ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከካርዲናል ኦ ማሌይ ጋር ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከካርዲናል ኦ ማሌይ ጋር 

ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮስ፡ በሕጻናት ላይ የሚፈጸሙትን ማነኛውም ዓይነት ጥቃቶች መታገስ አይገባም!!

ለታዳጊ ሕጻናት ጥበቃ የሚያደርግው ጳጳሳዊ ኮምሽን በሕጻናት ላይ የሚደርሱ ማነኛውም ዓይነት ጥቃቶች በትዕግስት መታለፍ እንደሌለባቸው አስታወቀ።  በቅድስት መንበር ሥር የሚተዳደረው ለታዳጊ ሕጻንት ጥበቃ የሚያደርገው ጳጳሳዊ ኮምሽን በነሐሴ 15/2010 ዓ.ም ይፋ ባደረገው መልእክት እንደ ገለጸው በቤተ ክርስቲያን ጥላ ሥር የሚገኙ በማነኛው የእድሜ ደረጃ ላይ በሚገኙ ታዳጊ ሕጻናት ላይ የሚፈጸመውን አካላዊ፣ ስነ-አእምሮኣዊ እና ወሲባዊ ጥቃት በከፍተኛ ደረጃ እንደ የሚቃወመው እና በፍጹም በትዕግስት ሊታለፍ የማይገባው ጥቃት መሆኑን መገለጹን ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ- ቫቲካን

ኮሚሽኑ ይህንን መግለጫ ያወጣው በቅርቡ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ በሕጻንት ላይ የተፈጸሙትን እና እየተፈጸሙ የሚገኙትን አካላዊ፣ ስነ-አእምሮኣዊ እና ወሲባዊ ጥቃቶች በማውገዝ ያስተላለፉትን መልእክት ተከትሎ ይህንን የቅዱስነታቸውን ጠንካራ መልእክት ለመደገፍ ባወጣውም መገለጫ እንደ ሆነ ለቫቲካን ዜና ከደረሰው መረጃ ለመረዳት ተችሉዋል።

በቅርቡ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዓለም ዙሪያ በምትገኘው በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጥላ ሥር በሚገኙ ሕጻናት ላይ የሚፈጸመውን አካላዊ፣ ስነ-አእምሮኣዊ እና ወሲባዊ ጥቃት በከፍተኛ ደረጃ በማውገዘ ጠንካራ የሆኑ ቃላትን በመጠቀም ይህንን በሚፈጽሙ የቤተ ክርስቲያኒቱ አባላት ላይ የማያዳግም እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ መሆናቸውን ባስተላለፉት መልእክት መገለጻቸው የሚታወስ ሲሆን ከዚህ በተጫማሪም በተለያየ ደረጃ የሚገኙ አንዳንድ የቤተ ክርስቲያኗ አስተዳዳሪዎች የተሰጣቸውን መንፈሳዊ ኃላፊነት በመዘንጋት መንፈሳዊ ስልጣናችውን ያለአግባብ በመጠቀም የመጨቆኛ እና የመበዝበዣ መሳሪያ በማድረግ ላይ እንደ ሚገኙ መግለጻቸው የሚታወስ ሲሆን ይህ ጉዳይ በማነኛውም መስፈርት ተቀባይነት የሌው ጉዳይ እና ከቤተ ክርስቲያኗ መንፈሳዊ አስተምህሮ ጋር በእጅጉ የሚጣረዝ በመሆኑ ድርጊቱን እየፈጸሙ የሚገኙ ሰዎች ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ እና ይህንን ወንጀል በመፈጸሙ ሰዎች ላይ ትዕግሥት አልባ እርምጃ እንዲወሰድ መልእክት ማስተላለፋቸው ይታወሳል።

በካርዲናል ኦ ማሌይ የሚመረው እና ለታዳጊ ሕጻናት ጥበቃ የሚያደርገው ጳጳሳዊ ኮምሽን ውስጥ በከፍተኛ የሥራ ደረጃ ላይ የተሰማሩት የሕገ ቀኖና ትምህርት ሙሁር የሆኑት ፕሮፌሰር ማርያም ዊሄልሰን  ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ባስተለለፉት መልእክት እንደ ገለጹት በቅርቡ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሕጻናት ላይ የተፈጸሙትን አካላዊ፣ አእምሮኣዊ እና ወስባዊ ጥቃቶች በተመለከተ ያስተላለፉት ጠንካራ መልእክት ሦስት ፍሬ ሐሳቦችን አቅፎ መያዙን የገለጹ ሲሆን “ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በመልእክታቸው ወሲባዊ፣ አእምሮኣዊ እና ስልጣንን ያለአግባብ በመጠቀም የሚፈጸሙ ጥቃቶች ተያያዥነት እንዳለቸው በእርግጠኛነት መናግረቸው” አንደኛው እና ዋነኛው ፍሬ ሐሳብ መሆኑን ገለጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቅርቡ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሕጻናት ላይ የተፈጸሙትን አካላዊ፣ አእምሮኣዊ እና ወስባዊ ጥቃቶች በተመለከተ ያስተላለፉት ጠንካራ መልእክት በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠው ፍሬ ሐሳብ ይህንን ጥቃት በሁለት ደረጃዎች መክፈላቸው እንደ ሆነ  የገለጹት ፕሮፌሰር  ማርያም ዊሄልሰን  በቀዳሚነት የሚገለጸው ስልጣንን ያለአግባብ መጠቀም ከሚለው ጽንሰ ሐሳብ ጋር ተያይዞ የመጣ ጥቃት እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው መጥቀሳቸውን አስታውሰው በዚህም ደረጃ አንዳንድ የቤተ ክርስቲያኗ መሪዎች የተሰጣቸውን ሥልጣን ተገን በማድረግ በሕጻናት እና ለጥቃት ተጋላጭ በሆኑ ታዳጊ ወጣቶች ላይ ጥቃት መፈጸማቸው የመጀመሪያው ደረጃ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በሌላ ሰው የተፈጸሙትን ጥቃቶች ሥልጣንን ተገን በማድረግ ለመደበቅ መሞከር ደግም በሁለተኛ ደረጃ የሚጠቀስ ጥቃት እንደ ሆነ ጨምረው ገለጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቅርቡ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሕጻናት ላይ የተፈጸሙትን አካላዊ፣ አእምሮኣዊ እና ወስባዊ ጥቃቶች በተመለከተ ያስተላለፉት ጠንካራ መልእክት በሦስተኛ ደረጃ የሚያስተላልፈው መልእክት “ይቅርታን ጠይቆ የተፈጸሙትን ወንጀሎች ለማለፍ መፈለግ በራሱ በቂ አይደለም” የሚለው የቅዱስነታቸው መልእክት ጠንካራ ጎን እንደ ሆነ የገለጹት ፕሮፌሰር ማርያም ይህንን አስከፊ ጥቃት ዘላቂ በሆነ መልኩ ለማጥፋት  ሥር ነቀል የሆነ እርምጃ መወሰድ ይገባዋል የሚለው   ሦስተኛው የቅዱስነታቸው መልእክት ጠንካራ ጎን እንደ ሆነ ጠቅሰው ይሁን እንጂ ይህንን ጥቃት መከላከል የቤተ ክርስቲያን አባቶች ድርሻ ብቻ ሊሆን እንደ ማይገባ ጠቅሰው ሁሉም የማኅበርሰብ ክፍል በጋር ችግሩን ለመቅረፍ የበኩሉን አስተዋጾ ማድረግ ይገባዋል ብለዋል።

21 August 2018, 16:02