ፈልግ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሐምሌ 15 ቀን 2010 ዓ. ም. ከብስራተ ገብርኤል ጸሎት በኋላ ያስተላለፉት መልዕክት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሐምሌ 15 ቀን 2010 ዓ. ም. ከብስራተ ገብርኤል ጸሎት በኋላ ያስተላለፉት መልዕክት 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በሐምሌ 15/2010 ዓ. ም. ከብስራተ ገብርኤል ጸሎት በኋላ ያስተላለፉት መልዕክት

የሰው ሕይወት መጥፋት እንዳይከሰት፣ ዓለም አቀፉ ማሕበረ ሰብ ቆራጥ ውሳኔዎችን በመውሰድ የጉዞ ዋስትና እንዲሰጣቸው ጥሪዬን አቀርባለሁ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በሐምሌ 15/2010 ዓ. ም. ከብስራተ ገብርኤል ጸሎት በኋላ ያስተላለፉት መልዕክት

ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፣

በመጨረሻዎቹ ሳምንታት፣ በሜዲተራኒያን ባሕር ላይ ስደተኞችን የጫኑ ጀልባዎች በመስመጣቸው በርካታ ስደተኞች ሕይወታቸውን እንዳጡ ከዜናዎች ሰምተናል። በዚህ ኣሳዛኝ ክስተት የተሰማኝን ልባዊ ሐዘን እየገልጽኩ፣ በአደጋው ሕይወታቸውን ያጡትንና፣ ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እንዲያገኙ በጸሎቴ እንደማስታውሳቸው ላረጋግጥ እወዳለሁ። በተጨማሪም ተመሳሳይ የሰው ሕይወት መጥፋት እንዳይከሰት፣ ዓለም አቀፉ ማሕበረ ሰብ ቆራጥ ውሳኔዎችን በመውሰድ የጉዞ ዋስትና እንዲሰጣቸው፣ መብታቸውን እንዲስከብር፣ ሰብዓዊ ክብራቸውን እንዲያስጠብቅ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

ከሮም ከተማ ነዋሪዎችና መንፈሳዊ ጉዞን በማድረግ እዚህ ለተገኛችሁት በሙሉ ሰላምታዬን አቀርባለሁ። በተጨማሪም ከብራዚል ለመጣችሁት፣ ለሪዮ ዶ ሱል ሀገረ ስብከት ምዕመናን ሰላምታዬ ይድረሳችሁ። እንደዚሁም ከስፔን፣ ሰቪላ ሀገረ ስብከት ለመጣችሁ ወጣቶች እና ከፖላንድ ፔልፕሊን ሀገረ ስብከት፣ ለመጭው የብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ጸሎት ለማድረግ አሲሲ ለቆያችሁት ወጣቶችም ሰላምታዬን አቀርባለሁ።

ለልዩ ልዩ ቁምስና ምዕመን እና በኢጣሊያ፣ ቪቸንዛ ሀገረ ስብከት፣ የፒያሶላ ሱል ብረንታ ወጣት ማሕበራት አባላት በሙሉ ሰላምታዬን አቀርባለሁ። ለሁላችሁም መልካም ሰንበት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ። እባካችሁ በጸሎታችሁ እንድታስታውሱኝ አደራ እላለሁ።        

 

22 July 2018, 16:49