ፈልግ

ሕጻን አልፊዬን ኢቫንስ ሕጻን አልፊዬን ኢቫንስ  

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ፡ ሕጻን አልፊዬን ለመታደግ እስከ መጨረሻ አስፈላጊውን ሕክምና ማድረግ ያስፈላጋል

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ፡ ሕጻን አልፊዬን ኢቫንስን ለመታደግ እስከ መጨረሻ አስፈላጊውን ሕክምና ማድረግ ያስፈላጋል. የ23 ወር ሕጻን ወይም የአንድ አመት 11 ወር እድሜ ያለው አልፊዬ ኢቫንስ የተባለ አንድ እንግሊዛዊ ሕጻን ልጅ ጉዳይ አነጋጋሪ እየሆነ መምጣቱ ይታወቃል። የእዚህ የአንድ አመት ከ11 ወር እድሜ ያለው ሕጻን ልጅ ጉዳይ አነጋጋሪ መሆነ የጀመረው በምያሳዝን መልኩ ይህ ሕጻን ከተወለደ ከስባት ወራት በኃላ አንድ ጤናማ የሚባል ሕጻን ልጅ ልያሳየው የሚገባውን ዓይነት አካላዊ የሆነ አድገት ሳያመጣ ወይም ሳያሳይ ይቀራል። በእዚህም ጉዳይ የተደናገጡት የሕጻን አልፊዪ አባት እና እናት ልጃቸውን በእንግልዚ ሀገር ሊቬርፑል በሚባል ከተማ ወደ ሚገኘው አልዴር ሄይ የሕጻናት ሆስፒታል እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በ2016 ዓ.ም. ላይ ይዘውት ይሄዳሉ።

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ፡ ሕጻን አልፊዬን ለመታደግ እስከ መጨረሻ አስፈላጊውን ሕክምና ማድረግ ያስፈላጋል.

የ23 ወር ሕጻን ወይም የአንድ አመት 11 ወር እድሜ ያለው አልፊዬ ኢቫንስ የተባለ አንድ እንግሊዛዊ ሕጻን ልጅ ጉዳይ አነጋጋሪ እየሆነ መምጣቱ ይታወቃል። የእዚህ የአንድ አመት ከ11 ወር እድሜ ያለው ሕጻን ልጅ ጉዳይ አነጋጋሪ መሆነ የጀመረው በምያሳዝን መልኩ ይህ ሕጻን ከተወለደ ከስባት ወራት በኃላ አንድ ጤናማ የሚባል ሕጻን ልጅ ልያሳየው የሚገባውን ዓይነት አካላዊ የሆነ አድገት ሳያመጣ ወይም ሳያሳይ ይቀራል። በእዚህም ጉዳይ የተደናገጡት የሕጻን አልፊዪ አባት እና እናት ልጃቸውን በእንግልዚ ሀገር ሊቬርፑል በሚባል ከተማ ወደ ሚገኘው አልዴር ሄይ የሕጻናት ሆስፒታል እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በ2016 ዓ.ም. ላይ ይዘውት ይሄዳሉ።

የጤና ባለሙያዎች ለሕጻን አልፊዬ አስፈላጊውን ምርመራ ካደረጉ በኃላ ሕጻኑ ከእዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ባልተለመደ ዓይነት በሽታ እየተሰቃ እንደ ሚገኝ ይደርሱበታል። በሕይወት የመኖር ተስፋው የመነመነ መሆኑን የሕክምና ባለሙያዎች ከገለጹ በኃላ ነገር ግን ሕጻኑን ለማትረፍ አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ ቃል በመግባት ሕክምና ማድረግ ይቀጥላሉ። ነገር ግን በተደጋጋሚ ለሕጻኑ ያደርጉለት ሕክምና በተወሰነ መልኩ የሕጻኑ ጤና እንዲሻሻል አድርጎ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን አሁንም የሕጻኑ የጤና ሁኔታ ይህ ነው የሚባል ለውጥ ሳያመጣ ይቀራል። በእዚህም ምክንያት ሕጻን አልፊዬ የመተነፈሻ መሳሪያ ተገጥሞለት ለበርካታ ወራት ምንም ዓይነት የጤና መሻሻል ሳያሳይ ይቆያል።

በሆስፒታሉ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ሕጻን አልፊዬ ምንም ዓይነት ለውጥ ባለማሳየቱ፣ ሕጻኑ የማገገም እድል ከአሁን በኃላ ስለማይኖረው የተገጠመለት የመተንፈሻ መሳሪያ እንዲነቀል ይወስናሉ፣ ጉዳዩንም ለሚመለከተው ፍርድ ቤት ያቀርባሉ። ይህ ማለት ደግሞ ሕጻኑ አልፊየ በተወለደ በ23 ወሩ ከእዚህ ዓለም በሞት ይለያል ማለት ነው። ጉዳዩ የቀረበለት የእንግሊዝ ፍርድ ቤተ ጉዳዩን ከመረመረ በኃላ እና የገራ የቀኙን ክርክር ካዳመጠ በኃላ ሕጻን አልፊዬ ካሁን በኃላ የማግገም እንድል ስለሌለው የተገጠመልት የመተንፈሻ መሳሪያ እንዲነቀል ይወስናል።

ጉዳዮን በጥብቅ የተቃወሙት የሕጻኑ ወላጆች ይግባኝ በመጠየቅ ወደ ከፍተኛ ፍርድቤት ጉዳዩን ይወስዱታል። የእንግሊዝ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይህንን የይግባኝ ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ቀደም ሲል የተወስነው ውሳኔ ገቢራዊ እንዲሆን በድጋሚ ይወሰናል። በእዚህም መሰረት ሕጻን አልፊዬ የተገጠመለት የመተነፈሻ መሳሪያ ይነቀላል፣ ከእዚያም ሕጻን አልፊዬ በ23 ወር ማለትም በአንድ አመት ከ11 ወር እድሜው ከእዚህ ዓለም በሞት ይለያል ማለት ነው።

ይህንን ጉዳይ በቅርበት ሲከታተሉ የቆዩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ይህንን ውሳኔ በተጋጋሚ የተቃወሙት ሲሆን ሕጻን አልፊዬ የተገጠመለት የመተንፈሻ መሳሪያ እንዳለ እንዲቀጥል ምኞታቸው እንደ ሆነ ገልጸው ማን ያውቃል አንድ ቀን ይህ ሕጻን አልፊዬ አሁን የምሰቃይበት በሽታ መፈወስ የሚችል ቴክኖሎጂ ሊመጣ ይችል ይሆናል በማለት በተደጋጋሚ መናግራቸው ይታወቃል። በእዚህም መሰረት ቅዱስነታቸው በዛሬው እለት ይህንን በተመለከተ ባስተላለፉት የተምጽኖ ምልእክት እንደ ግለጹት “ለሕጻን አልፊዬ የሚደርገው ሕክምና እንደ ሚቀጥል ተስፋ አደርጋለሁ፣ የወላጆቹ ጥልቅ የሆነ ስቃይ እና መከራ ሊደመጥ ይገባዋል” ማለታቸው የተገለጸ ሲሆን ለሕጻን አልፊዬ እና ለወላጆቹ እንዲሁም ይህ ጉዳይ ለሚመለከታቸው ሰዎች ሁሉ በጸሎቴ ከእነርሱ ጋር ለመሆን እፈልጋለሁ ማለታቸው ተገልጹዋል።

የእንግሊዝ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይህንን ጉዳይ በነገው እለት በድጋሚ እንደ ሚመለከተው የገለጸ ሲሆን የሕጻኑ ወላጆች እስካሁን ያደርጉት ጥረት ከንቱ እንደ ነበረ ገልጸው በነገው እለት የሚደርገው የመጨረሻ ውሳኔ በጉጉት እየተጠባበቁ እንደ ሆነ ገለጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ጉዳዩን አስመልክተው እንደ ተናግሩት ሕጻን አልፊዬን እስከ መጨረሻው እስትንፋሱ ድረስ የተቻለውን ሁሉ በማድረግ መንከባከብ እንደ ሚገባ ገልጸው የሰው ልጆችን ሕይወት መንከባከብ በተለይም ደግሞ በእንደዚህ ዓይነት በሽታዎች የሚሰቃዩትን ሕጻናት መንከባከብ እግዚኣብሔር ለእያንዳንዳችን የተሰጠን የፍቅር ተልእኮ መሆኑን ገልጸው ሕጻን አልፊዬ በሮም ከተማ በሚገኘው እና በቫቲካን ስር በሚተዳደረው ባንቢኖ ጀዙ በአማሪኛው ሕጻኑ ኢየሱስ በመባል በሚታወቀው ሆስፒታል መጥቶ እንዲታከም ጥሪ ማቅረባቸውም ያታወሳል።

በትላንትናው እለት ማለትም በሚያዚያ 10/2010 ዓ.ም. ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለትሰበሰቡ ምዕመናን በወቅቱ በምስጢረ ጥምቀት ዙሪያ አድርገውት ከነበረው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በመቀጠል ባስተላለፉት መልእክት ባልተለመደ ዓይነት በሽታ እየተሰቃዩ በሚገኙት " ቪንሰንት ሌምበርት እና ቀደም ሲል የጠቀስነው አልፊዬ ቶማስ” በሚባሉ ሁለት ሕጻናት ዙሪያ ላይ ያደረገ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን ቅዱስነታቸው በወቅቱ አጽኖት ሰጥተው እንደ ተናግሩት “ ከመጀምሪያው ከውልደታችን ቀን አንስቶ እስከ መጨረሻው የሕልፈታችን ቀን ድረስ የሕይወታችን ባለቤት የሆነ እግዚኣብሔር ብቻ በመሆኑ የተነሳ ይህ እግዚኣብሔር የሰጠንን ሕይወት እስከ መጨረሻው ቀን ጠብቀን የማቆየት ኃልፊነት አለብን” ማለታቸ ተገልጹዋል። 

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በወቅቱ ካደርጉት የትምህተ ክርስቶስ አስተምህሮ በመቀጠል የሕጻን አልፊዬ ወላጅ አባት ከሆነው ቶማስ አቫንስ ጋር በቫቲካን በሚገኘው የቅድስት ማርታ ሕጻን ውስጥ ተገናኝተው መወያየታቸውም የተገለጸ ሲሆን የሕጻን አልፊዬ ወላጅ አባት የሆነው ቶማስ ኢቫንስ ይህንን አስቸጋሪ ሁኔታ በትዕግስት እና በጸሎት እንዲወጣው፣ እርሳቸውም በጸሎት ከእርሱ ጋር እንደ ሚሆኑ መናግራቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በተደጋጋሚ ይህ ሕጻን አልፊዬ በቫቲካን ስር በሚተዳደረው እና በሮም ከተማ በሚገኘው ባንቢኖ ጄዙ በመባል በሚታወቀው የሕጻናት ሆስፒታል መጥቶ ሕይወቱ እስከሚያልፍበት ቀን ድረስ እንክብካቤ እንዲደርግለት በተደጋጋሚ ጥሪ ማቀረባቸው የሚታወቅ ሲሆን ነገር ግን ይህ ጥሪ ሕጻን አልፊዬ እየታከበበት የሚገኘበት በእንግልዚ ሀገር ሊቬርፑል በሚባል ከተማ የሚገኘው አልዴር ሄይ የሕጻናት ሆስፒታል እና የእንግሊዝ ፍርድ ቤት ይህንን ጥሪ በተደጋጋሚ ውድቅ ማረጋቸው ይታወሳል። በቅርብ ቀንም የእዚህ ሕጻን የመጨረሻ እጣ ፈንታው በእንግሊዚ ፍርድ ቤት እንደ ሚወሰን ይጠበቃል።

10 July 2018, 14:25