ፈልግ

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ “የኤስቶኒያ ምዕመናን ወደ ሙሉ ነጻነት ይደርሱ ዘንድ”።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ዛሬ ማክሰኞ መከረም 15 ቀን 2011 ዓ.ም. በኤስቶኒያ ዋና ከተማ በታሊን የነጻነት ኣደባባይ ላይ ለተገኙት በርካታ ምእመናን ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴን ስነ ስርዓት ላይ በዕለቱ በተነበቡት የቅዱስ መጽሐፍ ንባባት በመመርኮዝ ቃለ እግዚኣብሔር ኣሰምተዋል። የቅዱስነታቸው አስተንትኖ ቃል ትርጉም የሚከተለው ነው።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ አባ ግርማቸው ተስፋዬ - ቫቲካን

“ዛሬ በተነበብው የመጀመሪያ ንባብ ከኦሪት ዘጸኣት 19፡1 እስራኤላውያኑ ከባርነት ነፃ ወተው ወደ ሲና ተራራ መድረሳቸው ሰለ ኤስቶኔአና ሰለ ሁለቱ የባልቲክ ኣገሮች ጭምር እንድናስብ ይደርገናል። በተለይም በካንታና ኣብዮት በዚህ በቪሊኒኡስ ሁለት ሚሊዎን የሚጠጉ ሕዝቦች የነበሩበትን ኣጣብቂኝና እናስታውሳለን። እናንንተ ለነፃነት የሚደረግ ትግል ምን እንደሆነ ኣሳምራችሁ ታውቃላችሁ ይህም ትግል ከአይሁዳውያኑ ጋር ያመሳስላችኋል። ስለዚህ እግዚኣብሔር ለሙሴ የተናገረውን ቃል መስማቱ ለእኛም እንደ ኣንድ ሕዝብ መልካም ይሆንልናል።

ሁላችንም እንደምናውቀው ከብዙ ዉጣ ወረድ በኋላ ወደ ሲና ተራራ የደረሰው የእስራኤል ሕዝብ የኣምላኩን የእግዚኣብሔርን ብዙ ተዓምሮችና ድንቅ ነገሮችን በዓይኑ ተመልክቷል በዚህም ምክንያት ከኣምላኩ ከእግዚኣብሔር ጋር ኣንድ የፍቅር ስምምነት ለማድረግ ወስኗል ምክንያቱም እግዚኣብሔር ገና ከጅምሩ ይህንን ፍቅር ኣሳይቶታል ገልጾለታልም። እግዚኣብሔር ይህንን ሁሉ ለእስራኤላውያኑ ሲያደርግእንዲሁም ሕዝቡም መልሶ ወደ እግዚኣብሒር ሲመጣ ተገዶ ወይም ደግሞ በተፅእኖ ሳይሆን ከራሱ ነፃ ፍላጎት የተነሳ ነበር።

እኛ ሁላችን ክርስቲያኖች ነን ብለን ስንናገር ኣንድ ወጥ የሆነ የሕይወት ውቅጣጫ ይዘናል ብለን ስንናገር ያ ያለ ምንም ተጽእኖ መሆን ኣለበት ወይም ደግሞ እግዚኣብሔር ኣንድ ነገር ኣድርጎልኛልና እኔም መልሼ ኣንድ ነገር ላድርግለት በማለት ልክ እንደ መለዋወት ወይም የግብይት ዓይነት ነግር መሆን የለበትም። ከሁሉ በላይ መረዳት ያለብን ነገር ምንድን ነው እግዚኣንሔር ወደ እኛ ሲመጣ ከእኛ ምንም ፈልጎ ሳይሆን የእኛን ሕይወት ሙሉ ለማድረግ ነው የእኛን ፍላጎቶች ሁሉ በሙላት ሊፈፅምልን ኣስቦ ነው።

ኣንዳንድ ጊዜ ኣንዳንድ ሰዎች ነፃነትን ከእግዚኣብሔር ውጭ የሆነ ሕይወት ወይም ደግሞ ከእርሱ የተለይ ሕይወት ኣድርገው የሚወስዱ ኣሉ። በዚህ ጊዜ ያልተረዱት ነገር ምንድን ነው እየኖሩ ያሉት ልክ ኣባትና እናት እንደሌላቸው የማደጎ ልጆች መመሆነቸውን ነው ምክንያቱም የሚመለሱበት ቤት የላቸውም።

የር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ሓዋርያዊ መልዕክት ኢቫንጀሊኡም ጋውዲኡም ቁጥር 170 ላይ እንደተጠቀሰው ነጋዲያን መሆናቸውን ኣቁመው ምንም መድረሻ የሌላቸው ተጓዦች ይሆናሉ ይላል። ልክ ከግብጽ እንደወጣው ሕዝብ ማዳመጥና መፈለግ ለእኛ ለእያንዳዳችን የተተወ ኃላፊነት ነው። ኣንዳንድ ጊዜ ኣንዳንድ ሰዎች የኣንድ ኣገር ወይም ሕዝብ ጥንካሬ በተለያየ ሁኔታ የሚለካ የሚመስላቸው ኣሉ ኣንዳንዶች ድምፃቸውን ከፍ ኣድርገው በመናገራቸው ወይ በመጮሃቸው ብቻ ያለምንም ገደብ ያለምንም ጥርጣሬ ሁሉ ነገር የተስተካከለ ወይም በመልካም ሁኔታ ውስጥ ያለ የሚመስላቸው አሉ ኣንዳንዶች ደግሞ በጩኸታቸው ላይ የጦር መሳሪያ ማካተትን ማስፈራራትን ወታደሮች ማሰማራትን የተለያዩ ወታደራዊ ስልቶችን የጨበጡ

በመሆናቸው ብቻ ሁሉ ነገርን የተቆጣጠሩ የሚመስላቸው ኣሉ ይሄ ግን የእግዚኣብሔርን ፈቃድ መፈፀም ወይ መፈለግ ሳይሆን የራስን ነገር ለማከማቸት እና ለማግኘት መሠረት ያደረገ ኣሠራር ነው። ይህ ኣስተሳሰብ በራሱ በሥነ ምግባር ኣካሄድ ኣለመመራትና በዚህም ኣድርጎ ደግሞ ለእግዚኣብሔርም ኣለመታዘዝ ነው። ይህ ሥነ ምግባር ሁልጊዜ ከእግዚኣብሔር ነፃ መልስ እንድንሰጠው ከሚጠብቀን ኣምላክና ከሌሎች ወድሞቻችን እንዲሁም በዙሪያችን ካሉ ፍጥረታት ጋር ኣድርግልኝ ላድርግለህ ዓይነት ግንኙነት ሳይሆን መልካምና የተስተካከለ ግንኙነት እንዲኖረን ያደርጋል።

የር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ሓዋርያዊ መልዕክት ኢቫንጀሊኡም ጋውዲኡም ቁጥር 57። እግዚአብሔር ሁሌም የሚያስፈልገንን ያውቃል እኛ ብዙ ጊዜ በስተጀርባ የምንደብቀውን ለማግኘት የምንመኘውን ያልተስተካከለልንን በእርሱም ኃይል ያገኘነውን ሁሉ ሳይቀር ያውቃል። በሰዎች ሁሉ ልብ ውስጥ የሚገኘው ጥማት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዛሬ በሰማነው ወንጌል ኣማካኝነት ከእርሱ ጋር ለመገናኘት እንድንሞክር ያበረታታናል። እሱ ብቻ ነው በጥማታችን በውሀው ሙላት በንጹህነቱና ሞልቶ በሚትረፈረፈው ኃይሉ ሊያረካን የሚችለው።

ዕምነት እርሱ ዘወትር ከእኛ ጋር እንዳለ ማመንና እና እኛን እንደሚወድ መቀበል ነው እርሱ ፈጽሞ ኣይተወንም ሁሌም ኣብሮን ኣለ ስለዚህም በእያንዳዳችን ታሪክ ውስጥ ሚስጥራዊ በሆነ መንገድ ጣልቃ መግባት ይችላል። እርሱ በኃይሉ ማለቂያ በሌለው ችሎታው ከመጥፎ ውስጥ መልካሙን ያፈልቃል። ኢቫንጀሊኡም ጋውዲኡም ቁጥር 287። በምድረ በዳ የእስራኤል ህዝብ በራሳቸው ጥንካሬ በመተማመን ሌሎች አማልክትን በመፈለግ ወርቃማ ጥጃውን በማምለክ ወደ ፈተና ውስጥ ወድቀዋል ነገር ግን እግዚአብሔር ሁልጊዜ እነርሱን ካሉበት የተሳሳተ ሁኔታ ይመልሳቸዋል ከወደቁበት ማጥ መልሶ ያወጣቸዋል እነርሱም በተራራው ላይ የሰሙትን እና የተመለከቱትን ያስታውሳሉ።

እንደ እስራኤል ሕዝብ ሁሉ እኛም የተመረጠ ክህነታዊና ቅዱስ ሕዝብ መሆናችንን እናውቃለን (ዘጸ 19፣ 6 1 ኛጴጥ 2፣ 9) እነዚህን ሁሉ ነገሮች የሚያስታውሰን መንፈስ ቅዱስ ነው (የዮሓንስ ወንጌል 14:26)። የተመረጡ ማለት በሁሉ ነገር የተለዩና ከነሱ ሌላ ማንም የለም ማለት ዓይደለም እኛ ሁላችን ልክ ሙሉዉን ሊጥ እንዳቦካችው እንደ ትንሿ እርሾ ሁሉም ነገር ጥሩ እንዲሆን በውስጥ ሆነን የምናግዝ እንጂ በውስጥ ገብተን የምንደበቅና የምንለያይ ኣይደለንም። ይህን በማድረጋችን ደግሞ ከሌላው በምነም መልኩ የተለየንና ከሌላዉም በምንም መልኩ የተሻልን ኣይደለንም።

ንስር ጫጩቶቿን በተረጋጋ መንፈ ከሚቀመጡበት ጎጆኣቸው ወደ ከፍተኛ ቦታ በመውሰድ ክንፋቸውን እንዲዘረጉና ለመብረር እንዲሞክሩ ራሳቸውን እንዲፈትሹ ራሳቸውን እንዲችሉ ለመድረግ ይለቃቸውና እርሱ ግን ክፉ ኣንዳይነካቸው እንዳይወድቁ ከሥራቸው ሆኖ ይበራል። ልክ እንደ ንስሩ እግዚኣብሔርም የመረጠው ሕዝብ በራሱ እንዲወጣ ይፈልጋል ነገር ግን ኣስፈላጊውን ጥበቃና እገዛ ሁሌም ከጎኑ ሆኖ ያደርግለታል። ፍርሃትን ከውስጣችን ማውጣትና እና የጦር ነገሮችን ሁሉ መተው አለብን ምክንያቱም ዛሬ አብዛኛዎቹ ኤስቶኒያውያን እንደ አማኞች ኣይታወቁም። ሁሌም በጥምቀታችን ኣማካኝነት በተቀበልነው በካህናት መንፈስ

መንቀሳቀስና መሥራት መግባት መውጣት ያስፈልጋል። ከእግዚኣብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ሁልጊዜ በማቴዎስ ወንጌል 11,28 ወደ እኔ ኑ እያለ ከሚጠራንን ድምጽ ጋር የፍቅር ግንኙነት ለማድረግ ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል። አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ ሁሉ ሌላውን ለማነቃቃትና ለማንቀሳቀስ ኣንዲሁም ኣብሮ በነገሮች ላይ ለማስተንተን የቅርርብን መንፈስ ማሳደግ ይኖርብናል። ይህ የመቀራረቢያያ ጥበብ ነው ይህ ጤናማ ግንኙነት የሚተገበርበት አካሄድ ነው ይህ በአክብሮትና በርህራሄ የተሞላ የመፈወስ ችሎታ ያለዉና ኣላስፈላጊ ያልሆኑትን ነገሮች ወደ ጎን በመተው በክርስትና ሕይወት ማደግ የሚያስችል ነው። ኢቫንጀሊኡም ጋውዲኡም 169።

እና በመጨረሻም የተቀደሰ ህዝብ መሆናችሁን በተግባራችሁ አሳዩ ምሥክርነትም ስጡ። ቅድስና ለአንዳንዶች ወይም ለተመረጡት ብቻ የተሰጠ እንደሆነ በማሰብ ፈተና ውስጥ ልንወድቅ እንችል ይሆናል ነገር ግን ሁላችንም በምንኖርበት ቦታ ሁሉ በፍቅርና በዕለታዊ ኑሮኣችን የተሰጠንን ኃላፊነት በመወጣት ቅዱሳን እንድንሆን ተጠርተናል። የር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ሓዋርያዊ መልዕክት ጋውዴት ኤሱልቴት ቁጥር 14። በበረሃ ያለ ዉሃ የግል ሳይሆን የጋራ ነው መናም ስለሚበላሽ ለነገ ማሳደር እንደማይቻል ሁሉ በዕለታዊ ኑሮኣችን የሚገባንንና የሚጠበቅብንን ካደረግን ቅድስናን ይለመልማል እንደ ውኃም ይፈሳል በዙሪያው ያሉትን ሁሉ ያረሰርሳል።

ዛሬ እኛም ቅዱሳኖች በመሆን በዙሪያችን የሚገኙትን ስደተኞችን የተገለሉትንና በተለያየ ቦታ ኣስፈላጊዉ የሰው ልጅ ፍላጎቶች ማሟሏት ባለልተቻለበት ቦታ የወደቁትን በሚቻለን ሁሉ እንንከባከብ። ከእኛ በኃላ የሚመጣውን በመጠበቅ ለእሱ ኃላፊነታችንን መተው ሳይሆን እኛ ራሳችን ዓይናችንን በተቸገረው ወንድማችንና እህታችን ላይ እናሳርፍ እጁንም በመያዝ ቀና እናድርገው ምክንያቱም የእግዚኣብሔር ማንነት በእሱ የእግዚኣብሔር ማንነት በእሷ ውስጥ ይገኛልና። እሱም ሆነ እሷ ሁለቱም በጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ደኅነነትን ያገኙ ናቸውና።

ይህ ማለት እውነተኛ ክርስቲያን መሆንና የቅድስናን ሕይወት ዕለት በዕለት መኖር ማለት ነው። ጋውዴት ኤሱልቴት ቁጥር 98። እናንተም የስቶኒኣ ዜጎች የዝች ሃገር ዜጋ በመሆናችሁ እንድምትኮሩና በመዝሙራችሁም እንደምትዘምሩት ስቶኒያዊ ነኝ ስቶኒያዊ ሆኜ እስከመጨረሻ እዘልቃለሁ ስቶኒያዊ መሆን በጣም ውብ ነገር ነው እኛ ስቶኒያዊ ነን እንዳላችሁት ነው። የኣንድ ሕዝብ ኣካል መሆን እንዴት ደስ ይላል ነፃነት መጎናፀፍ እንዴት ደስ የሚል ነገር ነው።

ሁላችንም በኣንድነት ወደ ሙሴ ተራራ ወደ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ተራራ በመሄድ የዚህ ጉብኝት መሪ ሓሳብ እንደሚለው የመንፈስ ቅዱስን ሥጦታዎች ለሁሉም ለማዳረስና ነፃነታችንን ለመጎናጸፍ መልካም የሆነዉን ሁሉ ኣጥብቀን ለመያዝና መመረጣችንን በሙላት ለመረዳት ልባችንን ያነሳሳልን። እግዚኣብሔር በሁሉም ነገር “በመላው ዓለምና በዚህ በእስቶኒያ የእርሱ ቅዱስና ክህነታዊ ሕዝብ ኣድርጎ እንዲያሳድገን በረከቱ ይብዛልን”

25 September 2018, 17:50