ፈልግ

ር.ሊ.ጳ. ፍራንችስኮስ ቅዳሜ መስከረም 5/2011 ዓ. ም. በሲሲሊያ ሓዋርያዊ ጉብኝት ኣደረጉ።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳስት ፍራንችስኮስ የደቡብ ኢጣሊያ ግዛት በሆነችው በሲሲሊያ ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማድረግ ወደዚያው መጓዛቸው ታውቋል። የቅዱስነታቸው ሐዋርያዊ ጉብኝት ዓላማ ከ25 ዓመት በፊት በፓለርሞ ከተማ ውስጥ በማፊያ እጅ ለተገደሉት ለብጹዕ አባ ጁሰፔ ፑሊሲ መታሰቢያ በሚደረገው መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ለመገኘት እንደሆነ ታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ አባ ግርማቸው ተስፋዬ - ቫቲካን

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቺስኮስ ዛሬ ማለትም መስከረም 15 ቀን 2018 እ.ኣ.ኣ. ሲቺሊያ ውስጥ ካታኛ እንዲሁም ፓሌርሞ በሚባሉ ቦታዎች ሓርያዊ ጉብኝት ኣድርገዋል ። በተለይም በፓሌርሞ ያደረጉት ጉብኝት ከ 25 ዓመት በፊት የተገደሉትን ኣባ ፒኖ ፑሊሲን ለመዘከር በሚደረገው የቅዳሴ ሥነ ሥርዐት ላይ ተሳትፈዋል።

በመሥዋተ ቅዳሴዉም ላይ እግዚኣብሄር ዛሬ በኣሸናፊነትም በተሸናፊነትም ውስጥ እንድሚናገር ጠቅሰው እግዚኣብሔር ለሰው ልጅ የሰጠው ትልቁ ሥጦታ ሕይወት መሆኑን ኣስረድተዋል። በመቀጠልም እግዚኣብሔር ለሰው ልጅ የሰጠውን ይህን ሕይወት በደንብ መጠበቅና መንከባከብ እንደሚያስፈልግ ኣስረድተው ሕይወቱን ስለ ራሱ ብቻ የሚኖርና ስለ ራሱ ብቻ የሚያስብ ሕይወቱን ያጠፋታል ብለዋል።

እሳቸው እንዳስረዱት ሕይወቱን በራሱ ዙሪያ ብቻ የሚኖር ሰው በሚያገኘው ስኬትና ሓብት በዚህ ዓለም ኣስተሳሰብ ኣሸናፊ መስሎ ቢታይም ይህ ኣላፊና ጊዜኣዊ ነው ብለውል። በዚሁ መሥዋተ ቅዳሴ ከፍቅርና ከራስ ወዳድነት ኣንዱን መምረጥ እንደሚያፈልግና ገንዘብና ሥልጣን ሰውን ወደ ባርነት እንጂ ወደ ነፃነት ኣይወስዱትም ብለዋል። ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ በመቀጠል ዛሬ አዚህ የተሰበሰብን ሁላችን ከየትኛው ወገን መሆናችንን መምረጥ ያስፈልጋል ።ሕይወትን ስለ ክርስቶስ ብሎ መስጠት ወይስ ለራስ ብጫ መኖር ከሁለቱ ኣንዱን መምረጥ ግድ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

በመጨረሻም በሰማዕትነት የተገደሉጥ ኣባ ፒኖ በዚህ በተወለዱበት ኣካባቢ ከድሆች ጋር ኣብሮ ድህነትን የኖሩና ስለ ክርስቶስ ሲሉ ሕይወታቸውን የሰጡ መሆኑን ገልጸው በመቃብራቸውም ላይ የተፃፈዉን ቃል ማለትም ራስን ለሰው ኣሳልፎ ከመስጠት የበለጠ ፍቅር የለም የሚለዉን የክርስቶስን ቃል በማስታወስ ይህን ኣባ ፒኖ በህይወታቸው ፈጽመውታል እኛም እንግዲህ ኣንድሱ ተክክለኛዉን እንምረጥ ብለው ደምድመዋል።

15 September 2018, 18:45