ፈልግ

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ “ከኢየሱስ ሥጋ እና ደም የዘለዓለም ሕይወት ምን ማለት እንደ ሆነ እንማራለን”

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዘወትር እሁድ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን፣ መንፍሳዊ ነጋዲያን እና የሀገር ጎብኝዎች በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተመርኩዘው የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ እንደ ምያደርጉ ይታወቃል። በዚህ መስረት በትላንትናው እለት ማለትም በሐምሌ 13/2010 ዓ.ም ያሰሙት የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ በእልቱ “ከሰማይ የወረደ ሕያው እንጀራ እኔ ነኝ፤ ማንም ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘላለም ይኖራል፤ ይህም እንጀራ፣ ለዓለም ሕይወት እንዲሆን የምሰጠው ሥጋዬ ነው”(ዮሐ 6፡51-58) በተጠቀሰው በኢየሱስ ቃላቶች ላይ መሰረቱን ያደርገ እንደ ነበረ ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህ አስተንትኖ አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስት ፍራንቸስኮስ በትላንትናው እለት ማለትም በነሐሴ 13/2010 ዓ.ም በዕለቱ ቅዱስ ወንጌላ ላይ ተመርኩዘው ያሰሙትን አስተንትኖ ሙሉ ይዘት እንደ ምከተለው ተርጉመነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

በዛሬው እለት ሰንበት የተነበበልን ቅዱስ ወንጌል (ዩሐንስ 6፡51-58) ኢየሱስ በአምስት ዳቦ እና በሁለት ዓሳዎች በጣም ብዙ የሆኑ ሕዝቦችን ከመገበ በኋላ በቅፍርናሆም ምኩራብ ውስጥ የሰበከው ሁለተኛ ስብከት እንደ ሆነ ያሳየናል። ኢየሱስ ራሱን “ከሰማይ የወረደ ሕያው የዘለዓለም ሕይወት የሚሰጥ እንጀራ” እንደ ሆነ አድርጎ ራሱን በማቅረብ ይህም እንጀራ፣ ለዓለም ሕይወት እንዲሆን የምሰጠው ሥጋዬ ነው” (ቁ. 51) በማለት ያክልበታል። ይህ የወንጌል ክፍል በጣም ወሳኝ የሚባል ክፍል ሲሆን እንዲያውም ይህንን መልእክት ሲሰሙ የነበሩ ሰዎች እርስ በእርሳቸው ከፍተኛ የሆነ ውይይት በማድረግ እንበላ ዘንድ ይህ ሰው ሥጋውን እንዴት ሊሰጠን ይችላል?” (ቁ. 52) በማለት ጥያቄ ማንሳት ይጀምራሉ። አብረውት የተካፈሉት እንጀራ  ራሳቸውን እስከ መጨረሻ ድረስ መስዋዕትነት እስከ መክፈል ድረስ አሳልፎ መስጠት የሚለውን እውነተኛ የሆነ ፍቺ መግለጽ በጀመረበት ወቅት አለመግባባት የፈጠራል፣ ሌላው ቀርቶ ቀደም ሲል በድል አድራጊነት መንፈስ ተሞልቶ እንዲመጣ የሚፈልጉት ሰው ሳይቀሩ እርሱን ላለመቀበል ማቅማማት ይጀምራሉ። ነገር ግን ቀደም ሲል ሕዝቡ ኢየሱስን ሊያነግሡት በፈለጉበት ወቅት ኢየሱስ ሸሽቶ እንደ ሄደ ማስታወስ ያስፈልጋል።

ፈልገውም ባገኙት ጊዜ ኢየሱስ እውነት እላችኋለሁ፤ የሰውን ልጅ ሥጋውን ካልበላችሁና ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም” (ቁ.53) በማለት ይመልስላቸዋል። ሰለዚህ ከሥጋው ጋር ደም አብሮ ሲቀርብ እናያለን። በመጽሐፍ ቅዱሳዊ አገላለጽ ስጋ እና ደም የሰውን ተጨባጭ ስብዕና ያመለክታሉ። ሕዝቡና ደቀ-መዛሙርቱ ራሳቸው ኢየሱስ ከእርሱ ጋር ኅበረት እንዲፈጥሩ፣ “እርሱን” ሰብዓዊነቱን እንዲበሉ፣ ከእረሱ ጋር በመሆን ነፍሳቸውን ለዓለም ሕይወት ለማስገኘት በስጦታነት እንዲያቀርቡ እንደ ጠየቃቸው ገምተዋል። ከድል አድራጊነት እና ከስኬት ባሻገር ኢየሱስ ለእኛ ተላልፎ የሚሰጥ መስዋዕት ነው።

ይህ የሕይወት እንጀራ፣ የኢየሱስ የሥጋው እና የደሙ ምስጢር ለእኛ በመስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት በነጻ የሚሰጠን ስጦታ ነው። በዚህ መስዋዕት በሚደረግበት በመንበረ ታቦት ዙሪያ መንፈሳዊ ጥማታችንን እና መንፈሳዊ ረሃባችንን ዛሬ እና ለዘለዓለሙ የሚያረካውን ምግብ እና መጠጥ እናገኛለን። መስዋዕተ ቅዳሴን በምንሳተፍባቸ ወቅቶች ሁሉ ሰማያዊ የሆኑ ክስተቶችን በምድር ላይ ሆነን መለማመድ እንጀምራለን፣ ምክንያቱ በክርስቶስ ሥጋ እና ደም አማካይነት የዘለዓለም ሕይወት ምን ማለት እንደ ሆነ ስለምንማር ነው። ይህ ማለት ለጌታ መኖር ማለት ነው! እርሱም የሚበላኝም እንዲሁ በእኔ የተነሣ በሕይወት ይኖራል” (57) ብሎ ተናግሯልና። ቅዱስ ቁርባን እኛ ለራሳችን ብቻ ሳይሆን ለክርቶስ እና ለእህት ወንድሞቻችን እንድንኖር ያነሳሳናል። የሕይወት ደስታ እና ዘለዓለማዊነት በቅዱስ ቁርባን አማካይነት፣ የቅዱስ ወንጌል የፍቅር እሴቶችን ገቢራዊ በማድረግ ውጤታማ ፍሬን በማፍራት ላይ መሰረቱን ያደርገ ነው።

ኢየሱስ እንደ ቀድሞ ዘመን ሁሉ ዛሬም ለእያንዳንዳችን እውነት እላችኋለሁ፤ የሰውን ልጅ ሥጋውን ካልበላችሁና ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም” (ቁ. 53) በማለት በድጋሚ ይናገራል። ወንድሞቼ እና እህቶቼ ሆይ! ይህ ጉዳይ ቁሳዊ የሆነ ምግብን የሚመለከት ጉዳይ አይደለም፣ ነገር ግን ሕይወት ያለው እና የሚበላ እንጀራ የእግዚአብሔርን ሕይወት የሚያስተላልፍ መንፈሳዊ ምግብ ነው። ቅዱስ ቁርባንን በምንቀበልበት ወቅቶች ሁሉ የእግዚአብሔርን ሕይወት እንቀበላለን ማለት ነው። ይህንን ሕይወት ለማግኘት ደግሞ ለቅዱስ ወንጌል እና ለወንድሞቻችን ያለንን ፍቅር መጎልበት አስፈላጊ ነው። ኢየሱስ ሥጋውን እና ደሙን እንድንመገብ  ግብዣ በሚያቀርብበት በአሁኑ ወቅት ልክ በዛሬ ቅዱስ ወንጌል (ዮሐ. 6፡51-58) ውስጥ እንደ ተጠቀሱ ሕዝቦች እኛም ስለእዚህ ግብዣ በመወያየት መቃወም እንዳለብን ሊሰማን ይችል ይሆናል። ይህ የሚሆነው እኛ ማንነታችን  በኢየሱስ ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ለማድረግ ስንታገል፣ በዓለም መስፈርት መሰረት ሳይሆን በእርሱ በኢየሱስ መመዘኛዎች ለመመርኮዝ ትግል በምናደርግበት ወቅት ነው። ይህንን ምግብ በመመገብ ራሳችንን ከእርሱ ስሜቶች እና ባህሪ ጋር ሙሉ በሙሉ ልናግባባ እንችላለን። ይህ በጣም አስፈላጊ የሆነ ጉዳይ ነው፡ መስዋዕተ ቅዳሴን መሳተፍና ቅዱስ ቁርባን መቀበል ማለት ከክርስቶስ ጋር ኅበረት መፍጠር እና ይህንን ሕያው ክርስቶስን መቀበል ማለት ነው፣ እርሱ ውስጣችንን በመቀየር ለሰማያዊ ሕይወት ያዘጋጀናል።

የዚህን አስተንትኖ ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማደመጥ ትችላላቹ!
20 August 2018, 15:07