ፈልግ

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ የብጹዕ ጳውሎስ 6ኛ መካነ መቃብር ሥፍራ ተገኘትወ ጸሎት አደርጉ ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ የብጹዕ ጳውሎስ 6ኛ መካነ መቃብር ሥፍራ ተገኘትወ ጸሎት አደርጉ 

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ የብጹዕ ጳውሎስ 6ኛ መካነ መቃብር ሥፍራ ተገኘትወ ጸሎት አደርጉ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የብጹዕ ጳውሎስ 6ኛ መካነ መቃብር በሚገኝበት በቫቲካን ተገኘትወ ጸሎት ማድረጋቸው ተገለጸ።

ቅዱስነታቸው በቫቲካን ከተማ ውስጥ በሚገኘው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ሀውልት በሚገኝበት የሉርድ ማሪያም ዋሻ አጠገብ  በትላንትናው እለት ማለትም በሐምሌ 30/2010 ዓ.ም ተገኝተው ጸሎታቸውን ካደረሱ በኋላ በመቀጠል በትላንትናው እለት ብጹዕ ጳውሎስ 6ኛ ከእዚህ ዓለም በሞት የተለዩበት 40ኛው አመት የተዘከረበትን ቀን ምክንያት በማድረግ  በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ የምድር ቤት ውስጥ በሚገኘው የብጹዕ ጳውሎስ 6ኛ መካነ መቃብር በሚገኝበት ሥፍራ ተገኘተው ጸሎት ማድረሳቸውን ከቫቲካን ሬዲዮ ያገኘነው መረጃ ያስረዳል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኋይሌጊዮርጊስ-ቫቲካን

ብጹዕ ጳውሎስ እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በነሐሴ 06/1978 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው የሚታወስ ሲሆን ይህንን በተመለከተ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሐምሌ 29/2010 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን አስተላልፈው በነበረው ሳምንታዊ መልእክት ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት “ብጹዕ ጳውሎስ 6ኛ በዚህ ዘመናዊ በሚባል ዓለማችን ኑረው ያለፉ ‘ዘመናዊ የነበሩ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት እንደ ሆኑ’” መግለጻቸው ይታወሳል።

በወቅቱ እርሳቸው በሕይወት ዘመናቸው ላከናወኑዋቸው ተግባራት በሙሉ ምስጋና እያቀረብን በተጨማሪም እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በሚቀጥለው ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም ለእርሳቸው ስመተ ቅድስና ማዕረግ የሚሰጥበትን ቀን በጉጉት እንጠባበቃለን ማለታቸውን ከስፍራው ከደረሰን ዜና ለመረዳት ተችሉዋል። “ብጹዕ ጳውሎስ 6ኛ ባሉበት በሰማይ ቤት ሆነው በሕይወት ዘመናቸው እስከ መጨረሻ ጊዜያቸው ድረስ በጣም አጥበቀው ለሚወዱዋት ቤተ ክርስቲያን እና ለዓለም ሰላም ማማለዳቸውን ይቀጥላሉ” ማለታቸውንም መዘገባችን የሚታወሳል።

ብጹዕ ጳውሎስ 6ኛ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በመሆን በወቅቱ የነበሩትን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ 23ኛን በመተካት እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከ1963-1978  (ለ15 ዓመታት ያህል ማለት ነው) 262ኛው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በመሆን መመረጣቸው ይታወሳል።

በጹዕ ጳውሎስ 6ኛ በሕይወት ዘመናቸው እና በ15 ዓመታት የርዕሰ ሊቃነ ጵጵስናቸው ዘመን ካከናወኑዋቸው አብይት ተግባራት መካከል በዋነኝነት የሚጠቀሰው እና በወሳኝነት የሚገለጸው እንደ አውሮጳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በጥቅምት ወር 1962 ዓ.ም. በወቅቱ ከእርሳቸው በፊት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነበሩት በዮሐንስ 23ኛ የተጀመረውን ሁለተኛውን የቫቲካን ጉባሄ አስቀጥለው እ.አ.አ. 1965 ዓ.ም 16 ሰንዶችን በማጽደቅ እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ እና በጥበብ የተሞላ መንፈሳዊ አመራር የሰጡ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በመሆናቸው በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ዘወትር እንዲወሱ ከሚያደጋቸው አበይት ተግባሮቻቸው ውስጥ በቅዳሚነት የሚጠቀስ ነው።

07 August 2018, 15:01