ፈልግ

በአየርላን የኖክ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተመቅደስ በአየርላን የኖክ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተመቅደስ 

በአየርላን የኖክ የእመቤታችን ማርያም ቤተመቅደስ መዘምራን ለቅዱስነታቸው ዝማሬ እንደ ሚያቀርቡ ተገለጸ

ከነሐሴ 15-20/2010 ዓ.ም በአየርላንድ ዋና ከተማ በሆነችው በደብሊን ዓለማቀፍ የቤተሰብ ጉባሄ ይካሄዳል።

በነሐሴ 15-20/2010 ዓ.ም የአየርላንድ ዋና ከተማ በሆነችው በደብሊን በሚካሄደው ዓለማቀፍ የቤተሰብ ጉባሄ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እንደ ምገኙ ይታወቃል። ለዚህ በደብሊን ለምካሄደው ዓለማቀፍ የቤተሰብ ቀን ከወዲሁ ልዩ ልዩ ቅድመ ዝግጅቶች እየተደረጉ እንደ ሆነ ከደረሰን መረጃ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በዚህም መሰረት በደብሊን የሚገኙ ልዩ ልዩ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ማኅበራት በፈቃደኝነት በመሳተፍ ይህ የቤተሰብ ጉባኤ የሰመረ እና ያማር፣ በተጨማሪም ስኬታማ እና መልካም ፍሬ የምገኝበት ጉባሄ እንዲሆን የበኩላቸውን አስተዋጾ በማበርከት ላይ ይገኛሉ። በዚህም መሰረት በአየርላንድ ዋና ከተማ በደብሊን የምገኘው የማሪያም መዘመራን ማኅበር አባላት በዚህ ከነሐሴ 15-20/2010 ዓ.ም በምካሄደው ዓለማቀፍ የቤተሰብ ቀን ጉባሄ ላይ ተገኝተው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እና ከመላው ዓለም የተውጣጡ የዚህ ዓለማቀፍ ጉባሄ ተሳታፊዎች በተገኙበት ልዩ ልዩ መዝሙሮችን ለማስደምጥ ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅታቸውን እንዳጠናቀቁ ተገልጹዋል።

የዚህ ዘገባ አቅራቢ መብራቱ ኃይሌጊዮርጊስ- ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በመጪው ነሐሴ 20/2010 ዓ.ም እሁድ ቀን በአየራላንድ ዋና ከተማ በደብሊን በስተሰሜን በሚገኘው ሥፍራ ከዛሬ 150 ዓመት በፊት መመስረቱ በምነገርለት እና በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም በሚጠራው ኖክ በመባል በሚታወቀው የእመቤታችን እጅግ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተመቅደስ እንደሚገኙ ከወጣው የጉዞ መረሃ ግብር ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በዚያም የሚገኘው የማርያም የመዘምራን መኅበር ለቅዱስነታቸው እና በዚያ ለሚገኙ ምዕመናን መዝሙር እንደ ምያሰሙ ለመረዳት ተችሉዋል። በየርላን ኖክ በመባል የሚታወቀው የእመቤታችን እጅግ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተመቅደስ በአየርላንድ በሰሜኑ ክፍል በሚገኘው ደሴት ላይ የሚገኝ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ ከስፍራው የደርሰን ዜና የሚያስረዳ ሲሆን ይህም ቤተመቅደስ በአየርላንድ በሚገኙ የካቶሊክ ምዕመናን ልብ ውስጥ ታትሙ የሚገኝ፣ ማዮ በምትባል መንደር አከባቢ የሚገኝ ቤተመቅደስ መሆኑን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን የአየርላንድ ጠባቂ ቅዱስ ተብሎ ከሚታወቀው ከቅዱስ ፓትሪክ የሕይወት ታሪክ ጋር የተያያዘ ሥፍራ ነው።

ማርያም በሁሉም የእድሜ ደረጃ ለሚገኙ 15 ሰዎች በወቅቱ ተገልጻ ነበር

እ.አ.አ በነሐሴ 21/1878 ዓ.ም ከ6-75 የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ የማዮ ደሴት ነዋሪዎች በጣም ከባድ እና ነጎድጓድ በበዛበት ዝናብ ውስጥ በወቅቱ  በመጓዝ ላይ በነበሩበት ወቅት በአከባቢው በምትገኘው ትንሽዬ ቤተ ክርስቲያን አናት ላይ እመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ስትገለጽ ይመለከታሉ። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ ሥፍራዎች ለተለያዩ ሰዎች ተገልጻ መታየቷ የሚታወቅ ሲሆን ነገር ግን በዚህ ማዮ በመባል በሚታወቅ ሥፍራ በሚገኘው ትንሽዬ ቤተ ክርስቲያን ላይ 15 በተለያየ የእድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች የተገለጠችበት ሁኔታ ግን ልዩ እና ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የተከሰተ ግልጸት ነበር። ይህ ግልጸት ለየት ያለበት ምንክንያት በወቅቱ ማርያም እንደ ወትሮ ሁሉ ብቻዋን ሳይሆን የተገለጸችው ነገር ግን ከእርሷ ጋር ቅዱስ ዮሴፍ እና ቅዱስ ሐዋሪያው ዮሐንስ አብረዋት መገለጻቸው ይህንን ግለጸት ለየት ያለ የግልጸት ክስተት እንዲሆን አድርጎት ነበር። በወቅቱ ይህንን የግልጸት ክስተት የተመለከቱ በተለያየ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ 15 ሰዎች በትይንቱ ተገርመው እንደ ነበረ ከታሪክ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በተጨማሪም ከቱፊት መረዳት እንደተቻለው 15ቱ ሰዎች ይህንን ግልጸት በተመለከቱበት ወቅት ከፍተኛ በሆነ ዝናብ ውስጥ ቆመው ለሁለት ሰዓታት ያህል ጸሎት ያደርጉ እንደ ነበረ፣ በተጨማሪም ምንም እንኳን በወቅቱ ከፍተኛ የሆነ ዝናብ ይዘንብ የነበረ ቢሆንም ቅሉ፣ ነገር ግን እነዚህ ግልጸቱን ይመለከቱ የነበሩ 15 ሰዎችን ያ ከፍተኛ የሆነ ዝናብ እንዳልነካቸውና ከሁለት ሰዓታት ጸሎት በኋላ ግለጽቱ ማብቃቱ፣ ማርያም እና ከእርሷ ጋር አብረው የተገለጹት ቅዱስ ዮሴፍ እና ቅዱስ ሐዋሪያው ዮሐንስ መሰወራቸውን  ከቱፊት ለመረዳት ተችሉዋል።

የአየርላናዳዊያን እምነት ለማርያም ባላቸው ከፍተኛ አክብሮት ላይ መሰረቱን ያደረገ ነው

ይህ ቀደም ሲል የገለጽነው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ቅዱስ ዮሴፍ እና ቅዱስ ሐዋርያው ዮሐንስ በአየርላን ኖክ በመባል በሚታወቀው ስፍራ በምትገኘው በወቅቱ ትንሽዬ የሆነች ቤተ ክርስቲያን ጫፍ ላይ ለ15 በተለያዩ የእድሜ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ሰዎች የታየው የግልጸት ሁኔታ በወቅቱ በመላው አየርላንድ  በከፍኛ ሁኔታ ተሰርጫቶ የነበረ ወቅታዊ የሆነ ዜና እንደነበረ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የቤተ ክርስቲያኗ አስተዳዳሪዎች ምስክርነቱን በጥንቃቄ አድምጠው፣ መርምረው እና ትክክለኛነቱን ካረጋገጡ በኋላ ለግልጸቱ እውቅና ሰጥተው ነበር።

ይህ ግልጸት በቤተ ክርስቲያኗ አስተዳዳሪዎች እና በሚመለከታቸው የቤተ ክርስቲያን መሪዎች እውቅና ከተሰጠው በኋላ ከዚያም በመቀጠል በስፍራው ከፍተኛ ቁጥር ያለው ምዕመን በመገኘት መንፈሳዊ ንግደት ማድረግ መጀመራቸው እና ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ያላቸውን አክብሮት እና ፍቅር በመግለጽ፣ በእርሷ አማላጅነት ብዙ ጸጋዎችን እና መንፈሳዊ ቱርፋቶችን መቀበላቸውን፣ በተጨማሪም እምነታቸው እንዲያድግ ከፍተኛ አስተዋጾ ያደረገ እና እያደርገ የሚገኝ የእመቤታችን እጅግ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተመቅደስ ሲሆን እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር 1979 ዓ.ም በወቅቱ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት ዮሐንስ ጳውሎስ ሁለተኛ ግማሽ ሚሊዮን ከሚሆን ምዕመናን ጋር ይህንን የኖክ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተመቅደስ መጉብኘታቸው ይታወሳል።

የአዲሱ ቤተመቅደስ ግንባታ

እመቤታችን እጅግ ቅድስት ድንግል ማርያም ከቅዱስ ዮሴፍ እና እንዲሁም ከሐዋሪያው ዮሐንስ ጋር በጋራ ኖክ በሚባልበት ስፍራ በምትገኘው ትንሽዬ ቤተ ክርስቲያን ጫፍ ላይ በተለያየ የእድሜ ደረጃ ለሚገኙ 15 ሰዎች ከተገለጹ ከመቶ አመታት በኋላ ከደም ሲል ከነበረችው ትንሽዬ ቤተ ክርስቲያን ጋር በተገናኘ መልኩ አዲስ በጣም እጅግ ወብ እና ትልቅ የሆነ ቤተመቅደስ ተገንብቱዋል። የዚህ የኖክ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አዲስ ቤተመቅደስ የመሰረት ድንጋይ የተጣለው እ.አ.አ. 1973 በወቅቱ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነበሩት በጳውሎስ 6ኛ አማካይነት ሲሆን የመሰረት ድንጋይ ከተጣለ ከስድስት አመታት በኋላ ግንባታው መጠናቀቁ ይታወሳል። ይህ የኖክ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተመቅደስ በውስጡ “ለእመቤታችን እጅግ ቅድስት ድንግል ማርያም” ክብር የሚገለጽበት 5 የጸሎት ቤቶችን ያካተተ፣ እንዲሁም የቅዱስ ዮሴፍ እና የሐዋሪያው ቅዱስ ዮሐንስ ክብር የሚገለጽበት የተለያዩ የጸሎት ቤቶችን አካቶ የያዘ ቤተመቅደስ ነው።

የኖክ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በሁሉም አየርላንዳዊያን ልብ ውስጥ ትገኛለች

የኖክ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተመቅደስ በተለያዩ ሀገራት በሚገኙ አየርላንዳዊያን ስደተኞች ልብ ውስጥ የሚገኝ ቤተመቅደስ እንደ ሆነ የሚታወቅ ሲሆን በአንድ ወቅት ከግልጸቱ በፊት በድቅድቅ ጨለማ ተሞልታ የነበረችው ገጠራማዋ የማዮ ደሴት መንደር ውስጥ የምትገኘው ትንሽዬ ቤተ ክርስቲያን ከግልጸቱ በኋላ ደግሞ በርካታ አየርላንዳዊያን እና በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን በእየለቱ የሚጎበኙዋት እና በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ጸሎት በማደርግ መንፈሳዊ ጸጋ እና ትሩፋት የሚያገኙበት ቅዱስ ስፍራ በመሆን እያገለገለ የሚገኝ ቤተመቅደስ ሲሆን በተለያዩ ሀገራት ውስጥ በተለያዩ ምክንያቶች ተበታትነው የሚኖሩ የአየርላንዳዊያን  ልብ ውስጥ የሚገኘ ቤተመቅደስ ነው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከነሐሴ 15- 20/2010 ዓ.ም በአየርላንድ ዋና ከተማ በደብሊን በሚካሄደው ዓለማቀፍ የቤተሰብ ጉባሄ ላይ ለመሳተፍ ወደ እዚያው በሚያቀኑበት ወቅት ይህንን የኖክ የእመቤታችን እጅግ ቅድስት ድንግል ማሪያም ቤተመቅደስ እንደ ሚጎበኙ የሚጠበቅ ሲሆን በዚያው የሚገኘው የማርያም መዘምራን ማኅበር ለቅዱስነታቸው እና ከቅዱስነታቸው ጋር በዚያ ስፍራ ለሚገኙ ምዕመናን የተለያዩ መዝሙሮችን እንደ ሚያስደምጡ ከደረሰን መረጃ ለመረዳት ተችሉዋል።

17 August 2018, 09:27