ፈልግ

viaggio apostolico in Estonia,Lettonia e Lituania 2018 viaggio apostolico in Estonia,Lettonia e Lituania 2018 

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ ወደ ባልቲክ ሃገሮች ሓዋርያዊ ጉብኝት ለማድረግ እንደሚሄዱ ታወቀ።

ከመስከረም 22 እስከ 25 2018 ዓ.ም. እ.አ.አ. የሚቆየው የር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ 25ኛ ሓዋርያዊ ጉዞ ሊቷኒኣ ሌቶኒኣ እና ኤስቶኒኣ መሆኑንና ይህም ሓዋርያዊ ጉብኝት በተለያየ ምክንያት ለተሰቃዪትና ተስፋ ለቆረጡት ሰዎች መጽናኛና ብሩህ ተስፋ እንድሚሆንላቸው የተገለጸ ሲሆን ከዚህ ጋር ኣያይዘውም የቅድስት መንበር ፕሬስ ጽ/ቤት ዲሬክተር የሆኑት ግሬግ ቡርኬ ይህ 25ኛ የር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ሓዋርያዊ ጉዞ ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ሁለተኛ በባልቲክ ሃገሮች ላይ ያደረጉትን 25ኛ ጉዞ በማስታወስ ነው።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ አባ ግርማቸው ተስፋዬ - ቫቲካን

የቅድስት መንበር የሕትመት ቢሮ ኃላፊ ግሬክ ቡርኬ ለአጭር ሰዓት ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቆይታ ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ በሦስት የሰሜን ኣውሮፓ ኣገራት ሓዋርያዊ ጉብኝት እንድሚያደርጉ መግለጻቸውን የቫቲካን ከተማ የሬዲዮ ኣገልግሎት ባልደረባ አሜዲኦ ሎሞናኮን ዋቢ በማድረግ ጠቅሷል።

ይህ ለዐራት ቀናት ማለትም ከመስከረም 22 እስከ 25 2018 ዓ.ም. እ.አ.አ. የሚቆየው የር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ 25ኛ ሓዋርያዊ ጉዞ ሊቷኒኣ ሌቶኒኣ እና ኤስቶኒኣ መሆኑንና ይህም ሓዋርያዊ ጉብኝት በተለያየ ምክንያት ለተሰቃዪትና ተስፋ ለቆረጡት ሰዎች መጽናኛና ብሩህ ተስፋ እንድሚሆንላቸው የተገለጸ ሲሆን ከዚህ ጋር ኣያይዘውም የቅድስት መንበር ፕሬስ ጽ/ቤት ዲሬክተር የሆኑት ግሬግ ቡርኬ ይህ 25ኛ የር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ሓዋርያዊ ጉዞ ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ሁለተኛ በባልቲክ ሃገሮች ላይ ያደረጉትን 25ኛ ጉዞ በማስታወስ ነው።

ቅርብ ነገር ግን በጣም የተለያዩ ሓገራት

የቅድስት መንበር ፕሬስ ጽ/ቤት ዲሬክተር የሆኑት ግሬግ ቡርኬ ለቫቲካን የዜና ኣገልግሎት ኣያይዘው እንዳስረዱት እነዚህ የባልቲክ ሃገሮች ከሞላ ጎደል ስንመለከታቸው ኣንድ ይመስላሉ ነገር ግን ኣንዳንድ ጊዜ እህትማማቾም በመልክ በጣም እንድሚለያዩት ሁሉ እነዚህም ሃገራት ኣንድ ቢመስሉም በመሓከላቸው ግን ልዩነት ኣለ ይላሉ። እንደ የቅድስት መንበር ፕሬስ ጽ/ቤት ዲሬክተር ግሬግ ቡርኬ ኣገላለፅ በሊቷአኒኣ አብዛኛው ሕዝብ ማለትም ወደ 80% የሚሆነው የካቶሊክ እምነት ተከታይ ነው ብለዋል።

በሌቶኒኣ ኣብዛኛው ሰው የሉተራን እምነት ተከታይ ሲሆን የሌቶኒኣ እና የሩሲያ ሕዝብ ተደባልቆ የሚኖርበት ቦታ ነው። በኤስቶኒኣ ግን 75% የሚሆነው ሕዝብ ምንም ዓይነት እምነት የላቸውም። በመቀጠልም የቅድስት መንበር ፕሬስ ጽ/ቤት ዲሬክተር የሆኑት ግሬግ ቡርኬ ለር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ከበድ ያለ ቢሆንም ኣስደሳች ጉዞ እንደሚሆን እገምታለሁ ብለው በኤስቶኒኣ ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ወደ ኣምሥት ሺህ 5000 የሚጠጋ የካቶሊክ ኅብረተሰብ ጋር እንደሚገናኙና እንደሚወያዩ ኣስረድተዋል።

ታሪካዊ ጉዞ

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ በሚያደርጉት በዚህ ታሪካው ጉዞ በተለይም በመስከረም 23 ቀን 2018 ዓ.ም. እ.አ.አ. በቪልኒዩስ ሊቱዌኒያ የሙያ እና የነፃነት ውጊያ ሙዚየም የሚያደርጉት ጉብኝት ትልቅ ቦታ ከተሰጡት መካከል ኣንዱ ሲሆን በዛም በተለያዩ ሰው ሰራሽና የተፈትሮ ኣደጋ ሰለባ ለሆኑት በተሰራው የመታሰቢያ ሐውልት አጭር ጸሎት እንድሚያደርጉ ተገልጿል። እኚሁ የቅድስት መንበር ፕሬስ ጽ/ቤት ዲሬክተር በመቀጠል ይህ ሰቆቃና ችግር ያበቃበት 75 ዓመት በዚሁ ወቅት እንደሚከበር ኣስረድተው የዚህ ሙዚየም መኖር ይህ ሕዝብ ምን ያህል እንደተሰቃየና በችግር ውስጥ እንደነበር ለማመላከት የሚያስችል ኣንድ ቅርስ መሆኑንም ጨምረው ኣስረድተዋል።

በመጨረሻም የቅድስት ፕሬስ ጽ/ቤት ዲሬክተር ግሬግ ቡርኬ ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ በዚሁ ቆይታቸው የሞት ፍርድ ቤቶችን ቀሳውስትንና ጳጳስን ጨምሮ ብዙ ሰዎች ሲሰቃዩባቸው የነበሩ ቦታዎችና የተለያዩ ክፍሎችን እንደሚጎበኙ ገልጸዋል።

21 September 2018, 17:51