ፈልግ

ከጣሊያን ከተሞች የተወጣጡ ወጣት መንፈሳዊ ነጋዲያን በሮም ከተማ መሰባሰባቸው ተገለጸ።

ከጣሊያን ከተሞች የተወጣጡ ወጣት መንፈሳዊ ነጋዲያን በሮም ከተማ መሰባሰባቸው ተገለጸ።

ከተጣሊያን ከተሞች የተውጣጡ በቁጥር ከ70 ሺ በላይ የሚሆኑ መንፈሳዊ ነጋዲያን ከሳምንት በፊት የቀናት ጉዞ አድርገው በነሐሴ 05/2010 ዓ.ም ሮም ከተማ መድረሳቸውን ለቫቲካን ሬዲዮ ከደረሰው መረጃ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ይህ ወጣቶቹ ያደረጉት መንፈሳዊ ጉዞ በአስተንትኖ እና በጸሎት የታጀበ እንደ ነበረ ከደርሰን መረጃ ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህ ዜና አጠናቃሪ መብራቱ ኃይሌጊዮርጊስ-ቫቲካን

እነዚህ ከ70 ሺ በላይ የሚሆኑ ከተለያዩ የጣሊያን ግዛቶች የተውጣጡ ወጣቶች ወደ ሮም ከተማ ያደረጉትን መንፈሳዊ ጉዞ ከሳምንት በፊት መጀመረቸው የተገለጸ ሲሆን በርካታ ኪሎ ሜትሮችን በእግር አቆራርጠው በነሐሴ 05/2010 ዓ.ም በሮም ከተማ በሚገኘው ቺርኮ ማክሲሞ በመባል በሚታወቀው ስፍራ ተገኝተው ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጋር በጋር ጸሎት ማድረጋቸው እና ቅዱስነታቸውም በዚያ ለነበሩ ከ70 ሺ በላይ ወጣቶች ንግግር ማድረጋቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

ቤተ ክርስቲያን በሺዎች በሚቆጠሩ መንገዶች እየተጓዘች ትገኛለች

በነሐሴ 05/2010 ዓ.ም በሮም ከተማ የተገኙት ከ70 ሺ በላይ የሚሆኑ ወጣቶች በጣሊያን ከሚገኙ ከ195 ሀገረ ስብከቶች የተወጣጡ እንደ ሆነ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ይሁን እንጂ ወጣቶቹ ከተለያዩ ሥፍራዎች እና የተለያየ መንገድ ተከትለው የመጡ ቢሆንም ቅሉ ነገር ግን ሁሉም በአጋራ አንድ በሚያደርጋቸው መልኩ ለሣምንት ያደርጉት የእግር መንፈሳዊ ጉዞ በጸሎት እና በአስተንትኖ መንፈስ መደረጉ በዚህ መንፈሳዊ ጉዞ ወቅት የነበረውን የዓላማ አንድነት እና ትስስር ያንጸባረቀ እንደ ነበረ ለመረዳት ትችሉዋል።

13 August 2018, 15:35