ፈልግ

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ፡- በትዳር ውስጥ ያለው ፍቅር ከእግዚኣብሔር የተሰጠ ልዩ ስጦታ ነው!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዘወትር ረዕቡ እለት በቫቲካን በሚገኘው የጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ ወይም ደግሞ እዳስፈላጊነቱ እና እንደ አየሩ ሁኔታ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በተለያዩ አርእስቶች ላይ ተመርኩዘው የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። በዛሬው ዕለት ማለትም በነሐሴ 2/2010 ዓ.ም በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እንደ ወትሮ ከዚህ ቀደም በተከታታይ በዐስርቱ ትዕዛዛት ዙርያ ሲያቀርቡት የነበረው የጠቅላላ የትምህርተ  ክርስቶስ አስተምህሮ ቀጣይ ክፍል እንዳልነበረ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ይህም የሆነበት ምክንያት ቅዱስነታቸው ከባለፈው ከነሐሴ 19-20/2010 ዓ.ም በአየርላንድ ዋና ከተማ በደብሊን ያደርጉት 24ኛው ሐዋርያዊ ጉብኝት የተነሳ ልማዳዊ በሆነ መልኩ ማነኛውንም ሐዋርያዊ ጉብኝት አጠናቀው ወደ ቫቲካን በሚመለሱበት ወቅት ሐዋርያዊ ጉብኝታቸውን የተመለከተ መልእክት የማስተላለፍ ልምድ በመኖሩ የተነሳ እንደ ሆነ ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በዚህ መሰረት በዛሬው እለት ማለትም በነሐሴ 23/2010 ዓ.ም ቅዱስነታቸው በጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ፈንታ በአየርላንድ ዋና ከተማ በደብሊን አድርገውት የነበረውን 24ኛው ሐዋርያዊ ጉብኝታቸውን በተመለከተ አጠቃላይ የሁለት ቀን ቆያታቸውን በመዳሰስ እና በመገምገም በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን መልክት ማስተላለፋቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች የዚህን መልእክት ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው እናቀርብላችኋለን፣ ተከታተሉን።

በዕለቱ የተነበበው የእግዚኣብሔር ቃል. . .

እግዚአብሔርን የሚፈሩት ሁሉ፥ በመንገዶቹም የሚሄዱ ምስጉኖች ናቸው። የድካምህንም ፍሬ  ትመገባለህ፤ ምስጉን ነህ መልካምም ይሆንልሃል።  ሚስትህ በቤትህ እልፍኝ ውስጥ እንደሚያፈራ ወይን ናት፤ ልጆችህ በማዕድህ ዙሪያ እንደ ወይራ ቡቃያ ናቸው። እነሆ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው እንዲህ ይባረካል። እግዚአብሔር ከጽዮን ይባርክህ፤ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ፥ የኢየሩሳሌምን መልካምነትዋን ታያለህ።  የልጆችህንም ልጆች ታያለህ። በእስራኤል ላይ ሰላም ይሁን (መዝ.128፡ 1-6)።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ በዓለማቀፍ የቤተሰብ ቀን ላይ ለመገኘት ወደ አየርላንድ ሄጄ ነበር። ከሁሉም በላይ የእኔ በዛ መገኘት የክርስቲያን ቤተሰቦች ጥሪ እና ተልዕኮ ምን እንደ ሆነ ለማረጋገጥ ነበር። በሺዎች የሚቆጠሩ ቤተሰቦች፣ ባለትዳሮች፣ አያቶች እና ልጆች በዲብሊን መሰብሰባቸው የተለያዩ ቋንቋዎች፣ ባሕሎች እና ልምዶቻቸውን ይዘው መጥተው በዚህ ዓለማቀፍ የቤተሰብ ቀን ላይ መሳተፋቸው የእግዚአብሄር ሕላዌ ውበት የሚያንፀባርቁ ናቸው። የእግዚአብሄር ሕልም የታማኝነት፣ የይቅርታ እና እርሱ ራሱ በክርስቶስ አማካይነት የሰጠን የእርቅ ፍሬዎች የሆኑት አንድነት፣ኅብረት እና ሰላም ናቸው። ቤተሰቦች በዚህ ህልም ውስጥ እንዲሳተፉ እና ማንም ብቸኛ፣ የተገለለ ወይም የማይፈለግ ሳይሆን አንድ ሆኖ የሚኖርበት ቤተሰብ እንዲሆን ያደርገዋል። በዚህም  አግባብ ለዚህ ዓለማቀፍ የቤተሰብ ቀን የተመረጠው “የቤተሰብ መልካም ዜና ለዓለም ሁሉ ደስታ ነው” የሚለው መርዕ ቃል ተስማሚ የሆነ መርህ ቃል ነበር ማለት ነው።

የአየርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ የተለያዩ የመንግሥት ባለስልጣናትን እና የሲቪል ማኅበርሰበ ተወካዮች፣ የሐይማኖት መሪዎች በሙሉ በዚህ ዓለማቀፍ የቤተሰብ ቀን ላይ የተከናወኑትን ክስተቶች በሙሉ ስላዘጋጁ እና በመተባበር በሰላም እንዲጠናቀቅ በማድረጋቸው በሁሉም ደረጃ የሚገኙትን ሰዎች በሙሉ ለማመስገን እወዳለሁ። በደብሊን ቤተ መንግስት ውስጥ ከባለስልጣኖች ጋር በነበረኝ ቆይታ ቤተ ክርስቲያን የቤተሰቦች ቤተሰብ ናት፣ እንደ አካል የተለያየ አስተዋጾ ያላቸውን የተለያዩ ሴሎችን አጠቃሎ እንደ ሚይዝ ሁሉ በዚህም መልኩ እንዲሁም እያንዳንዱ ቤተሰብ በአንድነት በወንድማማችነት እና በጠንካሬ መንፈስ የማህበረሰብ እድገት ለማምጣት እጅግ አስፈላጊ ሚና እንዳላቸው ገልጨ ነበር።

በእነዚህ ቀናት ውስጥ እውነተኛዎቹ "የብርሃን ነጥቦች" የነበሩት በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ የነበሩ ባለትዳሮች የሰጡት የደስታ እና የፍቅር ምስክርነት ነው። እነርሱ በታሪካቸው በትዳር ውስጥ ያለው ፍቅር ከእግዚአብሔር ዘንድ የሰጠ ልዩ ስጦታ መሆኑን፣ በቤተሰብ ውስጥ በየቀኑ እንዲያድግ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን እንድናስታውስ አድርገውናል። በተጨማሪም እምነት በየዕለቱ ሕይወታቸው ውስጥ እንዴት እንደ ረዳቸው፣ "በቤት ጠረጴዛ ዙሪያ" እንዴት እንደሚከናወን በማሳየት ይህንንም መልካም ምሳሌ በቤተ ክርስቲያን እና በአጠቃላይ በመላው ማኅበርሰብ ውስጥ እንዲስፋፋ ያደርገዋል።

ቀዳማዊ በሆነው በደብሊን በሚገኘው ካቴድራል ውስጥ በነበረኝ ቆይታ ይህንን የቤተሰብ ቀን ለማክበር በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የነበሩ ብዙ የትዳር ጉደኛሞችን፣ ወጣት ባለትዳሮችን እና እንዲሁም ብዙ ሕጻናትን አግኝቻቸው ነበር። ከዛም አንዳንድ ተግዳሮቶች እና ችግሮች ያጋጠሟቸውን አንዳንድ የቤተሰብ አባልት አግኝቼ ነበር። ለፍራንቸስካዊያን ማኅበር ወንድሞች እና በአጠቃላይ ለቤተ ክርስቲያን ማኅበርሰብ ምስጋና ይድረሳቸውና በዚህ ዓይነት ችግር ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን በመደገፍ ለእነርሱ ያላቸውን አጋርነት በመግለጽ ላይ ይገኛሉ።

በጉብኝቴ ወቅት በጣም ደስታን ከፈጠሩብኝ ነገሮች መካከል ዋነኛዎቹ የነበሩት ቅዳሜ ማታ የተከበረው የቤተሰብ ቀን እና እሁድ በፎኒክስ ፓርክ ተከናውኖ የነበረው መስዋዕተ ቅዳሴ ነበር። ቅዳሜ ምሽት ላይ በተከበረው የቤተሰብ ቀን ላይ በጦርነት የተጎዱ ቤተሰቦች፣ በእርቅ መንፈስ አማካይነት ተመልሰው አንድ እንዲሆኑ የተደረጉ ቤተሰቦች፣ ከሱሰኝነት ነጻ የወጡ ቤተሰቦች፣ የሞባይል ስልኮቻቸውን እና ታብሌቶቻቸውን በአግባቡ መጠቀም የጀመሩ ቤተሰቦች እና ለቤሰብ ትክክለኛ የሆነ ጊዜ መስጠት እንደ ሚኖርባቸው የተማሩ ሰዎችን ምስክርነት አዳምጠናል። ይህም ውጤት ሊገኝ የቻለው ለትውልድ ሲተለለፍ በመጣው እና አያቶች ከሚጫወቱት ከፍተኛ ሚና የተነሳ በቤተሰብ መካከል ያለውን ትስስር በማጠናከር እና የእግዚአብሄር ወድ  ስጦታ በሆነው በእምንት አማካይነት ነው።

እሁድ ዕለት ጥዋት ላይ በአየርላንድ ሕዝቦች በጣም ተወዳጅ የሆነውን የኖክ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተመቅደስ ለመጎብኘት ወደ እዚያው አቅንቼ ነበር። በዚያው ስፍራ በሚገኘው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተገልጻ በነበረችበት ስፍራ ላይ በነበረው የጸሎት ቤት ተገኝቼ መላውን የዓለም ቤተሰብ በተለይም ደግሞ የአየርላንድ ሕዝቦችን በእናንትነት ጥበቃዋ እንድተከልላቸው በአደራ ሰጥቻታለሁ። ይህ ሐዋርያዊ ጉብኝት ሰሜን አየርላንድን ያላካተተ ጉብኝት መሆኑን በሚገባ ባውቅም ነገር ግን ለሰሜን አየርላድ ሕዝብ ሰላምታዬን በማቅረብ እርቅ፣ ሰላም፣ ወዳጅነት እና ማኅበራዊ ትስስር የሰፈነበት ማኅበርሰብ እንዲመሰርቱ አበረታትቻቸዋለሁ።

በዚህ በአየርላድ በነበረኝ ቆይታ ከተሰማኝ ከፍተኛ ደስታ ባሻገር በእዚያ ሀገር በተለያየ ሁኔታ በቤተ ክርስቲያን ሰዎችም ሳይቀር በተፈጸሙት በደሎች ከፍተኛ እና መራራ የሆነ ሐዘን ተስምቶኝ የነበረ ሲሆን ቀደም ሲል የነበሩ የቤተ ክርስቲያን ኃላፊዎች ይህንን ጉዳይ በተገቢው ሁኔታ መፈታት እንደ ነበረበት ባለማወቃቸው የተነሳ የተፈጸመ ወንጀል ነው። የዚህ ጥቃት ሰላብ ከሆኑ ሰዎች ጋር ተገናኝቼ የተሰማኝን ጥልቅ ሐዘን ገልጬ የነበረ ሲሆን ለእነዚህ ኃጢኣቶች በሙሉ እግዚኣብሔር ምሕረቱን እንዲሰጠን አሎት አቅርብያለሁ። በአየርላንድ ከሚገኙ ብጹዕን ጳጳሳት ጋር በተገናኘውበት ወቅት የዚህ ዓይነቱ ጥቃት ተመልሶ እንዳይፈጸም ከፍተኛ የሆነ ሥራ መስራታቸውን እና ከመንግሥት ባለስልጣናት ጋር በጋራ የተለያዩ ጠበቅ ያሉ ሕጎችን በማውጣት ላይ እንደ ሚገኙ፣ ወጣቶችን ከማነኛውም ጥቃት ለመከላከል ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን አዳምጫለሁ።

ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ በአየርላንድ ተከናውኖ የነበረው ዓለማቀፍ የቤተሰብ ቀን ትንቢታዊ በሆነ መልኩ በጣም ብዙ ቤተሰቦችን ያጽናና እና ብዙ ቤተሰቦች በሐይማኖታዊ መንገድ በቤተሰብ ሕይወት ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆኑ ያስቻለ አጋጣሚ ነበር፣ የቤተሰብ አባላት ሐዋርያ እና ሚስዮናዊያን እንዲሆኑ፣ የመላካም ተግባር እርሾ እንዲሆኑ፣ በሰላም፣ በቅድስና እና በፍትህ እንዲኖሩ ግንዛቤ የፈጠረ አጋጣሚ ነበር። የሚቀጥለው ዓለማቀፍ የቤተሰብ ቀን እ.አ.አ አቆጣጠር በ2021 ዓ.ም በሮም ከተማ የሚካሄድ ሲሆን ይህንን ዓለማቀፍ የቤተሰብ ቀን የቅዱስ ቤተሰብ አባላት ለሆኑት ለኢየሱስ፣ ለማርያም እና ለዮሴፍ በአደራ እንሰጣለን፣ ምክንያቱም በየቤታችን፣ በእየቁምስናዎቻችን እና በእየማኅበረሰቦቻችን ውስጥ በእውነተኛ መንገድ “ለዓለም የደስታ ምንጭ” ይሆኑ ዘንድ ለቅዱስ ቤተሰብ በአደራ እንሰጣለን።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
29 August 2018, 14:48