰገን የሚገባው ጉዳይ ነው።

የህብረተሰቡ እና የቤተክርስቲያን ቁስሎች መፈወስ የተሳሳተና እና አፍራሽ ድርጊት አይደለም ለእምነታችን ጥብቅና ለመስጠት ከፈለግን በእነዚህ የሰው ልጆች መከራዎች ውስጥ የጌታን ቁስሎች ማስተዋልን መማር አለብን። እነሱን ማየት እነሱን መንካት(ዮሐ 20፣ 27) ለእኛ ለክርስቲያኖች ትልቅ ትርጉም ኣለው። ይኸውም የጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ታሪክና ክቡር ሥጋው የድኅንነታችንና የመዳኛችን ቦታ መሆኑን ይገልጻል።

ስለዚህም ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ በዚህ ኣካባቢ ያለውን ችግርና ሰቆቃ በተሳካ መልኩ ለመፍታትና ለመቅረፍ ኣዲስ ተነሳሽነትና ጠንካራ እምነት እንዲኖራችሁ ምክሬን ኣስተላልፋለሁ።

የሃገረ ስብከታችሁን ምሥረታ ሁለት መቶኛ ዓመት ካከበራችሁ በኃላ አንድ አስደናቂ ተግባር ይጠብቃችኋል ይኸውም የሥምምነት ቤተክርስቲያንን ገጽታና ቃል ማደስ የቤተክርስትያን የወንጌል ተልእኮን በፍቅር ማስፋፋት እንዲሁም በቤተክርስቲያን የቅዱስ ቁርባን ማህበረሰብ በሚሉ ጉዳዮች ዙሪያ መንቀሳቀስ እና የበለጠ መሥራት ይጠበቅባችኋል።

የኣንድ ሲኖዶሳዊ ቤተክርስቲያን ኣመለካከትና የእግዚኣብሔር ቃል ሁለቱንም በሚገባ ማዳመጥና መረዳት ይስፈልጋል። በተለይም የእግዚኣብሔር ቃል ላይ የበለጥ ትኩረት ሊደረግ ይገባል። ከምንም ነገር የበለጠ የሆነውን የእግዚኣብሄርን ቃል እንጂ ሌለ ምንም ነገር በክርስቲያኑ ማኅበረሰብ ውስጥ ኣታስቀምጡ ነገር ግን ከሁሉ ባላይ ይህን የእግዚኣብሔርን መልኮታዊ ቃል የራሳችሁ በማድረግ ከጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ጋር ልብ በልብ ተገናኙበት በክርስቶስም ላይ እረፉበት።

የእግዚአብሔር ቃል እና ሲኖዶሳዊ ሕብረት ልክ በተስፋ የሚኖርና ተስፋ ባጣ ሕዝብ መካከል እግዚኣብሔርን ለመለመን የተዘረጉ እጆች ሲሆኑ ለእነዚህ በአካልና በመንፈስ ተሸንፈው ላሉ እጆች መድረስ ያስፈልጋል። ይህንን ተልዕኮ ለመፈጸም ሁልጊዜ በጴንጤቆስጤ እሳት የተሞላው የመጀመሪው የክርስቲያን ማኅበረሰብ ወደ ፈጣሪው በድፍረት ምስክር በመሆን ያሳለፈውን የመጀመሪያውን መንፈስ ማሳወቅ አስፈላጊ ነው። የተወደዳችሁ ወንድሞቼና እህቶቼ በእምነት ወደ ውስጥ በመግባት ትክክለኛ የሆነ ምርጫና ውሳኔ ማድረግ በሕይወታችሁ ለሚኖራችሁ ደስታና የኣካባቢያችሁ ማኅበረሰብ ዕድገት ወሳኝ ነው።

የርህራሄ ወይም የፍቅር ቤተክርስትያን ለመሆን ዛሬ በሁሉም አቅጣጫ ትኩረት ለሚጠይቀው ለፍቅር አገልግሎት ልዩ የሆነ ቦታ ሊሰጠው ይገባል።ቀሳውስት ዲያቆኖች የተቀደሱ ሰዎች እንዲሁም በተለያዩ ማኅበራትና በግልም የሚኖሩ ሕይወታቸውን ለልዩ ኣገልግሎት የሰጡ ሰዎች ከተለያዩ ሰዎች የሚመጣዉን ክፋትና ኣላስፈላጊ ነገር ስለ እግዚኣብሔር ፍቅር ሲሉ ይቅር ማለትና ሰዎቹን ማገዝ ወደ ትክክለኛ መንገድ እንዲመጡ መርዳት ያስፈልጋል። በትልቅ ትህትና ወደ ውጪ ወደ መስቀለኛ መንገድ ወደ ዕረፍት ቦታ በመሔድ ሕይወት ኣስቸጋሪና ሁሌም በጥቁር መጋረጃ የተጋረደች ሳትሆን ሕይወት በእግዚኣብሔርን መልካም ፈቃድና በሰዎች መልካም ወንድማማችነት ውስጥ ያለች መሆኗን መስበክ ያስፈልጋል።

በቁምስናዎችና በተለያዩ የኅብረተሰቡ ክፍል ወንጌላዊ ፍቅር ወንድማዊ መተሳሰብና ከዓለማዊ ክፉ ወጥመድ ራስን መቆጠብ ኣስፈላጊ ነው። በቤተክርስቲያን ውስጥ ሰለምታካሂዱት በተለያዩ የካቶሊክም ሆሉ የሌላ የእርዳታ ድርጅቶች ስለምታሳዩት ትብብር ለምትመግቧቸዉና ለምታስጠልሏቸው ችግረኞች ስደተኛው እየሱስን በቤታችሁ የምትቀበሉት ሽማግሌውንና ተስፋ የቆረጠዉን ፍቅርና ተስፋ የምትሰጡትን ሁሉ እጅግ ኣድርጌ ኣበረታታለሁ አንድትቀጥሉበትም ኣደራ እላለሁ። ከርስቲያናዊ ማኅበረሰብ በየትኛዉም ቦታ በሚፈጠሩ ችግሮችና ተስፋ በቆረጡ ሰዎች ዉስጥ የእነሱ የችግራቸው ተካፋይ በመሆን በቻሉት ሁሉ ከጎነቸው ይቆማሉ ለችግሮቻጨዉም ኣብረው መፍትሄ ይፈልጋሉ።

አንዱ የተልዕኮ የበጎ አድራጎት ገጽታ ለወጣቶች እና ለችግሮቻቸው ትኩረት ይሰጣል። እዚህ እንደምመለከተው ብዙ ኣዳጊዎችና ወጣቶች በታላቅ ተስፋ ተሞልተው ኣደባባዩን ሞልተው ኣያለሁ ወድ ወንዲሞቼና እህቶቼ በዓላማችሁና በሕይወታችሁ ደስተኛ ሁኑ ምክንያቱም ጌታችን እየሱስ ክረስቶስ ይወዳችኋል እሱ ሁሌ ታማኝና ደግ ስለሆነ በፍጹም ኣይተዋችሁም እምነታችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ማሳደር ትችልላችሁ በችግርም ጊዜ ይሁን በጥርጣሬ ጊዜ በእርሱ እርዳታ ላይ መመርኮዝ ትችላላችሁ። እንዲሁም

ሁል ጊዜ ከጎናችሁ በምትቆም ቅድስት ቤተክርስቲያንም ላይ እምነታችሁን ኣሳድሩ ምክንያቱም በሁሉ መንገድ ወደ እናንተ በመቅረብ በዕለታዊ ችግሮቻችሁ ሁሉ ከእናንተ ጋር ነች የጸሎትን መንፈስ እንድትረዱ ከእግዚኣብሄር ጋር የጠበቀ ህብረት እንዲኖራችሁ ልባችሁም ወደ ቅድስና እንዲያቀና ታግዛችኋለች።

ሦስተኛው ሓሳብ የማቀርብላችሁ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ቁርባን ማኅበረሰብ የሚለዉን ሓሳብ ነው። በቅዱስ ቁርባን ውስጥ ይምናገኝዉን የክርስቶስን ፍቅር ወደ ዓለም በመዉሰድ ለወንድሞቻችንንና እህቶቻችን እንሰጣለን። ይህ ትልቁ ምስጢር ነው በጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ኣማካኝነት የእግዚኣብሔር ፈት በእኛ ላይ እንዲያበራ የእርሱ ፍቅር ፍቅር በጎደላቸው ላይ እንዲሞላ ሁሉንም ነገር በእግዚኣብሔር ፊት እናቀርባለን። በቅዳሴ መሳተፍን በተመልከተ በተለይ የእሑድን ቅዳሴ በሚገባ መሳተፍ ያስፈልጋል። የተራራዉን ስብከት በሕይወታችን መኖር ያስፈልጋል እንደ ትንሿ የሰናፍጭ ዘር እንደ ኣንድ እፍኝ እርሾ እንደማይጠፋው እሳት መሆን ያስፈልጋል እንድ ምድር ጨው መሆን ያስፈልጋል።

ቅዱስ ቁርባንና የክህነት ስልጣን የማይነጣጠሉ ናቸው ካህኑ የቅዱስ ቁርባን ሰው ነው። ለካህናት ወድሞቼ ሁልጊዜ ከጳጳሳችሁ ጋርና እርስበርሳችሁ የጠበቀ ግንኙነት ይኑራችሁ። ወድ ካህናቶች በትህትና ላይ የተመሠረተ ደስተኛ የሆነ ካህናዊ ቤተሰብ መመሥረት እርስ በእርስ መረዳዳትና መፈቃቀርር ኣብሮ መሥራት ምንኛ ደስ የሚል ነገር ነው።

በእግዚኣብሔር ሕዝብ ፊት እመክራችኋለሁ እናንተ እርስ በእርስ በሚደረግ መከፋፈልና መወነጃጀል ዙሪያ ራሳችሁን በማራቅ ለምዕመናን የመጀመሪያ ምስክርና ምሳሌ ልትሆኑ ይገባል። በመንፈስ ቅዱስ ኣማካኝነት በተሰጣችሁ ጸጋ በዚህ ምድር ላይ በሚከሰተው ነገር ሁሉ ትልቅ ትህትና በማሳየት እንድተተባበሩና ሕዝቡም በሁሉም ረገድ እውነተኛ ነፃነት እንዲሰማው ኣድርጉ። ከእግዚኣብሔር ባገኛችሁት መጽናናት ያዘኑትን ሁሉ በማጽናናት የሚያለቅሱትን እንባ በማድረቅ በሃዘንና በችግር የቆሰሉትን ቁስሎች በመፈወስ እንድታገለግሏቸውና በኣደራ የተሰጣችሁን ሕዝበ እግዚኣብሔር ሕይወት በሚገባ እንድትገነቡ ኣደራ።

የተከበራችሁ ወንድሞችና እህቶች ትንሽ ጊዜ አብሬኣችሁ ብቆይ መልካም ነበር። በእናንተም በልባችሁ ውስጥ ያለው እምነት እና ተስፋ ምን ያሀል ጠንካራ መሆኑ በውስጤ ይሰማኛል ነገር ግን ወደ ፓሌርሞ መሄድ ይገባኛል ብዙ ሰዎችም ይጠብቁኛል በዛም በሰማዕትነት የሞተዉን ካህን ፒኖ ፑሊሲን የክብር ማስታወሻ ቅዳሴ እናደርጋለን። እሱ ከመሞቱ በፊት በዚህ በፒያሳ ኣርሜሪና ትንሽ ጊዜ ማሳለፉንና በዛን ጊዜም ሴሚናሪስቶችን እንዲሁም የፓሌርሞን ዓብይ ዘርዐ ክህነት ተማሪዎችን ሲመክርና ሲያበረታታ እንደነበር ኣውቄኣለሁ።

በመጨረሻም በፒያሳው የተሰበሰበውን ሕዝብ ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ኣደራ ሰተው ሕዝቡን ባርከው ወደ ፓሌርሞ ጉዞኣቸውን ቀጥለዋል”።

15 September 2018, 18:14