ፈልግ

2018.08.12 Angelus 2018.08.12 Angelus 

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ ትናንት እሁድ ከእኩለ ቀኑ የብስራተ ገብርኤል ጸሎት በኋላ ያስተላለፉት መልዕክት።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ዘወትር እሁድ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡት ምዕመናን፣ መንፈሳዊ ነጋዲያን እና የሀገር ጎብኚዎች፣ ለእለቱ የቀረበውን ሁለተኛ ንባብ በመመርኮዝ አስተንትኖ ካቀረቡ በኋላ መልዕክትም አስተላልፈዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን-ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በአደባባዩ ለተሰበሰቡት፣ ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች ለመጡት እንግዶች በሙሉ ሰላምታቸውን አቅርበዋል። በመቀጠልም በኢጣሊያ ከሚገኙ 195 ሃገረ ስብከቶች፣ በጳሶቻቸው፣ ቆሞሶቻቸውና ትምህርተ ክርስቶስ አስተማሪዎቻቸው በመታጀብ ወደ ሮም የመጡ፣ ከ70 ሺህ በላይ ለሚገመቱ ወጣቶችም ሰላምታቸውን አቅርበውላቸው በሮም ባደሩጉት የሁለት ቀን ቆይታ ወቅት ላቀረቡት ክርስቲያናዊ ምስክርነት አመስግነዋቸዋል። ቀጥለውም ለወጣቶች ሐዋሪያዊ እንክብካቤን በመስጠት ዘወትር ስለረዷቸው ይህንን አገልግሎት ለመስጠት ላደረጉት ትዕግስት ምስጋናቸውን አቅርበው ከካህናት ጋር በመተጋግገዝ አገልግሎታቸውን ላበረከቱት ደናግልም ምስጋናቸውን አቅርበውላቸዋል።  

ቅዱስነታቸው በመቀጠልም መንፈሳዊ ንግደት በማዘጋጀትና በማስተባበር ትልቅ የአገልግሎት ድርሻቸውን ፍሬያማ በሆነ መንገድ የተወጣውን የኢጣሊያ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤን፣ የወጣቶች ሐዋርያዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤትን፣ በብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዚዳንት በሆኑት በብጹዕ ካርዲናል ጓልቲየሮ ባሰቲ ስም አመስግነዋል።

ቅዱስነታቸው በመጨረሻም ለወጣቶቹ ባስተላለፉት መልዕክታቸው ወደየ መጡበት ሀገረ ስብከት ሲመለሱ እውነተኛ ምስክርንርትን እንዲሰጡ፣ በሮም ባደረጉት የሁለት ቀን ቆይታ የተመለከቱትን የወንድማማችነት ፍቅር፣ በጋራ ስላቀረቡት ጸሎት እና በመንፈሳዊ ጉዞ የቀሰሙትን ልምድ ለሌሎችም እንዲያካፍሉ አደራ ብለዋል። ወደ መጡበትም በሰላም እንዲገቡ ተመኝተው፣ ወጣቶቹ በጸሎታቸው እንዲያስታውሷቸው አደራ ብለዋል።     

13 August 2018, 15:53