ፈልግ

9ኛው ዓለማቀፍ የቤተሰብ ቀን በአየርላንድ ዳብሊን ሲከበር 9ኛው ዓለማቀፍ የቤተሰብ ቀን በአየርላንድ ዳብሊን ሲከበር 

9ኛው ዓለማቀፍ የቤተሰብ ቀን የፍቅር ሐሴት በተሰኘው ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን እይታ

ከባለፈው ሰኞ ከነሐሴ 15-20/2010 ዓ.ም ድረስ ለአምስት ቀናት የሚዘልቅ “የቤተሰብ መልካም ዜና ለዓለም ሁሉ ደስታ”  በሚል መሪ ቃል 9ኛው የዓለም የቤተሰብ ቀን በአየርላንድ ዋና ከተማ በዳብሊን በመከበር ላይ እንደ ሚገኝ ይታወቃል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዚህ 9ኛው ዓለማቀፍ የቤተሰብ ቀን ላይ ለመሳተፍ በነሐሴ 19/2010 ዓ.ም ወደ አየርላንድ እንደ ሚያቀኑ ይታወቃል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ለዚህ 9ኛው ዓለማቀፍ የቤተሰብ ቀን አስተንትኖ ይሆን ዘንድ የተመረጠው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራቸስኮስ እ.አ.አ በመጋቢት 19/2016 ዓ.ም. ለንባብ ያበቁት በላቲን ቋንቋ “አሞሪስ ላይቲሲያ” በአማሪኛው በግርድፉ ሲተረጎም “የፍቅር ሐሴት” በሚል አርእስት ይፋ ያደርጉት ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን በዚህ የ9ኛው ዓለማቀፍ የቤተሰብ ቀን በሰፊው ትንታኔ እየተደረገበት የሚገኝ ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን ሲሆን ይህም የሆነበት ምክንያት ይህ ቃለ ምዕዳን  በቤተሰብ ውስጥ ሊኖር ስለሚገባው ፍቅር የሚተነትን ቃለ ምዕዳን በመሆኑ የቤተሰብ አባላት በዚህ ቃል ምዕዳን ውስጥ የተጠቀሱትን ቁምነገሮች በመጠቀም ሕይወታቸውን ማጠናከር እንደ ሚገባቸውም የሚያወሳ፣ ቤተስብ መሰረቱን በእግዚኣብሔር ላይ ማድረግ እንደ ሚገባው፣ የቤተሰብ ደስታ የሚመነጨው በቤተሰብ መካከል ካለው ፍቅር መሆኑን፣ በአንድ ቤተሰብ ውስጥ የሚታየው ደስታ የእዚያ ቤተሰብ ደስታ ብቻ ሆነ የሚቀር ሳይሆን ነገር ግን ለሌሎች በዓለም ውስጥ ለሚገኙ ቤተሰቦች የድስታ ምንጭ ሆኖ እንደ ሚቀጥል፣ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ማንኛውንም በቤተሰብ ውስጥ የሚከሰቱትን ችግሮች እና ተግዳሮቶች በጥንቃቄ እና በእግዚኣብሔር መልኮታዊ ምሕረት በመተገዝ መፍታት እንደ ሚኖርባቸው . . .ወዘተ የሚተነትን ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን በመሆኑ የተነሳ በዚህ 9ኛው ዓለማቀፍ የቤተሰብ ቀን በስፋት አስትንትኖ እንዲደረግበት ተመራጭ አድርጎታል።

አሞሪስ ላይትሲያ የፍቅር ሐሴት የተሰኘው የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን 9 ምዕራፎች ያሉት ቃለ ምዕዳን ሲሆን በአሁኑ ወቅት በአየርላንድ ዋና ከተማ ከባለፈው ከነሐሴ 9/2010 ዓ.ም ጀምሮ በመካሄድ ላይ ባለው  የ9ኛው ዓለማቀፍ የቤተሰብ ቀን አዘጋጅ ኮሚቴ በዚህ አሞሪስ ላይቲሲያ  የፍቅር ሐሴት በተሰኘው የቅዱስነታቸው ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን ላይ ትኩረቱን ያደረገ አውደ ርዕይ ከነሐሴ 16-18/2010 ዓ.ም ድረስ ለሦስት ቀናይ ያህል ማለት ነው በዚሁ ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን ዙርያ ከ116 ሀገራት የተውጣጡ 37 ሺ ሰዎች ተሳታፊ የሆኑበት አውደ ርዕይ ማዘጋጀቱን ለመረዳት ተችሉዋል።

ይህ አወደ ርዕይ በውይይት መልክ በመካሄድ ላይ እንደ ሆነ የገለጹት የዚህ አውደ ርዕይ አስተባባሪ የሆኑት በቅድስት መንበር ሥር የሚተዳደረው የምዕመናን፣ የቤተሰብ እና የሕይወት ጉዳይ የሚመለከተው ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤተ ምክትል ጸሐፊ የሆኑት ወይዘሮ ሊንዳ ጊዞኒ እንደ ገለጹት ይህ ለሦስት ቀናት ያህል እየተካሄደ ያለው እና ከ116 ሀገራት የተውጣጡ 37 ሺ ተሳታፊዎች የሚካፈሉበት አውደ ርዕይ ከዚህ በፊት እንደ ሚደረገው በቃለ ምዕዳኑ ላይ ብቻ በቀጥታ በማትኮር የዚህን ቃለ ምዕዳን ነገረ መለኮታዊ እሴቶችን በመገምገም ላይ ያተኮረ አውደ ርዕይ ሳይሆን ነገር ግን በተቃራኒው በአሁኑ ወቅት የሚገኙ ቤተሰቦች እየኖርቡበት የሚገኘው ተጨባጭ ሕይወት ከግምት ባስገባ መልኩ በመደረግ ላይ እንደ ሆነ ጨምረው ገለጸዋል።

ውይይት፣ ንጽጽር ምስክርነት

ውይይት፣ ንጽጽር እና ምስክርነት የሚሉት ሦስት ቃላት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በተለያዩ አጋጣሚዎች በተደጋጋሚ የሚጠቀሙባቸው ወሳኝ የሆኑ ቃለት እንደ ሆኑ የሚታወስ ሲሆን ይህ አውደ ርዕይ በእነዚህ ቃላት ስነ-አመክንዮ አግባብ እየተካሄደ መሆኑን የገለጹት በቅድስት መንበር ሥር የሚተዳደረው የምዕመናን፣ የቤተሰብ እና የሕይወት ጉዳይ የሚመለከተው ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤተ ምክትል ጸሐፊ የሆኑት ወይዘሮ ሊንዳ ጊዞኒ በተለይም ደግሞ ቅዱስ ሐዋርያው ጳውሎስ ወደ ቆሮንጦስ ሰዎች በጻፈው መልእክቱ ላይ በሚገኘው “(. . .) ከሁሉም የሚበልጠው ግን ፍቅር ነው” በሚለው ሐረግ ዙርያ እየተደረገ የሚገኝ አውደ ርዕይ ሁላችንም በዚህ አግባብ ሕይወታችንን የምንመራ ከሆንን የቤተ ክርስቲያኒቷን ሕይወት በሕይወታችን በመለማመድ፣ ያለ አንዳች ጭፍን ጥላቻ እያንዳንዱ ሰው በሕይወት ምስክርነቱ ለሌላው የምያበረክተው ከሆነ በሕያው ኅብረት፣ በጋራ እያንዳንዳችን የቤተ ክርስቲያንን ሕይወት ልምድ ወደ እያንዳንዳችን ቤት ማምጣት እንችላለን በዚህም የተነሳ በሕይወታችን ታማኝ እና እውነተኛ ደስታን እናገኛለን ማለተቸው ተገሉጹዋል።

በዚህ አውደ ርዕይ ላይ ከተገኙት ተጋባዥ እንግዶች መካከል አንዱ የሆኑት ካርዲናል ክርስቶፈር ሾንቦርን ባለፈው ረቡዕ ማለትም በነሐሴ 16/2010 ዓ.ም ማለት ነው ይህንን አውደ ርዕይ በመሩበት ወቅት እንደ ተናገሩት “ትዳር በአንድ ወንድ እና በአንድ ሴት መካከል የሚፈጸም፣ በፍጹም ሊፈርስ የማይገባው ጥምረት እንደ ሆነ መገለጻቸው” ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ይህም ሊፈርስ የማይገባ እውነተኛ ጥምረት መሰረቱን ግላዊ በሆነ መልኩ ከእግዚኣብሔር ጋር በሚደረግ ግንኙነት ላይ እና በጥንዶቹ መከከል የተፈጥሩ ሕጻንትን ከግምት ያስገባ መሆን እንደ ሚገባው ገልጸዋል።

በእየዕለቱ መጠኑ ይብዛም ይነስም በእያንዳንዱ ቤተሰብ ውስጥ ግጭቶች ሊከሰቱ እንደ ሚችሉ የገለጹት ካርዲናል ክርስቶፈር ሾንቦርን እንዲህ ዓይነት ተግዳሮቶች በቤተሰብ ውስጥ በሚያጋጥሙበት ወቅቶች ሁሉ በዚህ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለንባብ ባበቁት የፍቅር ሐሴት በተሰኘው ቃለ ምዕዳን ዙርያ አስተንትኖ በማድረግ በቤተሰብ ውስጥ የሚነሱ ማነኛውንም ዓይነት ችግሮች እና ጥርጣሬዎች በዚሁ አግባብ ማለፍ እንደ ሚችል ለተጨማሪ እና ለተሻለ ህይወት የሚሆኑ ጠቃሚ መልእክቶችን ማግኘት እንደ ሚቻል ጨምረው ገልጸዋል። የእያንዳንዱ ቤተሰብ ሕይወት እዚህ ደረጃ ላይ የሚደርስ ከሆነ ወላጆች በዚህ አግባብ ከገዛ ቤታቸው ውጪ በመሄድ ለራሳቸው ብቻ ሳይሆን ለጎረቤቶቻቸው፣ ከጎረቤታቸው ወደ ሥራ ቦታ ከዚያም ቀስ በቀስ ወደ መላው ማኅበርሰብ በመሄድ ቤተሰብ ደስተኛ እና በፍቅር የተሞላ ሕይወት እንዲኖር ማድረግ እንደ ሚቻል የገለጹት ካርዲናል ክርስቶፈር ሾንቦርን ከዚያም ባሻገር በመሄድ አሁን ባለንበት ዘመናዊ ዓለማችን የሚኖሩ የአንዳንድ ቤተሰብ አባልት በዲጅታል ቴክኖሎጂ ላይ ያለአግባብ ተዘፍቆ ከሚኖሩበት መላካም ከማይባል የዲጂታል ቴክኖሎጂ ባህል ተላቀው በእውነተኛው ዓለም ውስጥ ይኖሩ ዘንድ ለማገዝ እንደ ሚችላ ካርዲናል ክርስቶፈር ሾንቦርን ጨምረው ገለጸዋል። በተጨማሪም በወላጆች እና በልጆች መካከል ውይይ ማድረግ አስፈላጊ እንደ ሆነ የገለጹት ካርዲናል ክርስቶፈር ሾንቦርን በቤተ ክርስቲያን በምስጢራት ላይ መሰረቱን ያደርገ ሕይወት አስፈላጊ መሆኑን ገለጸው በተለይም ለአቅመ አዳም እና አቅመ ሄዋን ለደረሱ ልጆቻቸው ወላጆች የስነ-ጾታ፣ የጤና፣ ልጆች ስጦታ መሆናቸውን የሚገልጹ፣ በተለይም ደግሞ ሐያቶች በቤተሰብ ውስጥ ያላቸውን ከፍተኛ ሚና የተመለከቱ ትምህርቶች ወላጆች ለልጆቻቸው መስጠት እንደ ሚገባቸው ጨምረው ገለጸዋል።

የቅዱስ ጳውሎስ የፍቅር ውዳሴ

የክርስቲያን ቤተሰብ ሕይወት ዓለማችን  እያጋጠማት ከሚገኙ ዋኛ ችግሮች ጋር ተዛማጅነት እንናዳለው ምንም ክርክር የማያስፈልገው ጉዳይ እንዳልሆነ የሚታወቅ ሲሆን አሁን በከፍተኛ ሁኔታ እየታየ ካለው የስደተኞች ክስተት ጋር በተያያዘ መልኩ እየተፈጠሩ ከሚገኙ የስደተኞች እና የጥገኝነት ጠያቂዎች ጉዳይ፣ ሰዎችን ሕገ-ወጥ በሆነ መልኩ እንዲዘዋወሩ በማድረግ ለከፍተኛ እንግልት እና አደጋ እንዲዳረጉ ማድረግ፣ በኢኮኖሚ መስክ የሚታየውን ከፍተኛ ችግር እና በተለይም ሥራ አጥነት በዓለም ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ የሚንጸባረቅ ዋነኛ ችግር በመሆኑ በእነዚህ እና እነዚህን በመሳሰሉ ተግዳሮቶች የተነሳ የክርስቲያን ቤተሰብ አደጋ ላይ እንዲወድቅ አስተዋጾ አድርገዋል። በተለይም ደግሞ የጋራ መኖሪያ የሆነችው ዓለማችን ከገባችበት ከፍተኛ አጣብቂኝ ውስጥ ማውጣት እንደ ሚገባ የገለጹት በቅድስት መንበር ሥር የሚተዳደረው የምዕመናን፣ የቤተሰብ እና የሕይወት ጉዳይ የሚመለከተው ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤተ ምክትል ጸሐፊ የሆኑት ወይዘሮ ሊንዳ ጊዞኒ ቅዱስ ሐዋርያው ጳውሎስ “(. . .)ከሁሉም የሚበልጠው ግን ፍቅር ነው” ብሎ በተናገረው መሰረት በሁሉም መስክ በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ በቤተሰብ ላይ የተደቀነውን አደጋ ሙሉ በሙሉ ማስወገድ እንኳን ባይቻል መቀነስ ግን እንደ ሚቻል ገለጸዋል። በዚህም መሰረት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በላቲን ቋንቋ አሞሪስ ላይቲሲያ በአማርኛው የፍቅር ሐሴት በሚል አርእስት ቀደም ሲል እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በ2016 ዓ.ም ለንባብ ያበቁት ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን በተለይም በአራተኛው ምዕራፍ ላይ በሰፊው የተገለጸው “የፍቅር ጉዳዮችን” የተመለከቱ ሐሳቦች በጣም ጠቃሚ የሆኑ ምክሮች የተቀመጡበት ምዕራፍ በመሆኑ የተነሳ እግዚኣብሔር ለእያንዳዳችን ካለው ፍቅር በመነሳት ራሳችንን በራሳችን ዘግተን ለራሳችን ብቻ እንዳንኖር የሚመክር እንደ ሆነ የገለጹት የምዕመናን፣ የቤተሰብ እና የሕይወት ጉዳይ የሚመለከተው ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤተ ምክትል ጸሐፊ የሆኑት ወይዘሮ ሊንዳ ጊዞኒ “እኛ አንድ ቤተሰብ ልንሆን የምንችለው እርስ በእርስ ስንዋደድ ብቻ በመሆኑ የተነሳ፣ ከተዋደድን ይህንን ፍቅር እርስ በእርሳችን መለዋወጥ ከቻልን በዚህ የተነሳ ደግሞ ፍቅር እንዲስፋፋ እና ሕይወት እንዲኖረው ማድረግ ይቻላል ብለዋል።

24 August 2018, 11:29