ፈልግ

IRELAND POPE FRANCIS VISIT IRELAND POPE FRANCIS VISIT 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ከብስራተ ገብርኤል ጸሎት በኋላ ያስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት

“በጸሎቴ እንደ ማስባችሁ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ”

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በነሐሴ 20/2010 ዓ.ም በአየርላንድ በሚገኘው የኖክ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተመቅደስ ተገኝተው በዚያው ለተገኙ ከ45ሺ በላይ ለሚሆኑ ምዕመናን ንግግር ካደርጉ በኋላ በመቀጠል ዘወትር በታላላቅ መንፈሳዊ በዓላት እና በዕለተ ሰንበት ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከሚደግሙት፣ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ከሚቀርቡ የመማጸኛ ጸሎቶች መካከል አንዱ እና ዋነኛ የሆነውን “የእግዚኣብሔር መልኣክ ማሪያምን አበሰራት” የሚለውን የመልኣኩ ገብርኤል ጸሎት ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከደገሙ በኋላ ለዓለም ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት በአየርላንድ ማረምያ ቤቶች ውስጥ የሚገኙ ታራሚዎች እርሳቸው በአየርላንድ የሚያደርጉትን ሐዋርያዊ ጉብኝት ሰምተው ለእርሳቸው ደብዳቤ በመጻፋቸው ለየት ባለ ሁኔታ ምስጋና ያቀረቡላቸው ሲሆን “እንዲህ ልላችሁ እፈልጋለው፣ እኔ በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝ” ብለው እንደ ነበረ ከስፍራው ከደረሰን ዜና ለመረዳት ተችሉዋል። “በጸሎቴ እንደ ማስባችሁ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ” በማለት ሳምንታዊ መልእክታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “የምሕረት እናት የሆነችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እንድትጠብቃችሁ እና በእመንት እና በተስፋ እንድታበረታችሁ እማጸናታለሁ” ካሉ በኋላ ሐዋርያዊ ቡራኬያቸውን ሰጥተው መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

Photogallery

የኖክ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተመቅደስ
27 August 2018, 11:49