ፈልግ

ር.ሊ.ጳ. ፍራንችስኮስ፣ ስለ አይርላንድ ሐዋርያዊ ጉብኝት የቪዲዮ መልዕክት አስተላለፉ

በአይርላንድ ዋና ከተማ በዳብሊን ከነሐሴ 15 ቀን ጀምሮ ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ስብሰባ በመካሄድ ላይ መሆኑ ይታወቃል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለስብሰባው ተካፋዮች በላኩት የቪዲዮ መልዕክታቸው፣ መጪውን ትውልድ ተረካቢ የሆኑ ወጣቶችን ማዘጋጀት እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ አሳስበዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ ዮሐንስ መኮንን ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በአይርላንድ ዋና ከተማ በሆነችው በዳብሊን ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ስብሰባን በማድረግ ላይ ላሉት የቤተሰብ አባላት በላኩት የቪዲዮ መልዕክታቸው እንደገለጹት፣ በማሕበራዊ ሕይወት ውስጥ ለቤተሰብ የሚሰጠው ቦታ እና ለወጣቶች የተሻለ ሕይወትን ለማዘጋጀት የሚደረገው ጥረት እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው ይህን የቪዲዮ መልዕክት የላኩት በአይርላንድ የሁለት ቀን ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማድረግ መጪው ቅዳሜ፣ ነሐሴ 19 ቀን ከቫቲካን ከተማ ከመነሳታቸው አስቀድመው ነው።  

ወጣቶች የወደ ፊት ተስፋ በመሆናቸው ማዘጋጀትና ብቁ ማድረግ ያስፈልጋል ብለው ይህን የምናደርገው ከቀድሞ ትውልድ መልካም ልምድ በመነሳት ከዛሬ ጀምረን ወጣቶችን ማዘጋጀት ያስፈልጋል ብለዋል።

22 August 2018, 10:16