ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሳሪዬቮ 2015 ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሳሪዬቮ 2015 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ወንድማማችነትን የሚፈጥር ድልድይ መገንባት ያስፈልጋል” አሉ!

“ድልድይ የምንገነባበት ወሳኝ ጊዜ ላይ ደርሰናል፣ የዛሬው የካቶሊክ የስነ-ምግባር ነገረ መለኮት አስተምህሮ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ወንድማማችነትን የሚፈጥር ድልድይ መገንባት ያስፈልጋል” አሉ!

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ይህንን የተናገሩት ከሐምሌ 19-20/2010 ዓ.ም ድረስ ለሁለት ቀናት ያህል የቆየ የስነ-ምግባር የነገረ መለኮት ምሁራን ጉባሄ “ድልድይ የምንገነባበት ወሳኝ ጊዜ ላይ ደርሰናል፣ የዛሬው የካቶሊክ የስነ-ምግባር ነገረ መለኮት አስተምህሮ” በሚል መሪ ቃል በሳራዬቮ ከተማ ተካሂዶ በተላንትናው እለት በተጠናቀቀው ጉባሄ ላይ ባስተላለፉት መልእክት እንደ ሆነ ለመረዳት ተችሉዋል። በእዚህ ጉባሄ ማብቅያ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ መልእክት ማስተላላፋቸው የሚታወስ ሲሆን ቅዱስነታቸው ለዚህ ጉባሄ ተሳታፊ ለሆኑ የስነ-ምግባር የነገረ መልኮት ምሑራን “ወንድማማችነትን የሚፈጥር ድልድይ ልትገነቡ ይገባል” የሚል ጭብጥ ያዘለ መልእክት ማስተላለፋቸውን ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኋይሌጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በስነ-ምግባር የነገረ መለኮት አስተምህሮ ዙሪያ ለሚሰሩ ወንድ እና ሴት ካቶሊክ ምሁራን እንደ ገለጹት ኅራኄን በተሞላው መልኩ ውይይቶችን በመካሄድ እና በተቻለ መጠን ማኅበራዊ ትስስርን በማጠናከር የክፍፍል ግድግዳን በማፈራረስ የወንድማማችነት መንፈስ በዓለም ዙሪያ ልትገነቡ ይገባል ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

ቅዱስነታቸው ይህንን የማበረታቻ መልእክት ያስተላላፉት ከሐምሌ 19-20/2010 ዓ.ም ለሁለት ቀናት ያህል በቦሲኒያ ሄርዜጎቪና ዋና ከተማ በሆነችው በሳርዬቮ “ድልድይ የምንገነባበት ወሳኝ ጊዜ ላይ ደርሰናል፣ ዛሬ የሚገኘው የካቶሊክ የስነ-ምግባር ነገረ መልኮት አስተምህሮ” በሚል መሪ ቃል በተካሄደው በስነ-ምግባር የነገረ መለኮት አስተምህሮ ዙሪያ ለሚሰሩ ወንድ እና ሴት ካቶሊክ ሙሁራን ጉባሄ ላይ ባስተላለፉት የጹሁፍ መልእክት እንደ ነበረ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ከ80 ሀገራት የተውጣጡ 500 የሚሆኑ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የስነ-ምግባር የነገረ መለኮት ምሁራን በዚህ ጉባሄ ላይ መሳተፋቸውን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ይህ ጉባሄ “የካቶሊክ የስነ-ምግባር ነገረ መለኮት በዓለም አብያተ ክርስትያናት ትስስር ውስጥ” ( WTEWC )  በመባል በሚታወቀው ድርጅት የተዘጋጀ ጉባሄ እንደ ሆነ ከቫቲካን ያገኘነው ዜና ያስረዳል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሳራዬቮ በተካሄደው ጉባሄ ላይ አስተለፈውት በነበረው መልእክት እንደገለጹት የዛሬው ዓለማችን በተፈጥሯዊ ሁኔታዎች እና በሚታየው ክፍፍል የተነሳ አካባቢያችን የነገሰውን  ፍርሃትና የተፈጥሮ አደጋ የፈጠሩትን ስጋት ለማስወገድ በድልድዮች የተሞላች ከተማ በመገንባት በሰዎች፣ በባሕሎች፣ በእምነት ተቋማት፣ በሕይወት ፍልስፍናና በፖሌቲካ ጉዳዮች መካከል ያለውን ልዩነት በማስወገድ የመቀራረቢያ መድረኮችን ማዘጋጀት እንደ ሚገባቸው ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።

ስነ-ምዳራዊ ተግዳሮቶች

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በመልእክታቸው አጽኖት ሰጥተው እንደ ገለጹት አንዳንድ ሥነ ምህዳራዊ ተግዳሮቶች በሰው ልጅ እና በተፈጥሯዊ ግንኙነት አንፃር ብቻ ችግሮችን ወይም ተገዳሮቶችን የሚፈጥሩ ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ከትውልድ ወደ ትውልድ በመተላለፍ በሰው ልጆች መካከል አለመግባባት እንዲፈጠር በማድረግ በጣም ከባደ የሚባሉ ውዝግቦችን ልያስከስቱ ይችላሉ ብለዋል። በዚህ ረገድ አሁን በከፍተኛ ደረጃ እየታየ የሚገኘውን የስደተኞች ሁኔታ በዋቢነት መውሰድ እንደ ሚቻል የገለጹት ቅዱስነታቸው የስደተኞች እና የጥገኝነት ጠያቂዎች ሁኔታ ስነ-ምግባራዊ እና ነገረ መለኮታዊ አስተንትኖዎች እንድናደርግ የሚጋብዝ ሁኔታ እንደ ሆነ ጠቅሰው ማነኛውን ዓይነት ሐዋሪያው ተግባራትን የማከናወኛ እቅዶችን ከማውጣታችን በፊት ከዚህ ጉዳይ ጋራ በሚጣጣም እና መሳ ለመሳ ሊሄድ የሚችል አግባብ ያለው በተጠያቂነት መንፈስ እና በጥንቃቄ ፖሌቲካዊ ፖሊሲዎች ከመውጣታቸው በፊት ተገቢ የሆነ ግንዛቤ እንዲፈጠር መሥራት እንደ ሚኖርባቸው ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።

ይህንን ቀደም ሲል የተጠቀሱትን ሐሳቦች መሠረት በማደረግ ቅዱስነታቸው ጨምርው እንደ ገለጹት እያንዳንዱ ግለሰብ እና እያንዳንዱ ተቋም አመራራቸውን እና አመለካከታቸውን በድጋሚ በመከለስ ለሁላችንም የሚሆን በሀቅ ላይ የተመሰረተ መልኩ በዓለማችን ውስጥ አንድ የጋራ የሆነ ግብ ስላለን ወደ እዚህ የጋራ ግባችን ለመድረስ የሚያስችለን ዓይነት ሕይወት እንዲኖር የተቻለንን ጥረት ማድረግ ይገባል ብለዋል።

በሰዎች መካከል የሚፈጠር ትስስር

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ “የካቶሊክ የስነ-ምግባር ነገረ መለኮት በዓለም አብያተ ክርስትያናት ትስስር” ( WTEWC )  በመባል የሚታወቀውን የዚህ በሳራቴቮ ለሁለት ቀናት ያህል ““ድልድይ የምንገነባበት ወሳኝ ጊዜ ላይ ደርሰናል፣ ዛሬ የሚገኘው የካቶሊክ የስነ-ምግባር ነገረ መልኮት አስተምህሮ” በሚል መሪ ቃል የተካሄደውን ጉባሄ አዘጋጅ ድርጅት በተመለከተ ቅዱስነታቸው እንደ ተናገሩት ይህ ድርጅት በሕዝቦች እና በተለያዩ አህጉራት መካከል የሰነ-ምግባር የነገረ መለኮት አስተምህሮችን በመጠቀም ትስስር ለመፍጠር እያደርገ የሚገኘውን ጥረት ቅዱስነታቸው እንደ ሚያደንቁት ገልጸው ይህንን እቅዳቸውን ገቢራዊ ለማድረግ  ያላቸውን ኃይል እና አቅም በማቀናጀት ተግባራቸውን እንዲቀጥሉ ጥሪ ማድረጋቸው ተገልጹዋል።

28 July 2018, 16:12