ፈልግ

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ በኤስቶኒያ ለሃገሪቱ መሪና ከፍተኛ ባለሥልጣናት ንግግር ኣደረጉ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ አባ ግርማቸው ተስፋዬ - ቫቲካን

በዛሬው ዕለት ማለትም ዕለተ ማክሰኞ መከረም 25 2018 ዓ.ም. እ.አ.አ. ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ በታሊኒ ኤስቶኔአ ለመንግሥት ባለሥልጣናት ለሲቭሉ ማኅበረሰብና ለተለያዩ ዲፕሎማቲች ኣካላት ንግግር ማድረጋቸው ታውቋል። በዚህ ንግግራቸው ወቅት የኣገሪቱ ርዕሰ ብሔር እና የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት መገኘታቸው ታውቋል።

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ይህችን ከተማ በመጎብኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው አያይዘውም ርእሰ ብሔሩ ላሰሙት የእንኳን ደህና መጣችሁ ቃል እንዲሁም የዚህን የእስቶኔአን ሕዝብ ወክለው ለተገኙት ሁሉ ምስጋናቸውን አድርሰዋል። ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ይህ መሬት ወይም ይህ ቦታ የማርያም መሬት ወይም ማርጃማ ይባል እንደነበር ኣስታውሰው ይህ ሥም ደግሞ ከታሪካችሁ ጋር ብቻ ሳይሆን ከባሕላችሁም ጋር የተቆራኘ መሆኑን አስታውሰዋል።

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ስለ ማርያም ሳስብ ሁለት ነገሮች በጭንቅላቴ ይመጣሉ እነሱም ትውስታና ፍሬኣማነት ናቸው። ማርያም ሁሉን ነገር በልቧ ጽፋ ትይዘው እንደነበር በሉቃስ ወንጌል 2, 19 ላይ ያለዉንና ማርያምን ጌታችን እየሱስ ክርስቶስን በመውለዷ ፍሬኣማ እንደነበረች በማስታወስ ይህም ደግሞ ኤስቶኔአ የትውስታና የፍሬ ኣገር መሆንዋን ገልጸዋል። በመቀጠልም ቅዱስ ኣባታችን የእስቶኔአ ሕዝብ በታሪኩ ውስጥ ነፃነትን ለመቀዳጀት የተለያዩ ችግሮችና ሥቃዮችን ማሳለፉን ኣስታውሰው ባለፈው 25 ዓመት ውስጥ ግን ሙሉ በሙለ ልክ እንደ ኣንድ ቤተሰብ ነፃ የሆነች ኣንድ ኣገር መሆኗን ተናግረዋል።

የሰው ልጅ በተለያዩ መስኮች ውስጥ እየተተገበረ ባለው የእድገት ሂደት ውስጥ የሚከሰቱት ስህተቶች እያረሙ መሄድና ለሕዝቦች ደህንነት አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ ስኬቶች ደግሞ በየጊዜው ሊሞገሱ ይገባቸዋል። የትውስታ ወይም የመታሰቢያ ኣገር መሆን ማለት ከዚህ በፊት በአባቶቻችሁ ጥረት የተሠሩትን ሥራዎች የቅድሞ አባቶቻችሁን መንፈስ እና እምነት ማስታወስ ማለት ነው። ይህንን ነፃነት በተለያየ መንገድ እንድትጎናጸፉ ያደርጉትን ሁሉ የቅድሞ ኣባቶቻችሁንና እናቶቻችሁን በማስታወስ ከእናንተ በኋላ ለሚመጣው ትውልድ ደግሞ እናንተም በብዙ መልኩ በር ከፍች መሆን ይገባችኋል ብለዋል።

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ በመቀጠል ሲያብራሩ ያኔ ገና የሮማ ጳጳስ ሆኜ ስመረጥ እንደተናገርኩት የሰው ልጅ በተለያዩ መስኮች ውስጥ እየተተገበረ ባለው የእድገት ሂደት ውስጥ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። ለሕዝቦች ደህንነት አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ ስኬቶች ሁሌም ሊሞገሱ ቢገባቸውም ቅሉ ከሁሉ በላይ ሁሉን ማግኘት ማለት ጥሩ ኑሮ መኖር እንዳልሆነ ኣስምረውበታል።

በቴክኖክራስት ማህበረሰቦች ውስጥ ልንመለከታቸው ከሚገቡ ክስተቶች አንዱ የመኖር ትርጓሜ ማጣት በሕይወት ውስጥ ደስታ ማጣት ሲሆን እነዚህ ነገሮች ደግሞ በስተመጨረሻ ወደ ከፋ ችግርና አዘቅት ውስጥ ይከታሉ ብለዋል።

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ኣያይዘው የኣንድን መሬት ምርታማነት ለመጨመር ተባብሮ መሥራትና መተጋገዝ እንድሚያስፈልግ ጠቅሰው ለዚህ ምርታማነት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሁሌም ከጎናቸው እንደምትቆና ለዚህች አገር ፍሬያማነት አስተዋፅኦ ለማበርከት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት በግግራቸው አረጋግጠዋል።

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ በመጨረሻም ስለተደረገላቸው መስተንግዶ የኣገሪቱን ርእሰ ብሔርና በቦታው የተሰብሰቡትን ሁሉ ኣመስግነው ለዝችም ሃገር ምርታማነትና ዕድገት ጠንክረው እንዲሰሩ ኣሳስበው እግዚኣብሔር ሃገሪቱንና ሕዝቧን ሁሉ እንዲባርክና ተመኝተው ንግግራቸውን ቋጭተዋል።

25 September 2018, 18:17