ፈልግ

Joseph Roger O Donnell - Nagasaki Joseph Roger O Donnell - Nagasaki 

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ኒውክሊየር የጦር መሣሪያ ሙከራን አወገዙ።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በአንድ ወቅት መልዕክታቸው እንዳስገነዘቡት በማንኛውም ወቅት ሊከሰት በሚችል ስህተት ኒውክሌር የጦር መሳሪያ ወደር የማይገኝለትን ጥፋት ሊያስከትል እንደሚችል ያላቸውን ስጋት ገልጸዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ዓለም አቀፍ ጸረ ኒውክልያር መሣሪያ ሙከራ፣ ዛሬ በመላው ዓለም ታስቦ መዋሉ ታውቋል። ከዘጠኝ ዓመት በፊት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በ2001 ዓ. ም. ጸረ ኒውክሊየር መሣሪያ ቀን ታስቦ እንዲውል መደንገጉ ይታወሳል። ካለፉት ዓመታት ወዲህ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ኒውክሌር የጦር መሣሪያን በማስመልከት የተቃውሞን መልዕክቶች ሲያስተላልፉ መቆየታቸው ይታወቃል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በአንድ ወቅት መልዕክታቸው እንዳስገነዘቡት በማንኛውም ወቅት ሊከሰት በሚችል ስህተት ኒውክሌር የጦር መሳሪያ ወደር የማይገኝለትን ጥፋት ሊያስከትል እንደሚችል ያላቸውን ስጋት ገልጸዋል። በመሆኑም የኒውክሌር የጦር መሳሪያ ሙከራን መቃወምና ማውገዝ ያስፈልጋል ብለዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ያለፈው ዓመት ወደ ባንግላደሽ ባደረጉት ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው ወቅት እንደገለጹት አሁን የምንገኝበት ወቅት ኒውክሌር የጦር መሣሪያ ሙከራ ወደ ከፍተኛ ደረጃ የደረሰበት እንደሆነ ገልጸው መጨረሻውም ለርካታ የሰው ልጅ ሕልፈት እንዲሁም ለንብረት ውድመት ምክንያት እንደሚሆን ያላቸውን ስጋት ገልጸዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ዘንድሮ በጥር ወር ላይ ወደ ቺሊ ባደረጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት ወቅት ለጋዜጠኞች ያደሉት ፎቶግራፍ፣ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት እጅግ በተጎዳችውና የጃፓን ከተማ በሆነችው በናጋሳኪ ሁለት ሕጻናት ቆመው የሚታዩበት እንደሆነ ይታወሳል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ዘንድሮ በግንቦት ወር በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ላይ ለተሰበሰቡት ምዕመናን ባስተላለፉት መልዕክት አንደገለጹት፣ የሁለቱ አገሮች መሪዎች ማለትም የሰሜን ኮሪያና የደቡብ ኮሪያ መሪዎች በመካከላቸው ያለውን ልዩነት አስወግደው ከጦርነት ነጻ የሆኑ አገሮች እንዲሆኑ በጋራ ጸሎት መተባበር እንደሚያስፈልግ ማሳሰባቸው ይታወሳል።   

31 August 2018, 16:42