ፈልግ

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ ለ16 አዳዲስ ካህናት በቫቲካን ማዕረገ ክህነት በሰጡበት ወቅት ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ ለ16 አዳዲስ ካህናት በቫቲካን ማዕረገ ክህነት በሰጡበት ወቅት  

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ ለ16 አዳዲስ ካህናት ማዕረገ ክህነት መስጠታቸው ተገለጸ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ባቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ለ16 አዳዲስ ካህናት ማዕረገ ክህነት መስጠታቸው ታውቁዋል። ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባሳርጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት “ሁልጊዜ የምሕረት መሳሪያ መሆን መታከት የለባችሁም” ማለታቸው ተገለጸ።

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ ለ16 አዳዲስ ካህናት ማዕረገ ክህነት መስጠታቸው ተገለጸ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ባቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ለ16 አዳዲስ ካህናት ማዕረገ ክህነት መስጠታቸው ታውቁዋል። ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባሳርጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት “ሁልጊዜ የምሕረት መሳሪያ መሆን መታከት የለባችሁም” ማለታቸው ተገለጸ።

“የግል ኃጢኣቶቻችሁን በማሰብ ለሌሎች ኃጢኣት ይቅርታን ከማድርግ በፍጹም እንዳትታክቱ” ያሉት ቅዱስነታቸው “ሁልጊዜም ቢሆን እግዚኣብሔርን ለማስደሰት ብቻ መጨነቅ ይኖርባችኃል፣ ለመገልገል ሳይሆን ለማገልገል የመጣውን መልካም የሆነ እረኛ መመልከት ይኖርባችኃል” ማለታቸው ተገልጹዋል።

በወቅቱ ማዕረገ ክህነት የተሰጣቸው ካህናት ከሮም ሀገረ ስብከት የተወጣጡ ካህናት እንደ ነበሩ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን እነዚህ ካህናት ከተለያዩ የዓለማችን ክፍል የተውጣጡ እንደ ሆነም በወቅቱ የተገለጸ ሲሆን 5ቱ ጣልያናዊያን፣ 3 ከሕንድ፣ አንድ ከክሮሺያ፣ አንድ ከሮማኒያ አንድ ከፔሩ፣ አንድ ከቬትናም፣ አንድ ከማያንማር ወይም በቅድሞስ ስሟ በርማ፣ አንድ ከኮሎንቢያ፣ አንድ ከኤል ሳልቫዶር እና አንዱ ከማዳጋስካር እንደ ሆኑ ለመረዳት ተችሉዋል።

እነዚህ ካህናት እግዚኣብሔር ላቀረበላቸው ጥሪ “አውንታዊ” ምላሽ የመለሱበት ቀን የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የክርስቲያን ማኅበረሰቦች ዘንድ አራተኛው የፋሲካ ሳምንት ሰንበት ላይ መልካም እረኛ የሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ በዓል በተከበረበት እና በዓለማቀፍ ደረጃ 55ኛው ለመነፈሳዊ ጥሪ ጸሎት በሚደርግበት እለተ ሰንበት ቀን እንደ ሆነም ለመረዳት ተችሉዋል።

ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባደርጉት ስብከት እንደ ገለጹት “በአዲስ ኪዳን ውስጥ ሊቀ ካህናት የሆነው ኢየሱስ ብቻ እንደ ሆነ” ገልጸው “በእርሱ የመለኮት ሙላት ውስጥ የእግዚኣብሔር የሆኑ ሕዝቦች በሙሉ ተስታፊ ይሆናሉ” ማለታቸው ተገልጹዋል።

“ሆኖም ግን ከሁሉም ደቀ-መዛሙርት መካከል ጌታ ኢየሱስ የተወሰኑትን ለየት ባለ ሁኔታ ለመምረጥ ይፈልጋል፣ ምክንያቱም በቤተክርስቲያን ውስጥ በስሙ ለሁሉም የክህነት አገልግሎት እንዲሰጡ፣ የእርሱን የጌትነት፣ የክህነት እና የእረኝነት ተልዕኮ እንዲያስቀጥሉ በማሰብ መርጡዋቸዋል” ብለዋል።

“ጌታ ኢየሱስ በአባቱ አማክይነት ወደ ምድር እንደ ተላከ ሁሉ፣ እርሱም በተራው ደቀ-መዛሙርቱን ወደ ዓለም ልኮ እንደ ነበረ” የገልጹት ቅዱስነታቸው “በእዚህም አግባባ ጳጳሳትና ቄሳውስት የእርሱ ሥራ ተባባሪ በመሆን የሕግዚኣብሔር ሕዝብ የሆኑትን በሙል በስብከተ ወንጌል፣ የስርዐተ አምልኮ አስተምህሮ በማድረግ፣ በተለይም ደግሞ በመስዋዕተ ቅዳሴ አገልግሎት ሕዝቡን እንዲያገለግሉ መላካቸውን” ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው በወቅቱ የማዕረገ ክህነትን ለመቀበል ለተዘጋጁ 16 ዲያቆናት በተለየ ሁኔታ እንደ ተናገሩት “ጌታ በሆነው በክርስቶስ ተልዕኮ ውስጥ ተሳታፊ መሆን እንደ ሚገባቸው” ገልጸው ይህንን በተመለከተ የሚከተለውን ብለዋል. . . “እናንተ በደስታ የተቀበላችሁትን የእግዚኣብሔር ቃል በደስታ አሰራጩ። ያነበባችሁትን ነገሮች ለማመን፣ ያመናችሁትን ለማስተማር፣ ያስተማራችሁትን ነገሮች ተግባራዊ ለማድረግ ያስችላችሁ ዘንድ በቅድሚያ የጌታን ቃል በሚገባ አንብቡ በቃላቶቹም ላይ ጥልቅ የሆነ አስተንትኖ አድርጉ” ማለታቸው ተገልጹዋል።

“ካህናት የሚናገሩዋቸው ቃላት ለምዕመኑ መንፈሳዊ ምግብ ነው” በማለት ስብከታቸው የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “የክርስቲያኖች ደስታ ለእናንተ ሕይወት መዓዛ እና ድጋፍ ነው” ብለው “ካህናት የተሰጣቸው ዋነኛው ተግባር እና ለየት ባለ ሁኔታ እነርሱን የሚመለከተው ጉዳይ ሊሆን የሚገባው “በምስጢረ ንስሓ አማካይነት በክርስቶስ እና በቤተ ክርስቲያን ስም ሆነው የኃጢኣት ሥርዬት” ማድረግ እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው በአጽኖት ከገልጸው ይህንን በተመለከተ ደግሞ የሚከተለውን ብለዋል. . .“እዚህ ጋር አንድ ጊዜ ቆም ለማለት እፈልጋለሁ፣ አባካችሁን ኃጢኣትን ይቅር ከማለት እንዳትታክቱ። የራሳችሁን የግል ኃጢያቶቻችሁን አስቡ፣ በኢየሱስ አማካይነት ይቅር የተባሉትን አሳሮቻችሁን በማሰብ እናንተም መሓሪዎች ሁኑ” ማለታቸው ተገልጹዋል።

“ሰዎችን ሳይሆን እግዚኣብሔርን ማስደሰት እንደ ሚገባቸው” በመጥቀስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በወቅቱ የማዕረገ ክህነት ለመቀበል በዝግጅት ላይ ለነበሩ 16 አዳዲስ ካህናት “የክህነት አገልግሎታቸውን በደስታ እና ሀቀኛ በሆነ ፍቅር ማከናወን እንደ ሚገባቸው” ገልጸው ይህንን በተመለከተ ደግሞ የሚከተለውን ብለዋል. . .”ራሳችሁን እና ሌሎች ሰዎችን ወይም ደግሞ ሌሎች ፍላጎቶቻችሁን ለሟሟላት ብላችሁ ሳይሆን ለየት ባለ ሁኔታ እግዚኣብሔርን ለማስደሰት ትጉ። እግዚአብሔርን ብቻ አገልግሉ፣ የእግዚኣብሔር ቅዱስ ሕዝብ ደኽንነት እንዲያገኙ የሚረዱ ቅዱስ አገልግሎት ብቻ ፈጽሙ” ማለታቸውም ተገልጹዋል።

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው ማጠቃለያ ላይ እንደ ገለጹት “እናንተ እንደ አንድ መልካም እረኛ በመሆን ራሳችሁን ሌሎችን ለማገልግል ማዘጋጀት ይኖርባችኃል” ካሉ በኃላ ይህንን በተመለከተ ደግሞ የሚከተለውን ብለዋል. . .”ለመገልገል ሳይሆን፣ ነገር ግን ሌሎችን ለማገልገል፣ ለመፈለግ እና የጠፋውን ለማዳን የመጣውን የመልካም እረኛውን ምሳሌ ሁልጊዜ በዓይኖቻችሁ ፊት ለፊት አኑሩት” ካሉ በኃላ ለእለት ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።

10 July 2018, 14:45