ፈልግ

በማርሲኔል የመዐድን ማውጫ ሥፍራ የዛሬ 62 አመት አደጋ በደርሰበት ወቅት በማርሲኔል የመዐድን ማውጫ ሥፍራ የዛሬ 62 አመት አደጋ በደርሰበት ወቅት  

በማርሲኔል የመዐድን ማውጫ ሥፍራ የደርሰው አደጋ 62ኛ አመት ተዘከረ

በማርሲኔል የመዐድን ማውጫ ሥፍራ የደርሰው አደጋ እና በተለያዩ ጊዜያት የነበሩ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሥራን እና የሰው ልጅ ክብር በተመለከተ የሰጡትን ማሳሰቢያ እና የጻፉትን ሐዋሪያዊ መልእክቶች በቅደም ተከተል እንደ ሚከተለው እናቀርብላችኋለን። ተከታተሉን።

በማርሲኔል የመዐድን ማውጫ ሥፍራ የደርሰው አደጋ 62ኛ አመት ተዘከረ

በቤልጄዬም ማርሲኔሌ በመባል በሚታወቀው የመዕድን ማውጫ ሥፍራ እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በነሐሴ 08/1956 ዓ.ም (የዛሬ 62 አመት ገደማ ማለት ነው) በደርሰው አደጋ 262 ሰዎች ሕይወታቸውን ማጣታቸው ይታወሳል። በወቅቱ በዚህ የማዕድን ማውጫ ሥፍራ 274 ሰዎች በሥራ ላይ ተሠማርተው የነበረ ሲሆን በደረሰው የእሳት አደጋ ከ95 % ያህሉ በአደጋ ምክንያት ሕይወታቸውን ማጣታቸው ይታወሳል። ከእነዚህ ሟች የመዕድን ሥፍራ ሠራተኞች መካከል አብዛኛዎቹ ከተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ሥራ ለመፈለግ ወደ ቤልጂዬም ያቀኑ የሌላ ሀገር ዜጎች መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን በዚህም መሰረት ከ262 ሟች የመዕድን ሥፍራ ሠራተኞች መካከል 136 ጣልያናዊያን፣ 95 በልጄማዊያን፣ 8 ፖላንዳዊያን፣ 6 ግሪካዊያን፣ 5 ጀርመናዊያን፣ 5 ፈረንሳዊያን፣ 3 ሀንጋራዊያን፣ 1 እንግሊዛዊ፣ 1 ሆላንዳዊ፣ አንድ ራሻዊ እና አንድ ዩክሬናዊ ይገኙበታል። 

በወቅቱ በመዕድን ማውጫ ሥፍራ የደርሰውን አሰቃቂ አደጋ ይህንን ያህል ካስታወስናችሁ በታሪክ ሂደት ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት የነበሩ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በማኅበራዊ አስተምህሮዎቻቸው ሥራ የሰው ልጅ ክብር መገለጫ በመሆኑ የተነሳ በሥራ ቦታዎች ለሰው ልጆች ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ፣ ደረጃውን የጠበቀ እና በተለይም የአደጋ ጊዜ መከላከያ ቁሳቁሶች ለሠራተኞች በበቂ ሁኔታ ተደራሽ ማድረግ እንደ ሚገባ ማሳሰቢያዎችን ሲሰጡ መቆየታቸው ይታወሳል።

በማርሲኔል የዛሬው 62 አመት ገደማ በመዕድን ማውጫ ሥፍራ የደርሰውን እና የ262 ሰዎችን ነብስ የቀጠፈው አሰቃቂ አደጋ 62 አመቱ በሚዘከርበት በአሁኑ ወቅት አሁንም ቢሆን እኛ ባለንበት ዘመን በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተለያዩ አደጋዎች በሠረተኞች ላይ እየደረሱ እንደ ሚገኝ የሚታወቅ ሲሆን ይህንን የዛሬ 62 አመት ገደማ የተከሰተውን አሰቃቂ አደጋ በምናስታውስበት በአሁኑ ወቅት በእኛ ዘመን በሥራ ቦታዎች በሠራተኞች ላይ እየደረሱ የሚገኙ አደጋዎችን፣ በተለይም አሰሪዎች በስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆነው ለሚሰሩ ሠራተኞቻቸው በቂ ጥበቃ እን እንክብካቤ ማድረግ እንደ ሚገባቸው ለማሳሰብ እድሉን የሚከፍት አጋጣሚ ነው።

የዚህ ዘገባ አቅራቢ መብራቱ ኃይሌጊዮርጊስ-ቫቲካን

ሥራን የተመለከቱ የቤተ ክርስቲያኗ አስተምህሮዎች

ሥራ መብት መሆኑን በተመለከተ ከዚህ በፊት እንደ ነበረ ሁሉ ዛሬም ቢሆን በከፋ ሁኔታ ለሕገ-ወጥ ሥራ እና በተወሰኑ በጥቂት ሰዎች ቁጥጥር ሥር በሚገኙ የሥራ መስኮች ውስጥ ገብተው የሚሠሩ ለጥቃት የተጋለጡ ብዙ ሰዎች አሁንም በዘመናችን መገኘታቸውን ማወቁ ከቤተ ክርስቲያኗ ወሳኝ እሴቶች ጋር የሚቃረን በመሆኑ ቤተ ክርስቲያን በትኩረት የምትከታተለው ጉዳይ ነው። ሥራ ክቡር መሆኑን የሚገልጹ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮዎችን በተመለከተ በተለያዩ ጊዜያት የነበሩ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የተለያዩ ማኅበራዊ አስተምህሮችን ማስተላለፋቸው የሚታወስ ሲሆን እነዚህ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሥራን በተመለከተ ያሰተላለፉቸው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ማኅበራዊ አስተምህሮዎች እንደ ወቅቱ ሁኔታ ከፍተኛ አዎንታዊ አስተዋጾዎችን አብርክተዋል።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ ውስጥ ሥራን በተመለከተ በሰፊው የተገለጹ ብዙ አስተምህሮዎች እንደ ሚገኙ የሚታወቅ ሲሆን ለአብነት ያህል የሚከተለውን እንመለከታለን. . .

 “ሰብኣዊ ሥራ የሚፈለቀው በቀጥታ በእግዚኣብሔር አምሳያ ከተፈጠሩና እርስ በእርስና ለጋራ ጥቅም ብለው መሬትን በማስገበር የፍጥረትን ሥራ እንዲያራዝሙ ጥሪ ከተቀበሉ ሰዎች ነው። ሥራ የፈጣሪን ስጦታዎች እና ከእርሱ የተለገሱትን ስጦታዎች እንድናዳብር ያደርጋል። ሥራ አዳኝ ሊሆን ይችላል። ሰው እንዲያከናውነው በተጠራበት ሥራ ላይ በዕየለቱ መስቀሉን በመሸከም የክርስቶስ ደቀ-መዝሙር መሆኑን ሊያሳይ ይችላል። ሥራ መቀደሻ፣ ምድራዊ እውነታዎችንም በክርስቶስ መንፈስ ማነቃቂያ ሊሆን ይችላል” (የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ ቁ. 2427)።

በተለይም ደግሞ ሥራን በተመለከተ በዚሁ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ ውስጥ እንደ ተጠቀሰው “ሰው በሥራው አማካይነት በተፈጥሮ የታደለውን ችሎታ በከፊል ገቢራዊ ያደርጋል። ቀዳሚ የሥራ ዋጋ የምፈልቀው ባለቤቱ እና ተጠቃሚ ከሆነው ከራሱ ከሰው ነው። ሥራ ለሰው እንጂ ሰው ለሥራ አልተፈጠረም። እያንዳንዱ ሰው ከሥራው ለሕይወቱ እና ለቤተሰቡ የሚያስፈልገውን የሚያሟላበት እንዲሁም ሰብኣዊ ኅበረተሰቡን የሚያገለግልበትን ብልሃት ማግኘት መቻል አለበት”  (ቁ. 2428)። ከዚህም ባሻገር ሥራ በእግዚኣብሔር ጸጋ አማካይነት ሰዎች ራሳቸውን የሚያነጹበት እና የሚቀድሱበት እንዲሁም ከክርስቶስ ጋር በመተባበር ሌሎች ሰዎችን ወደ ደኅንነት መስመር የሚመልሱበትን አጋጣሚ ልፈጥር ይችላል።

ሥራ የሰው ልጅ ክብር ነው

የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ማሕበራዊ አስተምህሮን በተመለከተ በቀዳሚነት እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በ1891 ዓ.ም. በወቅቱ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነበሩት ሊዮ 13ኛ አማካይነት የተጻፈው በላቲን ቋንቋ “Rerum Novarum”  በአማሪኛው በግርድፉ ሲተረጎም “አዳዲስ ነገሮች” በሚል አርእስት የተጻፈው ማኅበራዊ አስተምህሮ እንደ ሆነ የሚታወስ ሲሆን በወቅቱ በማንሰራራት ላይ በነበረው የእንዱስትሪ አብዮት ምክንያት ጉልበታቸው ያለ አግባቡ ሲበዘበዝ ለነበሩ ሠራተኞች ጥብቅና የቆመና ሠራተኞች ተገቢው እንክብካቤ እና ክብር እንዲሰጣቸው የሚያሳስብ ሐዋሪያው መልእክት እንደ ነበረ ይታወሳል።

ይህ በላቲን ቋንቋ “Rerum Novarum”  በአማሪኛው በግርድፉ ሲተረጎም “አዳዲስ ነገሮች” በሚል አርእስት የተጻፈው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያው ማኅበራዊ ጉዳዮችን የተመለከተው ሐዋሪያዊ መልእክት በሥራ ቦታ የሰው ልጆችን ሰብኣዊ ክብር የሚገፉ ወይም የሚያጎሉ ተግባራት እንዲወገዱ የሚመክር ሐዋሪያዊ መልእክት ሲሆን “ምክንያታዊ እና ሐይማኖታዊ በሆነ መልኩ ሥራን ስንመለከት ‘ሥራ ሰውን የሚያዋርድ ነገር አይደለም፣ ነገር ግን እሱ ራሱ በስራው ሐቀኛ በሆነ ተግባር ለመኖር የሚያስችለውን ሁኔታ በመፍጠር የሰው ልጅ ከብር መገለጫ ነው። የሰውን ክብር የሚቀንስ ሥራ ትርፍን ብቻ ለማጋበስ በሚል ሕሳቤ በምንጠቀምበት ወቅት ሰዎችን የሰውነት ክብራቸውን በመግፈፍ የራሳችን ጥቅም ማግኛ ዘዴ በማድረግ ሰብኣዊ ክብራቸውን በመግፈፍ እንደ አገልጋይ ባሪያ እንቆጥራቸዋለን፣ ይህም ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው’ በማለት “Rerum Novarum”  በአማሪኛው በግርድፉ ሲተረጎም “አዳዲስ ነገሮች” በሚል አርእስት የተጻፈው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያ ሐዋሪያዊ መልእክት ይገልጻል። ከልክ በላይ የሆነ ሥራ ወይም ጾታ እና እድሜን በተገቢው ሁኔታ የማይለይ እና ይህንን ያላማከለ ሥራ የሰራተኞች ጤናን ሊጎዳ ይችላል፣ በማለት በሥራ ቦታ ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ ለሠራተኞች ሊደረግ እንደ ሚገባው የሚያሳስብ ሐዋሪያዊ መልእክት ሲሆን ማነኛቸውም የሥራ ቦታዎች በሕግ እና በአግባቡ መመራት እንደ ሚኖርባቸው ያሳስባል። በተጨማሪም “የሰው ልጅ ሰብአዊ ፍጡር በመሆኑ የተነሳ ትርፍን ለማጋበስ ሲባል ብቻ ያለውን ኃይል አሟጦ እንዲጠቀም በማድረግ ሰውነቱን ለከፍተኝ ድካም እንዲጋለጥ ማድረግ የሰውን ልጅ ሰብኣዊ ክብር የሚቀንስ ተግባር በመሆኑ፣ የሰው ልጆችን ከተገቢው ሰዓት በላይ ሥራን እንዲሰሩ ማድረግ አካላቸውን ለጉዳት የሚያጋልጥ ተግባር በመሆኑ የተነሳ ከፍተኛ የሆነ ትኩረት ሊሰጠው እንደ ሚገባ፣ በተለይም ደግሞ በመዕድን ማውጫ ስፍራዎች የሚሰሩ ሠራተኞ ለጤናቸው እንክብካቤ እንዲደረግ”Rerum Novarum”  በአማሪኛው በግርድፉ ሲተረጎም “አዳዲስ ነገሮች” በሚል አርእስት እ.አ.አ በ1891 ዓ.ም በወቅቱ በነበሩት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ልዮ 13ኛ የተጻፈው ሐዋሪያዊ መልእክት ያስረዳል።

አካላዊ ጤና

የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት ዮሐንስ 23ኛ  በላቲን ቋንቋ “Pacem in Terris” በአማሪኛው “ሰላም በምድር ይሁን!” በሚል አርእስት በእ.አ.አ 1963 ዓ.ም ለንባብ ያበቁት ሐዋሪያዊ መልክት “የሰው ልጅ በኢኮኖሚ መስክ ውስጥ ነፃ የንግድ ክንውኖችን የማድረግ መብት እንዲኖረው እና ሥር የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ መብት ነው” በማለት በአጽኖት መገለጻቸው ይታወሳል። እንዲህ ያሉ መብቶች - በሐዋሪያዊ መልእክት ውስጥ እንደ ተገለጸው- “አካላዊ ጤንነት እና ሥነ ምግባርን የማይጎዱ የሥራ ሁኔታዎች ጋር ተያያዥነት እንዳለቸው በማሳየት” እንዲሁም በሰው ልጆች ውስጥ በተፈጠረው ውስጣዊ እድገት ውስጥ ጣልቃ የማይገቡ መሆን እንደ ሚገባቸው” የሚገልጹ በርካታ አንቀጾች የሚገኙበት ሲሆን በተለይም ደግሞ “ሴቶች እናቶች እና ሚስቶች በመሆናቸው የተነሳ ከሚያስፈልጋቸው እና ከተሰጣቸው ኃላፊነቶች ጋር የተጣጣመ የሥራ ሁኔታ የማግኘት መብት አላቸው” በማለት ይገለጻል።

የተቀናጀ እድገት

የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነበሩት ጳውሎስ 6ኛ በላቲን ቋንቋ “Populorum Progressio በአማሪኛው በግርድፉ ሲተረጎም “የሕዝብ እድገት/ልማት” በሚል አርእስት እ.አ.አ 1967 ዓ.ም ለንባብ ባበቁት ሐዋሪያዊ መልእክት ላይ ሥራን እና ነጻነትን በተመለከተ እንደ ገለጹት “ሥራ ሥራ ሊባል የሚችለው የሰው ልጆችን እውቀት እና ነጻነት በጠበቀ መልኩ ሲሠራ ብቻ ነው!!” በማለት መግለጻቸው ይታወሳል። “ሥራ ሚዛናዊ የሆነ የልማት ሂደትን በመጠበቅ ብቻ ሊከናወን ይገባል” የሚል ጭብጥ ያዘለ ሐዋሪያዊ መልእክት እንደ ነበረ የሚታወቅ ሲሆን “በሥራ ቦታዎች በሰው ልጆች ላይ የሚደረጉ ከፍተኛ የሆኑ ጫናዎች የሰው ልጆች እንዲዳከሙ በማድረግ የተፈለገውን ልማት እና እደገት ለማምጣት አስቸጋሪ የሆነ ሆኔታን የፈጥራሉ” በማለት በሥራ ቦታዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደ ሚገባ ይገልጻል።

ማነኛውም የማምረት ሂደት የሰው ልጆች ሕይወት ቀጣይ በሆነ መልኩ የሚያሻሽል ሊሆን እንደ ሚገባው በላቲን ቋንቋ “Populorum Progressio በአማሪኛው በግርድፉ ሲተረጎም “የሕዝብ እድገት/ልማት” በሚለው በሐዋሪያዊ መልእክታቸው የገለጹት ጳውሎስ 6ኛ “ማንኛውም ሕዝብ ያፈራው ሐብት የእርሱ የግሉ መጠቀሚያ ብቻ አድርጎ መቁጠር እንደ ሌለበት፣ በአንጻሩ ግን እያንዳንዱ ኅብረተሰብ ለእውነተኛ የሕይወት እድገት ደረጃ እንዲያውለው እና በተመሳሳይ መልኩም ለሰብአዊ ዕድገቱ አስተዋጾ በማድረግ ለመላው የሰው ልጆች ጥቅም እንዲወል ማደርግ ይኖርባቸዋል” የሚል ጭብጥ ያዘለ ሐዋሪያዊ መልእክት ነው።

ሥራ ለሰው መልካምነት

የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት ዮሐንስ ጳውሎስ ሁለተኛ በላቲን ቋንቋ “Laborem Exercens በሚል አርእስት የጉልበት ሥራን በተመለከተ እ.አ.አ በ1981 ዓ.ም ለንባብ ባበቁት ሐዋሪያዊ መልእክታቸው ላይ እንደ ግለጹት “ሥራ ለሰው ልጅ መልካም አገልግሎት ሊውል የገባዋል፣ ሥራ የሰው ልጅ ሰብኣዊነት መገለጫ ነው፣ ምክንያቱም የሰው ልጅ በሥራ አማካይነት ራሱን ከመጥቀሙ ባሻገር ከራሱ ፍላጎቶች ጋር በማስተባበር ብቻ ሳይሆን እንደ ሰው ራሱን እንዲገነዘብ፣ እንዲያውም በተወሰነ መልኩ የበለጠ ሰው መሆኑን እንዲረዳ ያደርገዋል” በማለት መገለጻቸው ይታወሳል። ሥራ ውስብስብ ከሆነ የሰው ልጆች ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ከመንቀሳቀስ መብት ጋር እንደ ሚያያዝ በሐዋሪያዊ መልእክታቸው የገለጹት ዮሀንስ ጳውሎስ ሁለተኛ  “ የሰው ልጅ በተለያየ ምክንያት ከትውልድ ሀገሩ የመውጣት እና ወደ ትውልድ ሀገሩም ተመልሶ የመግባት መብት አለው፣ የተሻለ ሥራ በመፈለግ ወደ ሌሎች ሀገራት የመሄድ መብት አለው” በማለት ጨምረው መገለጻቸው የሚታወስ ሲሆን በዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ በመግባት የተሻለ ሥራን ለመሥራት በማሰብ ከገዛ ሀገራቸው ተሰደው ወደ ሌላ ሀገር የሚሄዱ በቋሚ ወይም ወቅታዊ በሆኑ ሥራዎች ላይ የተሳተፉ ሥራተኞች ሰብዓዊ መብታቸው ሊከበር እንደ ሚገባ” በአጽኖት የሚገልጽ ሐዋሪያዊ መልእክት ነው።

“ድሆች በተለያዩ ሀገራት ውስጥ በሚገኙ የሥራ ቦታዎች ውስጥ የሚደረግባቸው ብዝበዛ ውጤቶች ናቸው” በማለት በላቲን ቋንቋ “Laborem Exercens በሚል አርእስት የጉልበት ሥራን በተመለከተ እ.አ.አ በ1981 ዓ.ም ጳውሎስ ሁለተኛ ለንባብ ባበቁት ሐዋሪያዊ መልእክታቸው ላይ እንደ ግለጹት “ሥራ አጥነታቸውን በመመልከት - በጣም ከመጠን ያነሰ ክፍያን በመፈጸም” በድሆች ላይ የሚፈጸመውን ይህንን ኢሰብኣዊ ተግባር በማስወገድ “ተገቢ የሆነ ደሞዝ በመክፈል፣ የሥራተኞችን እና እነዚህ ሠራተኞች የሚያስተዳድሩዋቸውን ቤተሰቦች ማኅበራዊ ደኅንነት እና ማኅበራዊ ዋስትና ማረጋገጥ የገባል” በማለት በአጽኖት መገለጻቸው ያታወሳል።

ደረጃውን የጠበቀ ሥራ

የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት በነዴክቶስ 16ኛ በላቲን ቋንቋ Caritas in Veritate በሚል አርእስት በእውነት መንፈስ ሊፈጸም ስለሚገባቸው በጎ ተግባራት በሚያወሳውና እ.አ.አ በ2009 ዓ.ም ለንባብ ባበቁት ሐዋሪያዊ መልእክት እንደ ገለጹት “አንድ ደረጃውን የጠበቀ ሥራ ማለት ምን ማለት ነው?” የሚለውን መሰረታዊ ጥያቄ አንስተው እንደ ነበረ የሚታወስ ሲሆን ሲመለሱም “አንድ ደረጃውን የጠበቀ ሥራ ማለት - ሥራ በሁሉም ማህበረሰብ ውስጥ የእያንዳንዱ ወንድና ሴት መሰረታዊ ክብር መግለጫ ሲሆን እና - በነፃነት የተመረጠ ሥራ፣ ሰራተኞችን፣ ወንዶችንና ሴቶችን፣ በአጠቃላይ መላውን የኅብረተሰብ ክፍል የሚየግዝ እና የሚደግፍ ሥራ ሲሆን ሥራ ደረጃውን የጠበቀ ነው ለማለት ይቻላል” ማለታቸው ይታወሳል። በዚህ መንገድ የሚሰራ ሥራ ሰራተኞች ከማንኛውም አድልዎ እንዲጠበቁ ያደርጋል፣ ለቤተሰቦቻቸው የሚያስፈልጉዋቸውን ነገሮች ለማሟላት እና ልጆቻቸውን ለማስተማር የሚፈቅድ ሥራ እንዲሆን ይረዳል፣ ልጆቻቸውም በሚያድጉበት ወቅት ለሥራ ተነሳሽነት እንዲኖራቸው ያበረታታል፣ ሰራተኞች በነፃነት እንዲያደራጁ እና ድምፃቸውን እንዲሰሙ ያስችላል፣ በግለሰብ፣ በቤተሰብ እና በመንፈሳዊ ሕይወት ውስጥ በበቂ ሁኔታ እንዲሳተፉ የሚያደርግ ሥራ፣ ይህም ጡረታ ለሚወጡ ሠራተኞች ክብራቸውን የሚያረጋግጥ የሥራ ሁኔታ ነው” በማለት መገለጻቸው ይታወቃል።

አከባቢያዊ ተጽኖ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በላቲን ቋንቋ Laudato si” በአማሪኛው “ወዳሴ ለአንተ ይሁን” በሚል አርእስት የጋራ የመኖሪያ ቤታችንን እንከባከብ የሚል ጭብጥ ዙሪያ የሰው ልጅ ሥራ እና አከባቢያዊ ተጽኖዎች በቀጥታ ይሁን በተዘዋዋሪ እንደ ሚገኛኙ በሚያወሳው እና እ.አ.አ. በ2015 ዓ.ም ለንባብ ባበቁት ሐዋሪያዊ መልእክታቸው እንደ ገለጹት "በአካባቢ ላይ እየደርሰ ያለውን የስነ-ምዕዳር ተጽኖ ለማወቅ የሚደረጉ ጥናቶች አንድ የታለመለትን ግብ የመታ የስራ እቅድ ለማዘጋጀት ታስቦ መደረግ የሚገባ ጥናት ወይም እንዲሁ ለይስሙላ የተለያዮ እቅዶችን እና ፖሌቲካዊ የሆኑ ፖሊሲዎችን ለማጸደቅ ታቅዶ መደረግ የሚገባው ተግባር መሆን እንደ ሌለበት መገለጻቸው ይታወሳል። ነገር ግን በአከባቢ ላይ የሚደርሰውን ተጽኖ ለማወቅ የሚደረጉ ጥናቶች የሥራው ሁኔታና በሰዎች የአካልና የአእምሮ ጤንነት፣ በአካባቢያዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ በደኅንነት ላይ ካለው ተፅዕኖ ጋር በተያያዘ መልኩ ሊደረግ የገባዋል” ማለታቸው ይታወሳል። በተጨማሪም በአከባቢ ላይ እየደርሰ የሚገኘውን ስነ-ምዳራዊ ተጽኖን በይበልጥ ለመረዳት የሚደረጉ ጥናቶች ሁልጊዜም ቢሆን የተለያዩ አመለካከቶችን፣ መፍትሄዎችን እና አማራጮችን ሊያመጡ ከሚችሉ የተለያዩ ማኅበራዊ ተዋናዮችን ሁል ጊዜ ማሳተፍ ተገቢ እንደ ሆነ በሰፊው የገልጻል።

ሥራ ቅድሚያ የሚሰጠው ክርስቲያናዊ ጉዳይ ነው

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እ.አ.አ በግንቦት 27/2017 ዓ.ም በጄኖቫ ከወጣቶች ጋር በነባራቸው ቆይታ እንድ ገለጹት “የሰው ልጅ ተቀዳሚ ትኩረት ሥራ ነው” ማለታቸው የሚታወስ ሲሆን የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ማኅበራዊ አስተምህሮ መቸም ጊዜ ቢሆን ለሥራ ቅድሚያ መስጠት እንዳለበት በተደጋጋሚ እንደ ሚያሳስብ የሚታወስ ሲሆን በተጨማሪም “ሥራ ቅድሚያ የሚሰጠው ክርስቲያናዊ ጉዳይ ነው” በማለት ሥራ በሰው ልጆች ሕይወት ውስጥ ያለውን ከፍተኛ መሰረታዊ የሆነ ሚና ያሳያል። በዚህ መሰረት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዚህ ጭብጥ ላይ ተመርኩዘው “የሰዎችን ስራ ማሰናከል ወይም ሰዎችን ተጠቅሞ ያልተገባ ሥራን ማከናወን ወይም ያለተገባ ደሞዝ መክፈል፣ ከዚህ ቀደም እንደ ነበረው ሁሉ ሕገመንግሥትን የሚጻረር ተግባር ነው” ማለታቸው ይታወሳል።

ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን በድምጽ የቀረበውን ዘገባ ያዳምጡ
10 August 2018, 16:03