ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ 

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ “ብጹዕ ጳውሎስ 6ኛ ዘመናዊ የሆኑ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ነበሩ”

 “ብጹዕ ጳውሎስ 6ኛ ዘመናዊ የሆኑ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ነበሩ”

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዘወትር እሁድ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተመርኩዘው የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ እንደ ሚያደጉ፣ ከዚያም በመቀጠል በካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ምዕመናን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማሪያም ከሚቀርቡት ጥንታዊ የመማጸኛ ጸሎቶች መከከል አንዱ የሆነውን “የእግዚኣብሔር መልኣከ ማርያምን አበሠራት”  የሚለውን ጸሎት ከምዕመናን ጋር በመቀባበል እንደ ሚደግሙ እና ከዚህም ጸሎት በመለጠቅ ለዓለም ሳምንታዊ መልእክት እደ ሚያስተላልፉ ይታወቃል።

በዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው በሐምሌ 29/2010 ዓ.ም በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተመርኩዘው የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ለምዕመኑ ካሰሙ በኋላ “የእግዚኣብሔር መልኣክ ማሪያምን አበሰራት” የሚለን ጸሎት ከምዕመኑ ጋር በመቀባበል ከደገሙ በኋላ ለዓለም ባስተለለፉት ሳምንታዊ መልእክት እንደ ገለጹት ከዓርባ ዓመታት በፊት ብጹዕ ጳውሎስ 6ኛ በዚህች ምድር ላይ የነበራቸውን የመጨረሻ ሕይወታት አገባደው እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በነሐሴ 6/1978 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው አስታውሰዋል።

ለእርሳቸው ያለንን አክብሮት ለመገለጽ እና እርሳቸው በሕይወት ዘመናቸው ላከናውኑዋቸው ተግባራት በሙሉ ምስጋናን እያቀረብን በተጨማሪም እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በሚቀጥለው ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም ለእርሳቸው የቅድስና ማዕረግ የሚሰጥበትን ቀን በጉጉት እንጠባበቃለን ማለታቸውን ከስፍራው ከደረሰን ዜና ለመረዳት ተችሉዋል። “ብጹዕ ጳውሎስ 6ኛ ባሉበት በሰማይ ቤት ሆነው በሕይወት ዘመናቸው እስከ መጨረሻ ጊዜያቸው ድረስ በጣም አጥበቀው ለሚወዱዋት ቤተ ክርስትያን እና ለዓለም ሰላም ማማለዳቸውን ይቀጥላሉ” ያሉት ቅዱስነታቸው በዚህ ዘመናዊ በሚባል ዓለማችን ኑረው ያለፉ “ዘመናዊ የነበሩ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት እንደ ሆኑ” የገለጹት ቅዱስነታቸው ለብጹዕ ጳውሎስ 6ኛ ያለንን አክብሮት “እባካችሁን በጭብጨባ” ግለጹ በማለት ለምዕመኑ ባቀረቡት ጥሪ መሰረት ምዕምኑ ለብጹዕ ጳውሎስ 6ኛ ያላቸውን አክብሮት በወቅቱ በጭብጨባ መግለጻቸውንም ለመረዳት ተችሉዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሳምንታዊ መልእክታቸው ማብቂያ ላይ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በወቅቱ ለነበሩት መንፈሳዊ ነጋዲያን ሰላምታ ካቀረቡ በኋላ እንደ ተለመደው “እባካችሁን ለእኔ መጸለይ በፍጹም እንዳትረሱ” ካሉ በኋላ ሐዋሪያዊ ቡራኬያቸውን ለግሰው መሰናበታቸውን ከስፍራው ከደረሰን ዜና ለመረዳት ተችሉዋል።

Photogallery

ምዕመናን በሐምሌ 29/2010 ዓ.ም በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ
06 August 2018, 14:41