ፈልግ

እመቤታችን እጅግ ቅድስት ድንግል ማሪያም እመቤታችን እጅግ ቅድስት ድንግል ማሪያም  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ፡ ለኖተር ዳም ሄኩዊፔስ ማኅበር አባላት መልእክት አሰተለለፉ

ጌታ ሆይ እኔን እንደገና አድነኝ!

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ፡ ለኖተር ዳም ሄኩዊፔስ ማኅበር አባላት መልእክት አሰተለለፉ

በፖርቹጋል ሀገር የዛሬ 100 አመት ገደማ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም በወቅቱ እረኛ ለነበሩ ለሦስት ሕጻናት የተገለጸችበት ፋጢማ በመባል በሚታወቀው የእመቤታችን እጅግ ቅድስት ድንግል ማሪያም የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ቤተመቅደስ በሚገኝበት ሥፍራ በአሁኑ ወቅት የኖተር ዳም ሄኩዊፔስ በሚል መጠሪያ የሚታወቀው መንፈሳዊ እንቅስቃሴ አባላት መንፈሳዊ ጉባሄ ለስድስት ቀናት ያህል ከተደረገ በኃላ በዛሬው እለት መጠናቀቁ ተገልጹዋል።

እነዚህ የኖተር ዳም ሄኩዊፔስ ማኅበር አባላት እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር 1938 ዓ.ም  በፈረንሳይ ሀገር በሚገኘው በኖተርዳም የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካህን በሆኑት በአባ ሄንሪ ካፋሬሌ የተመሰረተ መንፈስዊ እንቅስቃሴ እንደ ሆነ የሚታወቅ ሲሆን የእዚህ የመንፈሳዊ ማኅበር እንቅስቃሴ 122,532 አባላት ያሉት እና በአምስት አህጉራት ውስጥ በሚገኙ በ85 ሀገራት ውስጥ የሚንቀሳቀስ ከቅድስት መነበር ሕጋዊ መብት የተሰጠው መንፈሳዊ ንቅናቄ ነው።

በአሁኑ ወቅት በፖርቹጋል በፋጢማ የእመቤታችን እጅግ ቅድስት ድንግል ማሪያም ቤተመቅደስ በሚገኝበት ሥፍራ የዚህ መንፈሳዊ ንቅናቄ አባላት ጉባሄ በማድረግ ላይ እንደ ሆኑ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ለእዚህ ጉባሄ ተሳታፊዎች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ባስተላለፉት መልእክት እንደ ገለጹት “ቤተክርስቲያን እውነቱን መናገር ስላለባት ኅጢኣትን እንደ ምታወግዝ የገለጹ ሲሆን በተመሳሳይ መልኩ ቤተክርስቲያን ኅጢኣቱን ተገንዝቦ ለመመለስ የሚፈልገውን ኃጢኣተኛ የሆነ ሰው አቅፋ በመቀበል ወሰን የሌለውን የእግዚኣብሔር ምሕርት ይጎናጸፍ ዘንድ የበኩሉዋን ጥረት ታደርጋለች ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

የኖተር ዳም ሄኩፔስ በመባል የሚታወቀው እና በተለይም በባለትዳሮች መካከል ያለውን መንፈሳዊ እሴት ተጠብቆ እንዲሄድ፣ ባለትዳሮች በእለታዊ ሥራዎቻቸው በመጠመዳቸው የተነሳ እና ልጆቻቸውን ለማሳደግ በሚያደጉት እለታዊ ሩጫ እና እንቅስቃሴ የተነሳ መንፈሳዊ ሕይወታቸውን እንዳይዘነጉ የሚያበረታታ መንፈሳዊ ንቅናቄ እንደ ሆነ ይታወቃል።

የእዚህ ማኅበር አባላት ከሐምሌ 9-14 በፖርቹጋል የፋጢማ እመቤታችን እጅግ ቅድስት ድንግል ማሪያም ቤተመቅደስ ውስጥ በመካሄድ ላይ ባለው 12ኛ መንፈሳዊ ጉባሄ ማሪያ ቤርታ እና ጆዜ ሞውራ ሶዋሬስ በተባሉ የእዚህ ማኅበር መስራች በሆኑት ጥንዶች ለዚህ ጉባሄ እንዲሆን የመረጡት ጥቅስ የተወሰደው ጠፍቶ በተገኘው ልጅ ታሪክ ዙሪያ ላይ የሚያጠነጥን እንደ ነበረ ለመረዳት ተችሉዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በእዚህ በመካሄድ ላይ በሚገኘው የመንፈሳዊ ንቅናቄ ጉባሄ ማብቂያ ላይ በፖርቹጋል የቅድስት መንበር ልዑክ በሆኑት ሊቀ ጳጳስ ሪኖ ፓሳጂያቶ አማካይነት ያስተላለፉት መልእክት ቀደም ሲል እንደ ተጠቀሰው ጠፍቶ በተገኘው ልጅ ሕይወት ዙሪያ ላይ ጭብጡን ያደረገ እንደ ነበረ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ጠፍቶ የተገኘው ልጅ ወደ አባቱ በተመልሰበት ወቅት አባቱ በታላቅ ደስታ እንደ ተቀበለው ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው አስታውሰው አባት መቼም ቢሆን ልጆቹን በደስታ ከመቀበል ታክቶ አያውቅም መልሶም የልጅነት መብታቸውን ያጎናጽፋቸዋል ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

“በእንዲህ ዓይነት ታላቅ በጎነት ልባችሁ ተነክቶ. . . ‘እውነት ነው ጌታ ሆይ! እኔ ኃጢአተኛ የሆንኩ ሰው ነኝ’! በማለት ልባችሁ ለጌታ እውነቱን እንዲናገር ወይም እንዲገልጽ አድርጉ! እኔ ጠፍቼ ነበር። በሺህዎች በሚቆጠሩ መንገዶች ከአንተ ፍቅር ሸሽቼ ነበር፣ ነገር ግን እኔ እንደገና ካንተ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን ለማደስ እዚህ ተገኝቻለሁ። አንተ በጣም ታስፈልገኛለህ! ጌታ ሆይ እኔን እንደገና አድነኝ! አሁንም አዳኝ በሆነው ክንድህ ተቀበለኝ በማለት ልንጸልይ ይገባል’” ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

የተዘረጉ የክርስቶስ እጆች

ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን በቀጠሉበት ወቅት እንደ ገለጹት በመስቀል ላይ ተዘረግተው የነበሩትን የክርስቶስ እጆች በማስታወስ እንደ ገለጹት “የክርስቶስ ስቃይ የእግዚኣብሔርን ዘላለማዊ ምሕረት ያሳያል” ብለው ይህንን ሐሳባቸውን ለማጠናከር በማሰብ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ብለዋል. . .

ማንም ሰው ከእግዚኣብሔር ፍቅር ወይም ምሕረት የተገለለ አይደለም፣ ባል ወይም ሚስት፣ ቤተሰብ ወይም ልጆች . . .ወዘተርፈ፣ እርሱ ማንንም ማጣት አይፈልግም፣ በኢየሱስ እይታ ማንም ሰው ለዘለዓለም ጠፍቶ አይቀርም፣ ሁሉንም ሰዎች ኢየሱስ ፈልጎ ያገኛቸዋል፣ እኛም እንደ እነዚ ያሉ የጠፉ ሰዎችን ሂደን እንድንፈልጋቸው ይገፋፋናል፣ በእርግጥ ኢየሱስን ማግኘት ከፈለግን እኛ እርሱን ልናገኘው በምንፈልግበት ሥፍራ ሳይሆን መሄድ የሚኖርብን ነገር ግን እርሱ እኛን ሊገናኘን በሚፈልግበት ሥፍራ ሂደን በእዛ እርሱን ለመገናኘት እንችላለን።

ከሐምሌ 9-14 በፖርቹጋል የፋጢማ እመቤታችን እጅግ ቅድስት ድንግል ማሪያም ቤተመቅደስ ውስጥ በመካሄድ ላይ የነበረው 12ኛው መንፍሳዊ ጉባሄ በዛሬ ዕለት መጠናቀቁ የተገለጸ ሲሆን በእነዚህ 6 ቀናት ውስጥ የማኅበሩ አባላት የዛሬው 100 አመት ገደማ እመቤታችን እጅግ ቅድስት ድንግል ማሪያም በወቅቱ እረኛ ለነበሩ ሦስት ሕጻናት በተገለጸችበት ፋጢማ በመባል በሚታወቅበት ሥፍራ በተካሄደው መንፈሳዊ ጉባሄ በእግዚኣብሔር ቃል ላይ አስተንትኖ የተደረገበር፣ በጋራ የጸሎት ሥነ-ስረዓት የተካሄደበት፣ መስዋዕተ ቅዳሴ የተሳተፉበት፣ የሕይወት ምስክርነት እና የልምድ ልውውጥ የተደረገበት፣ በዕየለቱ በሚደረጉ የወንጌል አስተንትኖዎች የተማረኩበት እና በአጠቃላይ መንፈሳዊ መነቃቃት ያገኙበት የተቀደሰ ጊዜ እንደ ነበረ ከደርሰን መረጃ ለመገንዘብ ተችሉዋል። 

21 July 2018, 13:10