ፈልግ

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ የነሐሴ ወር የጸሎት ሐሳብ-ለቤተሰብ እንክብካቤ እና ጥበቃ እንዲደረግ እንጸልይ

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ የነሐሴ ወር የጸሎት ሐሳብ “ለቤተሰብ እንክብካቤ እና ጥበቃ እንዲደረግ እንጸልይ!”

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለየወሩ የሚሆን የጸሎት ሐሳብ ለምዕመናኑ ይፋ በማድረግ ምዕመኑ እርሳቸው በሚያቀርቡዋቸው የተለያየ ዓይነት የጸሎት ሐሳቦች ላይ ተመርኩዘው ጸሎት እንዲያድጉ በየወሩ ጥሪ እንደ ሚያደጉ ይታወቃል።

የዚህ ዜና አጠናካሪ መብራቱ ኋይሌጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከሁለት ቀናት በፊት ለተጀመረው የነሐሴ ወር እንዲሆን ያቀረቡት የጸሎት ሐሳብ በአሁኑ ወቅት በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የተለያዩ ቤተሰቦች እያጋጠማቸው ለሚገኘው ተግዳሮት ጸሎት እንዲደረግ ቅዱስነታቸው በቪዲዮ ባስተላለፉት መልእክት መገለጻቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

ቅዱስነታቸው በእዚሁ በቪዲዮ ባስተላለፉት ወራዊ መልእክት እንደ ገለጹት በአሁኑ ወቅት በዓለማችን ዙሪያ በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ የቤተሰብ አባላት በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ ከፍተኛ ተግዳሮቶች እየገጠሙዋቸው እንደ ሆነ የጠቀሱት ቅዱስነታቸው “የሁለንተናችን መሰረት ለሆነው ለቤተሰብ ጥበቃ ማድረግ ይገባል” በማለት ቅዱስነታቸው በቪዲዮ ባስተላለፉት መልእክት ጨምረው ገለጸዋ።

“የቤተሰብ ሁኔታ እንዲሻሻል እና በአሁኑ ወቅት በዓለማችን በሚታየው የዘመናዊ ሕይወት የአኗኗር ዘይቤ የተነሳ በቤተሰብ ሕይወት ላይ የተጋረጠውን ከፍተኛ አደጋ ለመቀነስ፣ ከተቻለም ደግሞ ከእነአካቴው ለማስወገድ በሚደርገው ርብርብ የሲቪል ማኅበረሰብ እና የተለያዩ የንግድ ድርጅት ያላቸው አካላት በተቻላቸው መጠን ድጋፍ ማድረግ” እንደ ሚገባቸው ያሳሰቡት ቅዱስነታቸው ይህንን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት በሁሉም ማህበረሰብ ውስጥ “ለቤተሰብ ተስማሚ የሆኑ ፖሊሲዎችን ማራመድ” አስፈላጊ እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው ባስተላለፉት የቪዲዮ መልእክት ጨምረው ገለጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከሁለት ቀናት በፊት ለተጀመረው የነሐሴ ወር 2018 ዓ.ም የጸሎት ሐሳብ ይሆን ዘንድ በቪዲዮ ባስተላለፉት መልእክት “የኢኮኖሚክስ ባለሙያዎችና ፖሌቲከኞች የሚያደርጉዋቸው መነኛውም ዓይነት ከባድ ውሳኔዎች ቤተሰብን እንደ አንድ ሰብአዊ ሀብት አድጎ በመቁጠር ቤተሰብን ከጉዳት የሚታደጉ ውሳኔዎችን ያደርጉ ዘንድ እንዲረዳቸው ኢየሱስን ልንጠይቀው የገባል” ማለታቸው የተገለጸ ሲሆን በተጨማሪም “የኑሮ ጭንቀት፣ ውጥረት፣ የሥራ ጫና እንዲሁም ተቋማት ለቤተሰብ የሚሰጡት ትኩረት ማነስ ቤተሰብን ችግር ላይ ወይም አደጋ ላይ ሊጥል ይችላል” ብለዋል።

እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በ2014 ዓ.ም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ራሳቸው በወሰዱት ተነሳሽነት የካቶሊክ ቤተክርስትያን ልዩ ወይም መደበኛ ያልሆነ ሲኖዶስ በማካሄድ የቤተሰብ ሁኔታ ትኩረት እንዲሰጠው የሚያሳስብ ልዩ መደበኛ ያልሆነ ሲኖዶስ ተደርጎ ማለፉ የሚታወቅ ሲሆን በእዚህ ልዩ መደበኛ ባልሆነ ሲኖዶስ ማብቂያ ላይ ብጽዕን ካርዲናሎች እና በጹዕን ጳጳሳት ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጋር በጋር በመሆን ባወጡት ያጋር የአቋም መገለጫ መሰረታዊ መርሆች መካከል ለጋብቻ የሚደረገው ዝግጅት ከፍተኛ የሆነ ትኩረት እንደሰጠው እና በጥንቃቄ እንዲካሄድ በተጨማሪም ወላጆች የገዛ ልጆቻቸውን በስነ-ሩካቤ ዙሪያ ያላቸው አዎንታዊ ግንዛቤ እንዲጨምር ለልጆቻቸው ይህንን የስነ-ሩካቤ አዎንታዊ የስነ-ምግባር ትምህርት ሊያስተምሩ እንደ ሚገባው መግባባት ላይ ደርሰው እንደ ነበረ ይታወሳል።

“ስለ ቤተሰብ ስናገር ብዙውን ጊዜ የአንድ ውድ ነገር ምስል ወደ አእምሮዬ ይመጣል” በማለት በቪዲዮ ባስተላለፉት መልእክት የገለጹት ቅዱስነታቸው “ስለ ቤተሰብ አስፈላጊነት መናገር በራሱ ብቻውን በቂ አይደለም፣ ይህንን ተጨባጭ በሆነ መንገድ ማበረታታትና በማህበረሰቡ ውስጥ የሚጫወቱትን መልካም የሆነ ሚና እንዲያሳድጉ ማድረግ ያስፈልጋል" ብለዋል።

በዚህ አሁን እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከሁለት ቀናት በፊት በተጀመረው የነሐሴ ወር 2018 ዓ.ም የጸሎት ሐሳብ እንዲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በመላው ዓለም ለሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስትያን ምዕመናን እና በጎ ፈቃድ ላላቸው ሰዎች ሁሉ ባስተላለፉት ወራዊ ጥሪ ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት “ቤተሰብ አንድ ልዩ የሆነ ዋጋ ያለው ሐብት በመሆኑ የተነሳ በቤተሰብ መካከል ያለው ግንኙነት በጣም አስፈላጊ እንደ ሆነ” ቅዱስነታቸው መናገራቸውን ለቫቲካን ሬዲዮ ከደረሰው ዜና ለመረዳት ተችሉዋል።

02 August 2018, 15:54